Training for parents disability & Rehab.pptx

king633743 1 views 19 slides Sep 18, 2025
Slide 1
Slide 1 of 19
Slide 1
1
Slide 2
2
Slide 3
3
Slide 4
4
Slide 5
5
Slide 6
6
Slide 7
7
Slide 8
8
Slide 9
9
Slide 10
10
Slide 11
11
Slide 12
12
Slide 13
13
Slide 14
14
Slide 15
15
Slide 16
16
Slide 17
17
Slide 18
18
Slide 19
19

About This Presentation

physiotherapy skill, basic rehabiltation skill for parents of Cwds.


Slide Content

የአካል ጉዳተኝነት ጽንሰ ሀሳብና አካል ጉዳተኞችን የተመለከቱ ጉዳዮች

የአካል ጉዳተኝነት ማለት ምን ማለት ነዉ ? የአካል ጉዳት ምን ማለት እንደሆነ የሚያሣይ ዓለም አቀፋዊና ወጥ የሆነ የጋራ ስምምነት የተደረሰበት ትርጓሜ የለም ፡፡ ስለዚህ አካል ጉዳተኝነት በየጊዜው እየተሻሻለ የሚሄድ ሰፊና ውስብስብ ፅንሰ ሀሣብ ነው ፡፡

… የቀጠለ የአካል ጉዳተኛ ማለት የተለያዩ መሰናክሎች ከሚያስከትሏቸው ተጽእኖዎች የተነሳ ከሌሎች አቻዎቹ /ቿ/ ጋር በእኩል ደረጃ በማህበረሰቡ ውስጥ ሙሉና ውጤታማ ተሳትፎ እንዳያደርግ / እንዳታደርግ ሊገድቡ ከሚችሉ የረዥም ጊዜ አካላዊ ፣ አእምሮአዊ ፣ ሥነ-አእምሮአዊ ወይም የስሜት ህዋሳት እክል / እክሎች ያለበት ሰው ነው ፡፡” ( UNCRPD, 2006, p. 4 ).

ስለዚህም አካል ጉዳተኝነት የምንለው በአካል ጉዳተኞችና በህብረተሰቡ መካከል በሚፈጠረው የተዛባ አመለካከት፣አካባቢያዊ፣የመረጃና ተ ቋ ማዊ መሰናክሎች ምክንያት በህብረተሰቡ ውስጥ የሚኖራቸው ሙሉ ተሣትፎና ተጠቃሚነት ሲገደብና ሲቀንስ ነው ፡፡

ዉ ስነት እና አካል ጉዳተኝነት ዉ ስነት + መሰናክሎች = አካል ጉዳት ዉ ስነት + አስቻይ ከባቢ = አካታችነት

የአካል ጉዳተኝነት መንስዔዎች የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ በቅድመ ወሊድ፣ በወሊድ ወቅትና ከወሊድ በኋላ በሚፈጠሩ የተለያዩ ጉዳቶች፣ የትራፊክ አደጋዎች፣ ግጭቶች፣ ተላላፊ በሽታዎች፣ ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶች፣ ተደጋጋሚ ድርቅና ረሃብ፣ ሌሎች ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ዋና ዋናዎቹ የአካል ጉዳት መንስኤዎች ናቸው፡፡ በቅድመ ወሊድ፣ በወሊድና ድህረ ወሊድ ወቅት የሚፈጠሩ አንዳንድ የአካል፣ የስሜት፣ የህዋሳትና የአእምሮ ጉዳቶች በ ቤተሰቦች፣ እንክብካቤ አድራጊዎች እና አገልግሎት ሰጪዎች ተገቢውን መረጃና ግንዛቤ ቢያገኙ ችግሮቹ ሊቃለሉ እንደሚችሉ ይታመናል :: አካል ጉዳተኝነት መንስዔዎች በሽታ 38.7% በአደጋ15.1% በጦርነት11.3 ከወሊድ በፊት 9.4 % ከወሊድ በኋላ 5.7 % ድብደባ 2.8% እሳት 2.0 % ምክንያቱ የማይታወቅ 0.6% በአጠቃላይ 85.3% አካል ጉዳተኝነት መንስዔዎች ልንከላከል የምንችላቸዉ ምክንያቶች ናቸዉ ፡፡ (YOHANNIS F & JOHANNA M.,2005, Prevalence and impact of disability in north-western Ethiopia)

በሀገራችን የ አካል ጉዳተኝነት መንስኤዎች ዋና ዋናዎቹ ድህነት፡ - ኋላቀር የአመጋገብ ሥርዓት፣ ንፁህ የመጠጥ ውሃ እጥረት፣ የሕክምና አገልግሎቶች አለማግኘት በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እንዲከሰት ምክንያት ይሆናሉ፡ በሌላ አገላለፅ ድህነት አካል ጉዳትን ያስከትላል የአካል ጉዳት ደግሞ ድህነትን ያባብሳል፣

