Art. 1. Scope of application. . .. . 1 Art. 1. Periods of time. . .. ' 1 An.3. Interpretation. . .. . 1 BOOK I. JURISDICTION OF COURTS CHAPTER 1. GENERAL PROVISIONS Art. ... Courts to try suits unless barred. . .. .. 3 Art. 5. Res judicata. . .. ..,. .. 3

Zerihun98 6 views 59 slides Oct 26, 2025
Slide 1
Slide 1 of 59
Slide 1
1
Slide 2
2
Slide 3
3
Slide 4
4
Slide 5
5
Slide 6
6
Slide 7
7
Slide 8
8
Slide 9
9
Slide 10
10
Slide 11
11
Slide 12
12
Slide 13
13
Slide 14
14
Slide 15
15
Slide 16
16
Slide 17
17
Slide 18
18
Slide 19
19
Slide 20
20
Slide 21
21
Slide 22
22
Slide 23
23
Slide 24
24
Slide 25
25
Slide 26
26
Slide 27
27
Slide 28
28
Slide 29
29
Slide 30
30
Slide 31
31
Slide 32
32
Slide 33
33
Slide 34
34
Slide 35
35
Slide 36
36
Slide 37
37
Slide 38
38
Slide 39
39
Slide 40
40
Slide 41
41
Slide 42
42
Slide 43
43
Slide 44
44
Slide 45
45
Slide 46
46
Slide 47
47
Slide 48
48
Slide 49
49
Slide 50
50
Slide 51
51
Slide 52
52
Slide 53
53
Slide 54
54
Slide 55
55
Slide 56
56
Slide 57
57
Slide 58
58
Slide 59
59

About This Presentation

Art. 1. Scope of application. . .. . 1
Art. 1. Periods of time. . .. ' 1
An.3. Interpretation. . .. . 1
BOOK I. JURISDICTION OF COURTS
CHAPTER 1. GENERAL PROVISIONS
Art. ... Courts to try suits unless barred. . .. .. 3
Art. 5. Res judicata. . .. ..,. .. 3
Art. 6. Review of udgments . 3
Art. 7. P...


Slide Content

የደን አደጋ መከላከልና ዝግጁነት የስልጠና ማንዋል ግንቦት 2011 አዲስ አበባ

ማውጫ I.መግቢያ II.ዓላማ 1.የደን እሳትአደጋ መከላከልና ዝግጁነት 2.የደን ተባይ እና በሽታ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት 3. የደን መጤና ወራሪ አረም አደጋ መከላከልና ዝግጁነት

I.መግቢያ አገራችን የበርካታ ተፈጥሮ ሃብቶች ባለቤት ስትሆን ከነዚህም ውስጥ የደን ሃብት አንዱና ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና አካባቢያዊ ጠቀሜታ በመስጠት ላይ የሚገኝ ሃብት ነው፡፡ ሃብቱ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ እና ለዘላቂ ልማትም የጎላ ሚና አለው፡፡ የደን ሃብት ለሀገራችን የግንባታ ኢንዱስትሪው ግብዓት፣ ለኃይል ምንጭነት፣ ለፋብሪካ ጥሬ እቃነት፣ ለምግብነት፣ ለባህል መድኃኒት ምንጭነት እና ወደ ውጭ ተልከው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ሊያስገኙ ለሚችሉ እንጨት ነክ ላልሆኑ የደን ውጤቶች ምንጭነት በማገልገል ለአገራችን ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ሃብት ነው፡፡

ይህ የሀገራችን የደን ሃብት ካለበት በርካታ ችግሮች ውስጥ የሰድድ እሳት ወይም የደን ቃጠሎ ፤ የደን በሽታና ተባይ እንዲሁም የመጤና ወራሪ አረም ክስተት ነው፡፡ ይህ አሳሳቢ ችግር በሀገራችን ውስጥ በተለያዩ ሥፍራዎች በሚገኙ ደኖች ላይ በተደጋጋሚ የሚከሰትና እየተከሰተ ያለ ችግር ነው፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ ግን ችግሩን ለመከላከል እና ሃብቱን ከውድመት ለማዳን የሚያስችል ሥራ በበቂ መጠንና ትኩረት ተሰጥቶት አልተሰራም፡፡ በዚህም የተነሳ በየጊዜው በርካታ የደን ሃብት እየወደመ ሲሆን ችግሩ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በአካባቢ ላይም ጉልህ አሉታዊ ተጽእኖ ሲያስከትል የቆየና እያስከተለም ያለ ችግር ነው፡፡

በመሆኑም የደን ሃብት ለሀገራችንና ለዓለም እያበረከተ ያለውን ፋይዳ ዘላቂነት ለማረጋገጥ ችግሩን በማስገንዘብ አስቀድሞ ለመከላከልና ሲከሰትም ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራር መከተል የግድ ይላል፡፡ ችግሩን የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ በደኑ አካባቢ የሚኖርን ሰፊ የህዝብ ተሳትፎ መሰረት ያደረገ ከመሆኑም በላይ የተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን የተደራጀና የተጠናከረ አሰራር የሚጠይቅም ነው፡፡ ክልሎችም ይህንን ችግር አስመልክቶ የራሳቸውን እርምጃ ሲወስዱ የቆዩና በመውሰድም ላይ ይገኛሉ፡፡

በአዋጅ ቁጥር 542/1999 የወጣውና አሁን ተሻሽሎ በወጣው በአዋጅ ቁጥር 1065/2010 የሀገራችን የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅም የደን አደጋን በተመለከተ ትኩረት በመስጠት የፌዴራልና የክልል መንግስት ኃላፊነትን፣ በደን ውስጥ ወይም በአካባቢው የሚኖሩ፣ የሚሰሩ ወይም የሚተላለፉ ሰዎችን እንዲሁም አደጋ መነሳቱን የተረዳ ማንኛውም ሰው እና መንግስታዊ ያልሆኑ የግል ድርጅቶች ወይም ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ዘርዝሮ አስቀምጧል፡፡ በመሆኑም ክልሎች አዋጁን ለማስፈጸም እንዲረዳቸውና ይህንን የደን አደጋ ችግር አስቀድመው መከላከል እንዲያስችላቸው አደጋ ሲከሰትም መቆጣጠር እንዲችሉ በማሰብ ይህ የደን አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማኑዋል ተዘጋጅቷል፡፡

II.ዓላማ የደን አደጋ በደን ሃብት ላይ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በአካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለህብረተሰቡ በማስገንዘብ ችግሩን አስቀድሞ መከላከልና ሲከሰትም በአፋጣኝ መቆጣጠር የሚቻልበትን የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ሀገራችን የጀመረችውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እውን ለማድረግ ነው፡፡ ለዚህም ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የደን አደጋ መከላከያና መቆጣጠርያ ስርዓት በመዘርጋት፣ ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠርና የባለድርሻ አካላትን ሚና በመለየት በደን አደጋ ይደርስ የነበረዉን ዉድመት መቀነስ ያስፈልጋል ፡፡

