የ 2016 ዓ.ም የምዝገባ አስፈጻሚዎች የውይይት ሰነድ PPT.pptx

sami774951 0 views 19 slides Oct 09, 2025
Slide 1
Slide 1 of 19
Slide 1
1
Slide 2
2
Slide 3
3
Slide 4
4
Slide 5
5
Slide 6
6
Slide 7
7
Slide 8
8
Slide 9
9
Slide 10
10
Slide 11
11
Slide 12
12
Slide 13
13
Slide 14
14
Slide 15
15
Slide 16
16
Slide 17
17
Slide 18
18
Slide 19
19

About This Presentation

This document is publshed


Slide Content

የ2016 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ግምገማ እንኳን ደህና መጣችሁ ! ህዳር /201 7 ዓ.ም የትምፈአ / አዳማ ኢትዮጵያ

የ ውይይት መድረኩ ይዘት መግቢያ የ ውይይቱ ዓላማና የሚጠበቅ ውጤት የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ፣ በምዝገባ አፈጻጸም ያጋጠሙ ችግሮ ች የተወሰዱ መፍትሔዎች ማጠቃለያና የ ቀጣይ አቅጣጫዎች

መግቢያ የተፈታኞች ምዝገባ ለትምህርት ጥራትና ግብአት መሟለት ሂደት መሰረታዊ መረጃዎች የሚሰበሰብበት ወሳኝ ሂደት በመሆኑ በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ ሊፈጸም የሚገባ ተግባር ነው ፤ ምዝገባ ተፈታኞች ለትምህርት ደረጃው የተዘጋጀውን ሥርአተ ትምህርት በተቀመጠው የትምህርት አሰጣጥ መርሃ ግብር መሰረት ተምረው ሲያጠናቅቁና ራሳቸውን ለፈተና ዝግጁ መሆናቸውን ሲያረጋግጡ ፈተናውን ለመውሰድ በተዘጋጀው የፈተና አሰጣጥ መርሃ ግብር ና አይነት (intended exam schedule and Modality) መሰረት ለመውሰድ የሚመዘገቡበት ሂደት ነው ፤ በምዝገባ ሂደት የምዝገባ አስፈጻሚዎች ለምዝገባ የሚያስፈልገውን የምዝገባ ማስፈጸሚያ ግብአትና የተሟላ ግንዛቤ ጨብጠው ወደ ሂደቱ መግባት ካልቻሉ የተፈለገውን የተፈታኝ መረጃ ማግኘት ስለማይቻል ቀጣዩ የፈተና አሰጣጥ ሂደት ችግር ውስጥ እንዲወድቅ ከማድረጉም በላይ ተፈታኞች ለከፋ እንግልትና ስቃይ እንዲጋለጡ ያደር ጋቸ ዋል ፤ የምዝገባ ሂደቱን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የባለፉት ዓመታትን የምዝገባ ሂደት ችግሮች መፈተሽ፣የማስተከከያ እርምጃዎችን መውሰድ፣የአፈጻጸም ሥርዓት መዘርጋትና በቂና ብቁ ፈጻሚዎችን በማዘጋጀት ወደ ትግበራ መግባት ያስፈልጋል ፡፡

የ ውይይቱ ዓላማና የሚጠበቅ ውጤት ደረጃውን የጠበቀ ፣ ውጤታማና ቀልጣፋ የምዝገባ ስርዓት በ መዘርጋት የተፈታኞችን ህጋዊነት በአግባቡ በመለየትና መረጃቸውን በማጣራት የምዘና ሥርዓቱን ና ሰነድ አያያዝን ውጤታማ ለማድረግ ፤ የምዝገባ አስፈጻሚዎችን የመፈጸም አቅም በማሳደግ በአጭር ጊዜ የተፈታኞችን ምዝገባ ለማካሄድና ጥራት ያለው የ ተፈታኞች መረጃ ለመሰብሰብ ፤ የ አስፈታኝ ትምህርት ቤቶችንና የፈተና ማዕከላትን ጥራት ባለው መረጃ ላይ ተመስርቶ የተሟላ ግብአት ፣ በቂና ብቁ የፈተና አስፈጻሚ በመመደብ አስተማማኝ የሆነ የፈተና አስተዳደር ስርአት እንዲኖር ለማድረግ ፤ የተፈታኞች ምዝገባን በበይነ መረብ (online & offline registration) በውጤታማነት በመፈጸም የተጀመረውን የድብልቅ ፈተና አሰጣጥ ( Haybrid Testing System) በማጠናከር በቀጣይ ፈተናውንም ሙሉ ለሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት (online examination) የሚያስችል መሰረት ለመጣል ነው ፡፡