አደጋ አደጋ ፡ - በአሁን ወቅት የመሰረተ ልማት ማደግን ተከትሎ የመንገድ ትራፊክ ፣ የኮንስትራክሽን እና የኢንዱስትሪ አደጋዎች ፣ የአካል ጉዳተኝነትን የሚያስከትሉ ዋነኛ መንስዔዎች ሆነዋል ፣ ጦርነት ፡ - ጦርነት ተዋጊዎችን ብቻ ሳይሆን ሰላማዊ ሰዎችንም የአካል ጉዳተኛ ያደርጋል ፡ ፡ መሬት ውስጥ የሚቀበር ፈንጅ እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች የአካል ጉዳተኝነትን ያበራክታሉ ፣

የሕክምና እንክብካቤ እጥረት ፡ - በቂ የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እንክብካቤ እጦት እንዲሁም በአደጋ ወቅት ወይም ከአደጋ በኋላ አስፈላጊ የቀዶ ጥገና ሕክምና እጦት ፣ የአካል ጉዳትን ያስከትላሉ ፣ የመረጃ እጥረት ፡- በአካል ጉዳት መንስኤዎች መከላከያና የህክምና አገልግሎት ድጋፎች በተመለከተ በቂ እውቀት ፣ ግንዛቤና መረጃ እጥረት ፣ አካል ጉዳተኝነትን ያባብሳል ፣

የአካል ጉዳት መንስኤዎች የቀጠለ .. አካባቢያዊ መንስዔዎች ፡- የተለያዩ ዓይነት ወረርሽኞች ፣ የእርስ በርስ ግጭቶች ፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ፣ የመኪና አደጋዎች ፣ በመርዛማ ውጋጅ እና ጎጂነት ባላቸው ነገሮች መመረዝ ፣ የአካል ጉዳት መንስዔዎች ናቸው ፣ የእርጅና ሂደት ፡- የጤና ሽፋን ማደግ እና የአናኗር ዘይቤ መሻሻል ረጅም እድሜ የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል ፡፡ በሰዉነት ላይ የሚከሰቱ ለውጦች እንደ የጡንቻ መጠን ፣ የደም መጠንና የአጥንት ክብደት መቀነስ ፣ የአካል ጉዳትን ሊያስከትሉ ይችላሉ ፡ ፡

ተፈጥሮአዊ ሁኔታዎች፡- የሰውነት እንቅስቃሴን የሚያግዱ በርካታ ሁኔታዎች በወሊድ ወቅት ይፈጠራሉ፡ ፡ እነዚህም የቅርጽ መዛባትን፣ የአንድ ወይም ከዛ በላይ የሰውነት ክፍሎች መጓደልን ወይም በትክክል መንቀሳቀስ አለመቻልን ያካትታሉ፡ ፡ የአካል ጉዳት መንስኤዎች የቀጠለ..

የአካል ጉዳት ዓይነቶች 1 . የስሜት ሕዋሳት ጉዳት ዓይነት / sensory impairments / ዓይነሥውርነት ፣ ( በከፈል ወይም በሙሉ አለማየት ) የመስማት የጆሮ ፣( በከፊል ወይም በሙሉ አለመስማት ) የማሸተት አፍንጫ ፣( ሽታን ወይም ጠረንን አለመለየት ) ከመቅመስ ጋር የተያያዘ የምላስ ስነት ፣ 2. የአካላዊ ጉዳት ዓይነት /physical disability/ - ከእጅ ፣ እግር ፣ ደረት ፣ ትከሻ ፣ መቀመጫ ጋር የተያያዙ ዉ ስነቶች ፣

3. የአእምሮ ዕድገት ውስንነት / Intelectual Disability ኦቲዝም፣ከትምህርትና ከማወቅ ፣ አካባቢን ከመገንዘብ ጋር የተዛመደ ፣ ምሳሌ ፡- ፅሑፍን ከተለመደው በተለየ ሁኔታ መገንዘብ ፣ ወደጐን በመገልበጥ ፣ በመዘቅዘቅ መጻፍ ፣ ሌሎች በጣም ሰፊና ስምምነት ያልተደረሰባቸው ጉዳቶችንም ያካትታል ፡፡

4. ሳይኮ ሶሻል የጉዳት ዓይነት ( ማህበረ-ስነ ልቦና ) በአንድ ሰው ላይ በአንድ ወቅት በሚደርስ ልዩ ሁኔታ የሚያጋጥመው የስነ-ልቦና ጫና የሚከሰት ነዉ ፡፡ ለምሳሌ ፤- በመጫጫን ፣ ድብርት ፣ በግልና በማህበራዊ ሕይወት ከሚጠበቅ እንቅስቃሴ መታጐል ( አለመነጋገር ፣ መገለል ፣ ለረጅም ሰኣት መተኛት ፣ ብቸኝነት እና ወዘተ . . .)

አካል ጉዳተኝነት አለመቻል አይደለም !!!

እናመሰግናለን !