1. የደን እሳትአደጋ መከላከልና ዝግጁነት

የሰደድ እሳት ክስተት፣ ዓይነት እና የሚስፋፋባቸው ምቹ ሁኔታዎች በማንኛውም ጊዜ እሳት ሊከሰት የሚችለው ተቀጣጣይ ነገሮች/ Fuel/ ፣ አየር/ኦክሲጅን/ እና ሙቀት/ Heat ወይም አቀጣጣይ ነገር/ በአንድነት ሲኖሩ ወይም ሲገናኙ ነው፡፡ በደን ቃጠሎ ሁኔታ ተቀጣጣይ ነገሮች የሚባሉት የጫካ/የደን ዕፅዋቶች በሙሉ፣ ኦክሲጅኑ ደግሞ በዙሪያችን ያለው አየር ሲሆን ሙቀቱ ደግሞ የሚመጣው በተፈጥሮ ወይም በሰው አማካኝነት ነው፡፡ ይኸውም በተፈጥሮ ከመብረቅ ወይም በናዳ አማካኝነት በሚፈጠር ሰበቃ የሚከሰትና ለማቀጣጠል መነሻ ሊሆን የሚችል ሲሆን ሌላኛውና በአብዛኛው የሚከሰተው ደግሞ በሰዎች የእለት ተእለት እንቅስቃሴ አማካኝነት ወደ ደኖች የሚገባው አቀጣጣይ ነገር ነው፡፡ ይህም እሳትን ለተለያዩ ተግባራት ሲባል በክብሪት፣ በሲጋራ ወይም አስቀድሞ እንደ ፍም ያሉ የተቀጣጠሉ ነገሮችን ከመኖሪያ አካባቢ ይዞ በመምጣት በደኖች አካባቢ በማቀጣጠል የሚከሰት ችግር ነው፡፡

የእሳት መስፋፊያ መንገዶች በሦስት ደረጃ ተለይተው የሚታወቁ ሲሆን እነዚህም :- - በመጀመርያ ደረጃ በተፈጠረው ሙቀት ተቀጣጣይ ነገሩ/ዕፅዋቱ መቀጣጠል ይጀምራል፣ - ቀጥሎ በተለያዩ መንገዶች ሙቀቱ ወደ አካባቢው ባሉ ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች ይተላለፋል፣ - በመጨረሻም እነዚህ ተቀጣጣይ ነገሮች ሙቀቱን ወደ ራሳቸው ይወስዱና ይቀጣጠላሉ፡፡

በደኖች አካባቢ የሚፈጠረው ይህ ሙቀት/አቀጣጣይ ነገር/ ወደ ሰድድ እሳት የሚሸጋገረውና የሚስፋፋው ሙቀቱ በሦስት መንገዶች በተቀጣጣይ ነገሮች ውስጥ በመተላለፍ ነው፡፡ እነዚህም የሙቀት መተላለፊያ መንገዶች/ Heat transfer/ በእንግሊዘኛው አጠራር Radiation, Convection እና Conduction በመባል ይታወቃሉ፡፡

Radiation አንድ ቦታ ላይ ተቀጣጣይ ነገሮችን በማቃጠል የተፈጠረ ከፍተኛ ሙቀት በአቅራቢያው ወዳለው ተቀጣጣይ ነገር ያለምንም አካላዊ ንክኪ የሚተላለፍበት መንገድ ሲሆን በደን ቃጠሎ ጊዜ የሚፈጠረው ሙቀት ወደ አቅራቢያው ላሉ ተቀጣጣይ ነገሮች የሚተላለፈው በአብዛኛው በዚህ መንገድ ነው፡፡ ይህም ሙቀት በቀላሉ ከፍተኛ ከሆነበት ቁስ አነስተኛ ሙቀት ወዳላቸው ቁሶች ኤሌክቲሮማግኔቲክ በሆነ መንገድ የሚተላለፍበት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ አንድ ቦታ ላይ የተፈጠረ ሙቀት በአቅራቢያው ባለ ተቀጣጣይ ነገር ሙቀት ላይ ተጽእኖ በማሳደር በቀላሉ እንዲቀጣጠል ያደርጋል፡፡ Convection በአንድ ቦታ በመቀጣጠል ላይ ካለ ተቀጣጣይ ነገር/ዕፅዋት/ በሚመነጭ ከፍተኛ ሙቀት ያለው ፈሳሽ /በደን ሁኔታ ሙቀት ያለው ጋዝ/ አማካይነት ሙቀቱ ወደ ላይ በመውጣት በዛፎቹ ቅርንጫፍ/ጎፈሬ አካባቢ ያለውን አየር በማሞቅና በዚህ አካባቢ ያለውን ተቀጣጣይ ነገር በማድረቅ እሳት በቀላሉ እንዲቀጣጠል የሚያደርግ የሙቀት መተላለፊያ መንገድ ነው፡፡

Conduction ደግሞ ሙቀት በማንኛውም ቁስ አካል አማይነት ከፍተኛ ሙቀት ካለበት ቁስ ዝቅተኛ ሙቀት ወዳለው ቁስ አካል የሚተላለፍበት መንገድ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ለሚተላለፍ ሙቀት የቁስ አካል መኖር ወሳኝ ሲሆን ዕፅዋቶች ዝቅተኛ የሙቀት ማስተላለፊያ ቁሶች / poor conductor/ ናቸው፡፡ በመሆኑም በደኖች ውስጥ ሙቀት የሚተላለፈው በዋናነት በ Radiation እና በቅርንጫፎች አካባቢ ደግሞ በ Convection ሲሆን በ Conduction የሚተላለፈው ሙቀት መጠን ዝቅተኛ እና ከጠቅላላው የሙቀት መተላለፊያ መንገዶች 5% ብቻ የሚሸፍን ነው፡፡

የሰደድ እሳቱ እንዲስፋፋ ምቹ ሁኔታ ሊፈጥሩ የሚችሉና ባህሪይውን ሊወስኑ የሚችሉት ሦስት ወሳኝ አካባቢያዊ ጉዳዮች የተቀጣጣይ ነገሮች ሁኔታ፣ የአካባቢው አየር ሁኔታ እና የመሬት አቀማመጥ ናቸው፡፡

የተቀጣጣይ ነገሮች ሁኔታ የተቀጣጣይ ነገሮች ሁኔታ ሲባል በአካባቢው ላይ የሚገኝ ተቀጣጣይ ነገር ዓይነት (ሣር፣ ቁጥቋጦ፣ ጭራሮ፣ መሬት ላይ የረገፉ ቅርንጫፎችና ቅጠሎች፣ ጉቶዎች፣ እ ን ጨቶች፣ ቅርፊቶችና ፍቅፋቂዎች፣ ግንድና ወዘተ)፣ መጠን (እንደ ሣር ያሉ ትናንሽና በቀላሉ ቶሎ የሚቀጣጠሉ፣ ትላልቅና ቶሎ ሊቀጣጠሉ የማይችሉ ነገር ግን ከተቀጣጠሉ በኋላ እሳት ይዘው በአካባቢው ላይ ሊዘገዩ የሚችሉ፣ በአንድ ቦታ ላይ ያላቸው ክምችት መጠን)፣ በተቀጣጣይ ነገሮች ውስጥ የሚገኝ የእርጥበት ወይም የውሃ ይዘት መጠን (እርጥብ ወይም ደረቅ) እና የተቀጣጣይ ነገሩ ስርጭት (ስርጭቱ ወደ ጎንም ሆነ ወደ ላይ ወጥነት ያለው ነው ወይስ አልፎ አልፎ የተከማቸ ወይም ሰብሰብ ያለ ነው?) ማለት ነው፡፡

የአካባቢው የአየር ሁኔታ በአንድ አካባቢ የሚከሰትን የሰደድ እሳት ባህሪይ እና የመስፋፋት ሁኔታ ሊወስኑ ከሚችሉ አካባቢያዊ ጉዳዮች አንዱ ቃጠሎው በሚከሰትበት አካባቢና ወቅት የሚገኝ የአየር ሁኔታ ነው፡፡ ይህም የአካባቢው የአየር ሙቀት መጠን (ሞቃት/ቀዝቃዛ፣ በረሃ/ቆላ/ወይናደጋ/ ደጋ)፣ የንፋስ ሁኔታ (ፍጥነትና አቅጣጫ)፣ በአካባቢው አየር ውስጥ የሚገኝ አንፃራዊ የእርጥበት መጠን (እርጥብ/ደረቅ) እና በወቅቱ የሚገኝ የዝናብ ሁኔታ (በጋ/ክረምት፣ ዝናባማ/ፀሐያማ) የሚሉት ናቸው፡፡

የአካባቢው የመሬት አቀማመጥ ሁኔታ የሰደድ እሳት የሚከሰትበት አካባቢ የመሬት አቀማመጥ ሁኔታም የሰድድ እሳቱን ባህሪይና የመስፋፋት ሁኔታውን ይወስናል፡፡ የሰደድ እሳት የሚከሰትበት አካባቢ የመሬት አቀማመጥ ሁኔታ ማለት ደኑ ያለበት የመሬት ተዳፋት ፣ አቅጣጫ/ Aspect/ ( ወደ ምሥራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ወይም ደቡብ መሆኑና ይህም የአካባቢውን የንፋስ ሁኔታ፣ የእርጥበት መጠን፣ የአካባውን የፀሐይ መጠንና የተቀጣጣይ ነገሮችን ሁኔታና ዓይነት መወሰኑ)፣ የተዳፋቱ መጠን፣ እሳቱ የሚከሰትበት የተዳፋት ክፍል (አናት ላይ፣ መካከል ላይ ወይም ታችኛው ክፍል ላይ መሆኑ)፣ የደኑ ቅርጽ (ጠባብና ረጅም፣ ስፋት ያለው፣ ሸለቆ ውስጥ ያለ፣ ወዘተ) እና ደኑ የሚገኝበት የመሬት ከፍታ (የተቀጣጣይ ነገሮችን የእርጥበትና ዘይት መጠን፣ የዝናብ ሁኔታ፣ የደረቅ ወቅትና እሳት የሚከሰትበትን ወቅት ርዝማኔ ይወስናል) ማለት ነው፡፡

የሰደድ እሳት ዓይነት የሰድድ እሳ ት ዓይነት ሦስት ሲሆን - መሬት ውስጥ ለውስጥ የሚሄድ ( ground fire ) ፣ ከመሬት ላይ የሚሄድ ( surface fire) እና ከመሬት በላይ የሚሄድ ( aerial fire) በመባል ይታወቃሉ፡፡

መሬት ውስጥ ለውስጥ የሚሄድ እሳት፡- ይህ ዓይነቱ የሰድድ እሳት በመሬት ውስጥ የሚገኝ ማንኛውንም ተቀጣጣይ ነገር ማለትም ሥራ ሥሮች፣ የወደቁ የበሰበሱና የተቀበሩ ግንዶችና ቅርንጫፎች እንዲሁም ሊቀጣጠሉ የሚችሉ ማናቸውም ዓይነት ቅሪቶችን የሚያቀጣጥል የሰደድ እሳት ዓይነት ሲሆን ይህ ዓይነቱ የሰድድ እሳት ችግር ሊሆን የሚችለው በዋናነት በደረቅ ወቅቶች ወይም በበጋ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ እሳት ልክ አፈር አልብሶ ከሰል እንደማክሰል ማለት ነው፡፡

ከመሬት ላይ የሚሄድ እሳት፡- ይህ ዓይነቱ የሰደድ እሳት ከመሬት ላይ የሚገኝ ወይም ከመሬት ትንሽ ከፍ ብሎ የሚገኝ ማንኛውንም ዓይነት ተቀጣጣይ ነገሮች ማለትም ቅጠላ ቅጠል፣ ሣር፣ የወዳደቁ ግንዶችና ቅርንጫፎች፣ ጉቶዎች፣ ቁጥቋጦዎች፣ ቅርንጫፎች፣ ጭራሮዎች እና የቆሙ እንጨቶችን የሚያቀጣጥል የሰደድ እሳት ዓይነት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው (99% of all fires) ዓይነት የደን ቃጠሎ ክስተት ነው፡፡

ከመሬት በላይ የሚሄድ እሳት፡- ይህ ዓይነቱ የሰደድ እሳት በደን ውስጥ ከመሬት ከፍ ብሎ በሚገኝ የደን አካል ላይ ማንኛውንም እርጥብ እና የደረቁ ዛፎች ማለትም ቅርንጫፎች፣ የዛፍ አናት፣ የእንጨት ሽበት እና ረጃጅም ቁጥቋጦዎችን የሚያቀጣጥል እና ለመቆጣጠርም እግጅ አስቸጋሪና አደገኛ የሆነ የሰደድ እሳት ዓይነት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰደድ እሳት ከመሬት ላይ የሚሄድ እሳት ሳይኖርም በራሱ ብቻ ደንን ሊያቀጣጥል የሚችል ነው፡፡ የቅርንጫፍ እሳት ( crown fire) በመባልም ይታወቃል፡፡

የሰደድ እሳት መንስኤዎች በሀገራችን የሰደድ እሳት ችግር በዋናነት በተለያዩ ምክንያቶች በሰዎች የሚነሳ ነው፡፡ይህም በአብዛኛው ከአጠቃቀምና ከጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ የሚመጣ ችግር ነው፡፡ ለዚህም መንስኤ የሚሆኑት በዋናነት በተለይ የህዝብ ብዛት ባለባቸው ደጋና ወይና ደጋ አካባቢዎች :- የእርሻ ማሳ ለማስፋፋት /ተዘዋዋ ሪ እርሻ ፍለጋ/፣ የእርሻ ማሳ ለማጽዳትና ለዘር ዝግጁ ለማድረግ፣ በእንስሳት እርባታ በሚተዳደሩ ቆላማ አካባቢዎች በዋናነት የጨሌ ሣር ለማግኘት (በምስራቅ፣ ሰሜን ምሥራቅ፣ ደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ቆላማ አካባቢዎች)፣ ከተሰቀለ ቀፎና የጫካ ማር ለመቁርጥ፣ ከሰል ለማክሰል፣ ለአደን አገልግሎት፣ ሰብልና የቤት እንስሳት የሚያጠቁ የዱር እንስሳትን ለማባረር፣ ተጠቅመዉ ሳያጠፉት በሚጥሉት ሲ ጋራ እና በመሳሰሉት እንደሆነ ማንም ሊያረጋግጥ የሚችለው የቅርብ ጊዜ ትዉስታችን ነዉ፡፡

ሰደድ እሳት በደን ሃብት ላይ እና በአካባቢ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት በደን ላይ በተደጋጋሚ የሚከሰተው ሰደድ እሳት የሀገራችንን የደን ሃብት በማውደም የደን ሽፋናችን እንዲቀንስ ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ ሰደድ እሳት ሲከሰት የደን ሃብትን በማቃጠል ከደኑ የሚገኘውን ማንኛውንም የደን ሃብት ውጤት እንዳናገኝ ከማድረጉም በላይ በዚያ አካባቢ ብቻ የሚገኙ ዝርያዎችንም መልሰን እንዳናገኝ ያደርጋል፡፡ የሰደድ እሳት ክስተት በአካባቢው የሚገኘውን የደን ሃብት ስለሚያወድምና ሥነ ምህዳራዊ ግንኙነቱን ስለሚያቋርጥ የደን ሃብቱ ቀደም ብሎ ይሰጥ የነበረውንም ሥነ ምህዳራዊና አካባቢያዊ አገልግሎት እንዳናገኝ ያደርጋል፡፡ በደኑ ውስጥ የነበሩ የዱር እንስሳት አካባቢውን ለቀው ይሰዳዳሉ፣ በርካቶችም በቃጠሎው ይሞታሉ፡፡ እነዚህ አካባቢያዊ አገልግሎቶች ባለመገኘታቸው ምክንያትም በዋናነት በአካባቢው ላይ እና በአጠቃላይ በሀገራችን ላይ የተለያዩ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፡፡

የሰደድ እሳት የሚከሰትባቸው ወቅቶች በአገራችን የሰደድ እሳት ክስተት ከአየር ንብረት ሁኔታ ጋር የሚያያዝ ሲሆን በዋናነት የሚከሰተው አየሩ ሞቃታማ በሆነ የበጋ ወቅት ላይ እና አልፎ አልፎ በሚከሰቱ የድርቅ ወቅቶች ነው፡፡ በዚህ ወቅት የእፅዋቶች የእርጥበት መጠን ይቀንስና በውስጣቸው ያለው ኬሚካላዊ ይዘትና የዘይት መጠን ( concentrated rather than diluted) በቀላሉ ለመቀጣጠል ምቹ ወቅት ላይ የሚገኝ ነው፡፡

የሰደድ እሳት መከላከያና መቆጣጠሪያ ስልቶች በደን ሃብት ላይ የሚከሰት ሰደድ እሳት የሚያስከትለውን ጉዳት ለማስቀረትና ለመቀነስ የምንከተለው ዘዴ ሁለት ነው፡ ይህም :- 1. ምንም ዓይነት እሳት እንዳይከሰት አስቀድሞ መከላከል /preventive እ ና 2. ከተከሰተም የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ማድረግ / supressive ናቸው ፡፡ ሁለቱም ዘዴዎች ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉትም የተጠናከረ እና የተደራጀ ሥራ ከተሰራ ብቻ ስለሆነ በትኩረት መስራትን ይጠይቃል፡፡

1. ምንም ዓይነት እሳት እንዳይከሰት አስቀድሞ መከላከል 1.1 በችግሩ ዙሪያ የህዝቡን ግንዛቤና ንቃተ ህሊና ለማሳደግ በደኖች አካባቢ ነዋሪ ለሆኑና ከችግሩ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተያያዥነት ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች (አ/አደሮች፣ አርብቶ አደሮች፣ ቱሪስቶች፣ ነዋሪዎች፣ ኢንቨስተሮች፣ ስደተኞች፣ የደን ባለቤቶች፣ የፀጥታ አካላት..) በተለያዩ መንገዶች ማስተማር፣ ማሰልጠን እና ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን መስራት ከምንም በላይ ወሳኝ ተግባር ነው፡፡

የትምህርትና ሥልጠና ሥራው ከወጪና ከጊዜ አንፃር በምን መልክ በቅድሚያ ለነማን ቢሰጥ ውጤታማ በሆነ መልክ ለህዝቡ ሊ ዳረስ ይችላል የሚለውን በመለየት መሰጠት ይኖርበታል፡፡ ይህም ለአንድ አካል የሚተው ተግባር ሳይሆን የተለያዩ አካላት የመገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ነገር ግን ሂደቱን በሚያስተባብር አካል በተቀናጀ መልክ ሊ ሠሩት ይገባል፡፡ የደን ባለሙያዎች፣ የደኑን ዘርፍ የሚመራው መስሪያ ቤትና ውሳኔ ሰጪ አካላት ትልቁን ሚና መጫወት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1.2 የህግ ድጋፍ እና ተፈጻሚነት/ The legal framework ሰደድ እሳት ስለሚያስከትለው ጉዳት ለህብረተሰቡ መንገር፣ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ፣ ማሰልጠን፣ ማስተማር እና በዚህ ዙሪያ ስላለው የህግ አግባብ፣ ስለተከለከሉ ደርጊቶችና ስለሚወሰዱ እርምጃዎች ማሳወቅ ብቻውን በቂ አይሆንም፡፡ ከዚህ ሁሉ አልፈው ድርጊቱን የሚፈጽሙ ስለሚኖሩ አስተማሪ የሆኑ ህጋዊ እርምጃዎችን መውሰድ እና የወጡ ህጎችን ተፈጻሚ ማድረግም ጠቃሚ ነው፡፡

2. የሰደድ እሳት መከላከያ ስልቶች የሰደድ እሳት መከላከያ ስልቶች ሲባል በደኖች ላይ እሳት እንዳይነሳ እንዲሁም ሰደድ እሳት የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ አስቀድሞ የሚወሰድ ማንኛውንም እርምጃ ያካትታል፡፡ የሰደድ እሳትን መከላከል ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠርንም የሚያካትት ሲሆን መቆጣጠርም ልክ እንደ መከላከሉ የተለያዩ ተግባራት ድምር ውጤት ነው፡፡ እሳትን መቆጣጠር ገና እሳቱ እንደተከሰተ በመጀመሪው ደረጃ ፈጣን እርምጃ በመውሰድ ማጥፋት እና በዚህ ደረጃ ያልጠፋን እሳት ሳይስፋፋ በቁጥጥር ሥር ማዋል ማለት ነው፡፡

የሰደድ እሳት መከላከያ ስልቶች የሚከተሉት ናቸው፡ - ሀ/ ለሰደድ እሳት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን መለየትና ማወቅ/ Identification and Mapping of Fire sensitive areas ለሰደድ እሳት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን መለየትና ማወቅ ወቅታዊና ተገቢ የመከላከያ ስራዎችን ለመስራት ከመርዳቱም በተጨማሪ ትኩረታችንን የት አካባቢ ላይ በምን ወቅት ማድረግ እንዳለብን ያመላክተናል፡፡ ለ/ የእሳት ክስተትን መከታተል / Fire detection/ Early Warning ለሰደድ እሳት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ውጤታማ የሆነና ጥንቃቄ የተሞላበት የቅኝት ሥራ ማከናወንና ምልክቶች ሲታዩ በፍጥነት ማሳወቅ እንዲሁም የተነሳ እሳት ካለ በፍጥነት ማጥፋት ወሳኝ ነው፡፡ ይህ የቅኝት ሥራ ለሰደድ እሳት መከሰት ምቹ በሆኑ ወቅቶች እና ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ወቅቱን ጠብቆና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ መከናወን ይኖርበታል፡፡

ሐ/ በደኑ የስረኛው ክፍል በቀላሉ ሊቀጣጠሉ የሚችሉ ዕጽዋቶችን ማጽዳት/ Localized undergrowth clearing በደኖች አካባቢ የሰዎች እንቅስቃሴ ሊበዛባቸው እና ሊዘወተርባቸው የሚችሉ የተለያዩ ቦታዎች ከተቀጣጣይ ነገሮች መጽዳት አለባቸው፡፡ እንዲህ ያሉ አካባቢዎች ለሰደድ እሳት መንስኤነት ከፍተኛ ድርሻ አላቸው፡፡ በመሆኑም በደኖች አካባቢ ያሉ የህዝብ መመላለሻ መንገዶችን እና የእሳት መከላከያ መስመሮችን ተከትሎ ያሉ ዕጽዋቶችን (ሣርን ጨምሮ ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮችን) ማጽዳት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ መ/ ተቀጣጣይ ነገሮች ወደ ጎን ያላቸውን ስርጭት መከፋፈል / Spatial planning ተቀጣጣይ ነገሮች ወደ ጎን ያላቸው ሽፋንና ስርጭት ወጥ ከሆነና ሰፊ ቦታ የሚሸፍኑ ከሆነ እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል አዳጋች ይሆናል፡፡ በመሆኑም ተቀጣጣይ ነገሮች/ ደኖች/ በመሬት ላይ ወደ ጎን ያላቸውን ተከታታይና ሰፊ ስርጭት በሰፋፊ መስመሮች በመከፋፈል ችግሩን ወይም ጉዳቱን መቀነስ ብሎም መቆጣጠር ይቻላል፡፡ ዓላማውም የሰደድ እሳቱን መስፋፋት ለመግታት በቀላሉ በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚያስችሉ የእሳት መከላከያ መስመሮችን / fire break or lines/ ለማዘጋጀት እና የእሳት መቆጣጠሪያ ምቹ ቦታዎችን በደኖች ውስጥ ለመፍጠር ነው፡፡

ሠ/ የተቀጣጣይ ነገሮችን ክምችት መቀነስ/ Fuel reduction Techniques የሰደድ እሳትን ባህሪይ ሊወስኑ ከሚችሉ አካባቢያዊ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ የተቀጣጣይ ነገሮች ክምችት/ fuel load/ ሁኔታ ሲሆን ክምችቱን መቀነስም አንዱ የመከላከያ ስልት ይሆናል፡፡ ረ/ ሲልቪካልቸራል የመከላከያ ተግባራት/ Preventive silviculture የሰደድ እሳትን ክስተት ለደኑ ጤናማና ምርታማ አያያዝ ስንል በቋሚነት በምንተገብራቸው የተለያዩ የደን ማኔጅመንት ወይም እንክብካቤ ተግባራትም/ silvicultural practicies / መከላከል ይቻላል፡፡ ሲልቪካልቸራል የመከላከያ ተግባራት ዓላማም በደኖች ላይ ሊከሰት የሚችለውን የሰድድ እሳት መስፋፋት እና የእሳቱን አቅም በመቀነስ በእሳቱ የሚወድመውን ደን መጠን ለመገደብ የሚያስችል ይዘት እና ስትራክቸር / composition and structure / ያለው የደን ቦታ / forest stand / መፍጠር ወይም እንዲኖረን ማድረግ ነው፡፡

ለሰደድ እሳት መቆጣጠሪያ የሚረዱ መሰረተ ልማቶች በደኖች አካባቢ የመሰረተ ልማቶች መኖር የደን ቃጠሎን ለመከላከል እና ከተከሰተም በኋላ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመቆጣጠር የራቸው ድርሻ አላቸው፡፡ በመሆኑም በደኖች አካባቢ አቅም በፈቀደ መጠን መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ ማድረግ ለአካባቢው ህብረተሰብ እና ለደን ልማቱ ከሚሰጠው ጠቀሜታ ባሻገር ሰደድ እሳት እንዳይከሰት እና ከተከሰተም በፍጥነት ለመቆጣጠር ለሚደረጉ ጥረቶች ስለሚጠቅም በትኩረት መሰራት አለበት፡፡

ለሰደድ እሳት መቆጣጠሪያ የሚረዱ መሰረተ ልማቶች የሚከተሉት ናቸው፡ - ሀ/ የመግቢያ መንገዶች/ Access roads ለ/ ዳጋፊ የእሳት መቆጣጠሪያ ቦታዎች / Support zones – defense lines prepared in advance ሐ/ የውኃ አቅርቦት / Water points መ/ የውኃ መርጫዎች/ Water sprayers

ለሰደድ እሳት መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ሥራ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች የተለያየ መጠን ያለው ምሣር/መጥረቢያ ዶማ፡- ለአፈር መቆፈሪያ፣ ትናንሽ ዕፅዋትንና ሥራሥሮችን ለመቁረጥ፣ አካባቢውን ለማጽዳት ገጀራ፡- ለመቁረጫና መመንጠሪያ አካፋ፡- ለመቆፈሪያ፣ ለመዛቅና ለመጣያ፣ ትናንሽ ሥሮችን ለመከትከቻ እሳት ማጥፊያ/መምቻ፡- ሬክ፡- በጀርባ የሚያዝ የውሃ መርጫ፡- የእሳት ማቀጣጠያ መሣሪያዎች፡- የእጅ መጋዝ

የውኃ ማጠራቀሚያ ታንከሮች፡- በተመረጡ ቦታዎች ላይ ለእሳት ማጥፋት ተግባር የሚውል ውኃ ለማጠራቀም ይረዳሉ፡፡ መኪና፡ የእሳት መከላከያ ኮፍያ/ሄልሜት፡ ቡልዶዘሮች፡- ሂሊኮፕተሮች እና አውሮፕላኖች፡- የመገናኛ ቁሳቁሶች፡- *** መሳሪያዎቹ ከተሟሉ በኋላ አገልግሎት መስጠት የሚችሉና ያልተበላሹ ስለመሆናቸው በየጊዜው በማየት ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ እጀታዎቻቸውና ጫፎቻቸው ያልተሰበሩ፣ ያልታጠፉ፣ ያልተሰነጠቁ፣ ጥሩ ሥለት ያላቸው መሆኑን በማረጋገጥ የማይሰራ ካለ ቀድሞ ማስተካከል ተገቢ ነው፡፡

ሰደድ እሳት ከተከሰተ በኋላ እንዴት ይጠፋል? ሰደድ እሳት ከተከሰተ በኋላ ከላይ በዝርዝር የተቀመጡ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግና በመገንዘብ ማጥፋት ይቻላል፡፡ ይህም፡- መቼ ይጠፋል? በምን ይጠፋል? እንዴት ይጠፋል? በማን ይጠፋል? የሚሉትን መሰረታዊ ነገሮች በጥንቃቄ በመገንዘብ የሚከናወን ሥራ ነው፡፡

እሳት እንደ ተቀጣጠለ በቁጥጥር ሥር ሊውል በሚችልበት ደረጃ በአቅራቢያው በሚገኝ በማንኛውም ሰው በፍጥነት መጥፋት አለበት፡፡ ይህንንም የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም አዋጃችን የማንኛውም ሰው ግዴታ መሆኑን በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ በዚህ ደረጃ መጥፋት ያልቻለና ሰፊ የሰው ኃይል የሚፈልግ እሳትም በፍጥነት መረጃው እንዲደርሳቸው በማድረግ በአካባቢው በሚገኙ የሰለጠኑ ሰዎች እና በአካባቢው ህዝብ በርብርብ መጥፋት አለበት፡፡

እሳቱ እንደተከሰተም በአቅራቢያው ላለ የቀበሌና የወረዳ አመራርና የመንግስት መስሪያ ቤት መረጃውን ቶሎ ማድረስ አስፈላጊና ግዴታም ጭምር እንደሆነ የደን አዋጃችን ላይ ተቀምጧል፡፡ እሳቱን የሚያጠፉ ሰዎች የእሳቱን ባህሪይ፣ መጠን፣ የንፋስ አቅጣጫ፣ የመሬት አቀማመጥ እንዲሁም የወቅቱን የአየር ንብረት ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ከላይ የተዘረዘሩ የተለያዩ ቁሳቁሶችን እና መሳሪያዎችን በመጠቀም እሳቱን ማጥፋት ይኖርባቸዋል፡፡

ይህም እሳቱን በአካል ቀጥታ በማጥፋት ( direct attack) እና በተዘዋዋሪ መልክ ( indirect attack) ተቀጣጣይ ነገሮችን በማስወገድና የአካባቢውን ሙቀት በመቀነስ የሚከናወን ይሆናል፡፡ በዚህ ወቅት የእሳት ማጥፋት ጽንሰ ሀሳብንም ተገንዝቦ መተግበር ይጠይቃል፡፡ ይህም ተቀጣጣይ ነገሮችን ማስወገድ/ማስራብ፣ አየር እንዲያጣ እሳቱን ማፈን እና ሙቀቱ እንዲቀንስ ማድረግ የሚሉትን መሰረታዊ ነገሮች እንደ እሳቱ ክብደት በማየት መርጦ ተግባራዊ ማድረግ ማለት ነው፡፡

እሳት በምናጠፋበት ወቅት የምንወስዳቸው ጥንቃቄዎች እሳት የሚያጠፉ ሰዎች ከላይ የተዘረዘሩ የሰደድ እሳት ባህሪያትን ማወቅና መጠንቀቅ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በመሆኑም እሳት በምናጠፋበት ጊዜ አንዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን ነገር እራሳችን በእሳቱ እንዳንከበብ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እየተቀጣጠለ ያለ ደን መሃል ገብቶ ማጥፋት መሞከርም አደገኛ በመሆኑ መጠንቀቅ አለብን፡፡

በጭስ መታፈንም ከፍተኛ የጤና ችግር ስለሚያስከትል መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ ከእሳት ነበልባልና ከተወርዋሪ እሳት እራስን መጠበቅ እንዲሁም ለአደጋ ጊዜ በቂ የማምለጫ አቅጣጫ ወይም ክፍት መስመር መኖሩን ማረጋገጥና ማመቻት አለብን፡፡ በእሳት ማጥፋት ሥራ ላይ ለሚሰማሩት በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መሰራት አለበት፡፡

የእሳት ቃጠሎ የደረሰበት ደን መልሶ እንዲያገግም ስለማድረግ የሰደድ እሳት ክስተት ከተጠናቀቀ በኋላ በእሳት ቃጠሎው ደኑ ላይ የደረሰው ጉዳት መታየትና መጠናት አለበት፡፡ ይህም ሰደድ እሳቱ ደኑ ላይ ያስከተለው ጉዳት መጠን እና ዓይነት ምን እንደሚመስል ለማወቅ እና ቃጠሎ በደረሰበት ደን ወይም የደን መሬት ላይ ቀጣይ መወሰድ ስለሚገባቸው ዝርዝር ተግባራት ለይቶ ለመተግበር ይረዳል፡፡ በተጨማሪም ቃጠሎው በአካባቢው፣ በማህበራዊው እና በነዋሪዎች ኢኮኖሚ ላይ ያደረሰው ጉዳት ምን እንደሚመስል ማወቅ ቀጣይ ለሚሰራው ሥራ ጠቃሚ ነው፡፡

ቃጠሎው ለአካባቢው ህብረተሰብ የተለያዩ የደን ውጤቶችን እና ግልጋሎቶችን ይሰጥ የነበረ ሰፊ ደን ካወደመ፣ በከተማ አቅራቢያ ወይም ለቱሪዝም እየዋለ ያለ ደን ካወደመ ጉዳቱን የከፋ ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም ከሰደድ እሳት ክስተት በኋላ ጉዳት የደረሰበት ደን መልሶ እንዲያገግም መንከባከብና መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ ቃጠሎ የደረሰበት ደን መልሶ እንዲያገግም የሚወሰደው እርምጃም እንደ ጉዳቱ መጠን የሚለያይ ሲሆን ተግባራቱም ወዲያውኑ መወሰድ የሚገባቸው እና በየጊዜው የሚወሰዱ ይሆናሉ፡፡ የአካባቢው ህብረተሰብም በቃጠሎው ተጎጂ እንጂ ተጠቃሚ ስለማይሆን ጉዳቱን ተገንዝቦ ደኑ መልሶ እንዲያገግም በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲኖረው ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

የህዝብ ተሳትፎና እንቅስቃሴ ከላይ በዝርዝር የተመለከትናቸውን የሰደድ እሳት መከላከያና መቆጣጠሪያ ሥራዎችን ለመስራት ሰፊ የህዝብ ተሳትፎ ያስፈልጋል፡፡ ያለ ህብረተሰቡ ሙሉ ተሳትፎና ተባባሪነት ዉጤታማ የሚሆን የሰደድ እሳት መከላከልና መቆጣጠር ተግባር እንደሌለ ሁሉ ህዝባዊ መሰረት ያለው የሰደድ እሳት መከላከልና መቆጣጠር ሥራ ውጤታማና የደን ሃብታችንን ከጥፋትና ከውድመት የሚከላከል ነው፡፡ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ሙሉና ውጤታማ እንዲሆንም የማስተማርና የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን በስፋት ከማከናወን በተጨማሪ በርካታ ሥራዎችን ያለማቋረጥ መስራትን ይጠይቃል፡፡ በደን አካባቢ የሚኖር ህብረተሰብ ከማንም በላይ በደኑ ላይ ለሚደርሰው ጎጂ የሆነ ተግባርና ክስተት በቅርብ የሚመለከት ነው፡፡

የሰደድ እሳት መከላከያና መቆጣጠሪያ ግብረ-ኃይል እና ብርጌድ በደን ሃብት ላይ የሚደርሰውን የደን ቃጠሎ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ የሚያስተባብር፣ የሚመራ፣ የሚቆጣጠር፣ የሚያደራጅ፣ ለህብረተሰቡ ትምህርትና ቅስቀሳ እንዲሰጥ የሚያደርግ እና በአጠቃላይ አስፈላጊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በበላይነት የሚመራ ግብረ-ኃይል ከክልል ጀምሮ እሰከ ቀበሌ ባለው መዋቅር ያስፈልጋል፡፡ ይህም ግብረ-ኃይል ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ ድርጅቶች እና የህብረተሰብ ተወካዮች የሚዋቀር ነው፡፡ ለዚህ ዓላማ ሌላ ግብረ-ኃይል ማዋቀር ሳያስፈልገን ከዚህ ቀደም የነበረውን የደን ልማትና ጥበቃ ግብረ-ኃይል መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡

በየደረጃው ያሉ የግብረ-ኃይሉ አባላት የሚከተሉት ናቸው፡ - የክልል የደን ሃብት ልማትና ጥበቃ ግብረ-ኃይል 1. የግብርና ቢሮ ኃላፊ……………………………………………………………... ..................... ሰብሳቢ 2. የደን ኢንተርፕራይዝ ባላቸው ክልሎች የኢንተርፕራይዙ ኃላፊ……… … አባልና ፀሐፊ 3. የክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ……...…………………………………………...….... ................... አባል 4. የክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ................................................... ..... አባል 5. የክልል አስተዳደርና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ…………………………………………… …………… አባል 6. የክልል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪ ኤጄንሲ/ቢሮ ኃላፊ.............................. ... አባል 7. በግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሃብት ሥራ ሂደት ባለቤት........................................ .... .አባል 8. በግብርና ቢሮ የደንና አግሮፎረስትሪ መምሪያ/ክፍል ኃላፊ........አባልና ፀሓፊ/ . አባል 9. የክልል አከባቢ ጥበቃና መሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ………………………..... ...... አ .. ባል የዞን የደን ሃብት ልማትና ጥበቃ ግብረ- ኃይል የወረዳ የደን ሃብት ልማትና ጥበቃ ግብረ- ኃይል

የቀበሌ የደን ሃብት ልማትና ጥበቃ ግብረ- ኃይል 1.የቀበሌዋናአስተዳዳሪ/ም/አስተዳዳሪ.......................................................ሰብሳቢ 2.የቀበሌግብርናጽ/ቤትኃላፊ.........................................................................አባል 3. የቀበሌ ፍትህና ፀጥታ ዘርፍ ሰብሳቢ…......……………..…………………….....አባል 4. የቀበሌ ታዋቂ ግለሰቦች ወይምየሀገርሽማግሌዎች/አራት/…...………......አባል 5. የቀበሌ የኃይማኖት መሪዎች /ሁለት/………..........………………..…..............አባል 6. የቀበሌ ት/ቤት ርዕሰ መምህራን.......………………………………...…………...አባል 7. የቀበሌ ማህበራዊ ፍርድ ሸንጎ ሰብሳቢ …………..……………………………...አባል 8. የቀበሌ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጣቢያ ባለሙያ……......……………………ፀሓፊ

ከላይ በየደረጃው በአባልነት ከተካተቱት የግብረ-ኃይል አባላት በተጨማሪ እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ለሰደድ እሳት መከላከልና መቆጣጠር ተግባር ይጠቅማሉ ወይም ይመለከታቸዋል የሚባሉ ተጨማሪ አባላትን ማካተት የሚቻል ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ፡- በደን ኢንቨስትመንት ወይም በደን አካባቢ ባሉ መሬቶች ላይ በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች , ስደተኞች በሚገኙበት አካባቢ የስደተኞችና ስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ኃላፊዎች እና በዩኒቨርስቲዎችና ምርምር ተቋማት አካባቢ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የትምህርት ወይም የምርምር ክፍል ኃላፊዎች ) ይገኙበታል፡፡

በየደረጃው የተቋቋሙት ግብረ-ኃይሎች ተግባርና ኃላፊነትም የደን ልማትንና አጠቃላይ ጥበቃን የሚመለከት ቢሆንም ከሰደድ እሳት አንፃር በዋናነት ችግሩን በታቀደ መንገድ የመፍታት ሥራ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት በየደረጃው የሚዋቀረው ግብረ-ኃይል የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡

የክልል የደን ሃብት ልማትና ጥበቃ ግብረ-ኃይል የስራ ሀላፊነት በክልሉ ውስጥ የሰደድ እሳትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያስችል አጋዥ የሆኑ አሠራሮችን ያመነጫል፣ የአተገባበር መርሃ ግብር እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ በተግባር መተርጎማቸውን ይከታተላል፡፡ በክልሉ ውስጥ የሰደድ እሳት ክስተት ያለባቸው ቦታዎች ተለይተው እንዲታወቁና መረጃቸው እንዲያዝ ያደርጋል፡፡ በክልሉ ውስጥ ለሰደድ እሳት መንስኤ የሚሆኑ ሁኔታዎች እና ወቅቶች ተለይተው እንዲታወቁ ያደርጋል፡፡ በክልሉ ውስጥ ሰደድ እሳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የህብረተሰብ ተሳትፎና ግንዛቤ የሚዳብርበትን አሰራር ይቀይሳል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡

በክልሉ ውስጥ ለሰደድ እሳት መከላከልና መቆጣጠር ተግባር አስተዋጽኦ ያላቸውን ጽሁፎች፣ ፖስተሮችና የመገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ ሌሎች የማስተማሪያ ዘዴዎች እንዲዘጋጁ አቅጣጫ ይሰጣል፣ መፈጸማቸውን ይቆጣጠራል፡፡ በክልሉ ውስጥ ለሰደድ እሳት ተጋላጭ በሆኑ ደኖች አካባቢ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶች፣ ቁሳቁሶች እና የህዝብ አደረጃጀቶች የሚሟሉበትን አቅጣጫ ይቀይሳል፣ አጋር አካላትን ያስተባብራል፣ ሥራውን ይመራል፡፡ ለሰደድ እሳት ተጋላጭ በሆኑ ደኖች አካባቢ ለመከላከል የሚያስፈልጉ ቅድመሁኔታዎች እንዲሟሉ ያደርጋል፡፡ የዞኖችን የደን ሃብት ልማትና ጥበቃ ግብረ-ኃይል ያጠናክራል፣ የሚላክለትንም ሪፖርት ይገመግማል፣ ግብረ መልስም ይሰጣል፣ የወረዳና የቀበሌ ግብረ-ኃይሎች መቋቋማቸውን ይከታተላል፣ ተጋላጭ በሆኑ ደኖች አካባቢ የእሳት መከላከያና መቆጣጠሪያ ብርጌዶች እንዲቋቋሙ ያደርጋል፡፡

የሰደድ እሳትን በተመለከተ በሚፈጸም የወንጀል ድርጊት ከማስተማሩ ጎን ለጎን ህጋዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያደርጋል፡፡ በዚህ ዙሪያ ባሉ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች አፈጻጸምና አተረጓጎም ላይ የሚፈጠርን ጎጂ ሁኔታ መርምሮ የአፈጻጸም መመሪያ ያስተላልፋል፡፡ ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት ለክልል ካቢኔ ያቀርባል፡፡ የ ዞን የደን ሃብት ልማትና ጥበቃ ግብረ-ኃይል የስራ ሀላፊነት የ ወረዳ የደን ሃብት ልማትና ጥበቃ ግብረ-ኃይል የስራ ሀላፊነት

የቀበሌ የደን ሃብት ልማትና ጥበቃ ግብረ- ኃይል የስራ ሀላፊነት በማንኛውም ምክንያት በደኖች ላይ እሳት እንዳይከሰት አስቀድሞ ይከታተላል፣ ይከላከላል፣ ከተከሰተም በፍጥነት በቁጥጥር ሥር ያውላል፡፡ የሰደድ እሳትን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ የቀበሌውን/በደኑ አካባቢ ያለውን ህብረተሰብ፣ ያስተምራል፣ ህዝባዊ መድረኮችን ይፈጥራል፣ ግንዛቤ ያስጨብጣል፣ ያስተባብራል፣ ሙሉ ተሳትፎአቸውን ያረጋግጣል፣ አጥፊዎችን ለይቶ ለህግ ያቀርባል፡፡ የወረዳው ግብረ-ኃይል የሚሰጠውን የሥራ መመሪያ ተግባራዊ ያደርጋል ለሰደድ እሳት መከላከያ እና መቆጣጠሪያ በግለሰብና በደኑ አካባቢ የሚሰሩትንና የሚያስፈልጉ ሥራዎችን በወቅቱ ያሰራል፣ ቁሳቁሶችን ህብረተሰቡ እንዲያሟላ ያስተባብራል፣ መሰራታቸውንና መሟላታቸውን ያረጋግጣል፡፡ የሰደድ እሳትን ከሚያባብሱ ድርጊቶች ህብረተሰቡ እንዲቆጠብ ያደርጋል፡፡ በደኖች አካባቢ የእሳት ብርጌዶችን ያቋቁማል፣ በቂ ሥልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ ከእሳት ብርጌዶች ጋር በቅርበት ይሰራል፣ ድጋፍም ያደርጋል፡፡ የሥራ ሪፖርት ለወረዳ ግብረ-ኃይልና ለቀበሌ ካቢኔ ያቀርባል፡፡ አፈጻጸሙን በየጊዜው ይገመግማል፣ የሚሰጠውን ግብረ-መልስ ይተገብራል

የእሳት ብርጌድ/ቡድን በቀበሌ ደረጃ ከተዋቀረው ግብረ-ኃይል በተጨማሪ ደኖች ባሉበት አካባቢ የሰደድ እሳት ተከላካይና ተቆጣጣሪ ወይም የእሳት ብርጌድ/ቡድን ማቋቋም እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ብርጌድ በቀጥታ ሥራው ላይ የሚሰማራና በቅርብ የሚከታተል ስለሚሆን በወረዳ ደረጃ በቂ ሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ሊሰጠው ይገባል፡፡ የእሳት ብርጌድ/ቡድን የሰደድ እሳትን ክስተት በቅርበት የሚቃኝና ችግሩ ሲከሰትም በፍጥነት የማጥፋት ሥራውን በራሱም ሆነ በአቅራቢያው ያለውን ህብረተሰብ አስተባብሮ የሚሰራ ቡድን ነው፡፡

ማጠቃለያ በአጠቃላይ የሰደድ እሳት ክስተት በሀገራችን የደን ሃብት ላይ ከፍተኛ ውድመት እያስከተለ ያለ ችግር በመሆኑ ልንከላከለውና ልንቆጣጠረው ይገባል፡፡ የሰደድ እሳትን የሚመለከት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራ እና የመከላከያና የመቆጣጠሪያ ተግባራት ውጤታማ የሚሆኑት በተገቢው ሁኔታ ታቅደውና በተደራጀ መልክ ሲፈጸሙ ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ክልላዊ የሰደድ እሳት አያያዝ/ማኔጅመንት/ ዕቅድ ሊኖረን ያስፈልጋል፡፡ ይህም ዕቅድ ለእያንዳንዱ የደን ቦታ እራሱን ችሎ የሚዘጋጅ እና የሚከተሉትን ነጥቦች የሚያካትት ነው፡፡ እነዚህም እንደ ቅደም ተከተላቸው ፡- አስቀድሞ ችግሩን መከላከል፣ ክትትል ማድረግ፣ ተዘጋጅቶ መጠበቅ፣ ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ፣ የእሳትን ክስተት ቀድሞ/ሳይስፋፋ በቁጥጥር ስር ሊውል በሚችልበት ደረጃ ማወቅ፣ ችግሩ ሲከሰት በፍጥነት በቁጥጥር ሥር ማዋል እና እሳት ከተከሰተ በኋላ ቃጠሎ የደረሰበት ደንና የደን መሬት አያያዝ ናቸው፡፡

በተጨማሪም በችግሩ ዙሪያ በዕውቀት የበለጸገ የህብረተሰብ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ በትኩረትና በዕቅድ ተይዞ ሊሰራ ይገባል፡፡ የመከላከያና የመቆጣጠሪያ ስልቶችን ማወቅ፣ አስፈላጊ የቅድመ መከላከል ተግባራትን መፈጸም እና አጋርና ባለድርሻ አካላትን በተለያዩ ሁኔታዎች ማሳተፍ ችግሩን ለመቅረፍ ትልቅ አቅም ይሆናል፡፡ አዲሱም ሆነ ነባሩ የደን አዋጅ ይህንኑ ተሳትፎ የሚያበረታታና የደን ቃጠሎን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በዜጎች ላይ ያሉ ግዴታዎችን በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ በመሆኑም በተባበረና በተደራጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ እንዲሁም ዕቀውቀትን መሰረት በማድረግ ችግሩን ልንከላከለው ይገባል፡፡
Tags