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም የምክክር መድረከ በ ሦስ ት ዙር በአዳማ ከተማ እዲካሄድ ተደርጓል ፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ በየክልሉና በየዞኑ የሚስተዋሉ የ201 5 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮች ገላጭ በሆነ መልኩ ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል ፡፡ ከ201 5 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ግምገማ በተጨማሪ የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞችን ምዝገባን በበይነ መረብ (online and Offline registration) ለማካሄድ የሚያስችል የአሰልጣኞች ሥልጠና በተግባር እንዲሰጥ ተደርጓል ፡፡ በ ማእከል ስል ጠና ላይ 28 የክልል ፈተና ጉዳይ እና አይሲቲ ክፍል ኃላፊዎች ፣ 2 88 የዞን ፈተና ክፍል እና የአይሲቲ ክፍል ኃላፊዎች እና 41 የአገልግሎቱ ባለሙያዎችና አመራሮች ፣በአጠቃላይ ከነድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ብድምሩ 382 ተሳታፊዎች በምዝገባ የአሰልጣኞች ስልጠና መድረክ ተሳትፈዋል ፡፡ በአጠቃላይ የምዝገባ አስፈጻሚ ሰልጣኝ ቁጥር በየአመቱ እየጨመረ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

የሶ ስት ተከታታይ አመታት የተፈታኞች ምዝገባ አስፈጻሚዎች ብዛት

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም … የ2016 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባን በአግባቡ ለመፈጸምና ለማስፈጸም በማእከል ደረጃ ከተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና በተጨማሪ ሁሉንም አስፈጻሚዎች እስከ ት/ቤት ድረስ ያሉ አስፈጻሚዎችን በዞን ደረጃ አሰልጥኖ ለማሰማራት በየምዝገባ ጣቢያዎች ተሰርቶ በጥቅሉ ለክልሎች ብር 26 ,794,585.54 ማስፈጸሚያ በጀት ተምድቦ ተልኳል። 2016 Registration Budght.xlsx የክትትልና ድጋፍ ሥራን ከማጠናከር አኳያ በአዲሱ አደረጃጀት የስራ አስፈጻሚውን ባለሙያዎች በ6 ምድብ በማደራጀት ክልሎችን ተከፋፍለው ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርጉ የተደረገ ሲሆን የቡድኑ አባላት ከሦስቱም ዴስክ የተውጣጡ እንዲሆኑና በጋራ ሆነው ክትትልና ድግፍ በማድረግ የተፈታኞች ምዝገባና የፈተና አስተዳደር መረጃዎችም በዚሁ አግባብ እንዲሰበሰቡ ተደርጓል ፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነትና የመረጃ ል ውውጥ ለማድረግ የሚያስችል የዋትሰአፕ ቡድን (EAES Exam Administration Stakeholders) በመፍጠር መረጃዎችን ለመለዋወጥና ተከታታይ የሆኑ ግብረ መልሶችን በመስጠት ምዝገባውን በተያዘው ጊዜ ማካሄድ ተችሏል ፤

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም … የካቲት 3/2016 ዓ.ም በበይነ መረብ( online and offline) የተጀመረው የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ ከተወሰኑ የተለየ ችግር ካለባቸው ውስን አካባቢዎች በስተቀር የካቲት 30/2016 ዓ.ም በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ተደርጓል ፤ የምዝገባ አስፈጻሚዎች በተቆራረጠ የኢንተርኔት ግንኙነትና በኦፍ ላይን ጭምር በመመዝገብ ኢንተርኔት ባለበት አካባቢ በመሄድ ወደ ምዝገባ መተግበሪያ በመጫንና በመላክ 100% በትጋት እንዲሳካ ተደርጓል፤ ተፈታኞችም የምዝገባው ወቅት የአንደኛ ወሰነትምህርት ጨርሰው የእረፍት ግዚያቸው ቢሆንም በወቅቱ በመመዝገብ ከፍተኛ ሚና ተጫው ተዋል፣ የተፈታኞች ምዝገባን በበይነ መረብ በኦንላይንና ኦፍላይን ሁለት አማራጭ ተጠቅመን 100% ባቀድነው መሰረት በማሳካት በቀጣይ አመታትም የተጀመረውን የቅይጥ ፈተና አሰጣጥ ስርአት በማጠናከር ፈተናውንም በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል መሰረት ተጥሏል፡፡ በአጠቃላይ የ2016 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ ለማካሄድ በተያዘው እቅድ መሰረት በሁሉም ክልሎች በበይነ መረብ (ኦንላይን እና ኦፍ ላይን) አማራጭን በመጠቀም ምዝገባውን ማተናቀቅ ተችሏል። የምዝገባ አፈጻጸሙም 701,774 መመዝገብ የተቻለ ሲሆን መረጃውን በማጥራትና በየደረጃው የተፈታኞችን ተገቢነት በማረጋገጥ ውድቅ መደረግ ያለበትን ውድቅ በማድረግ ለ701 , 460 ተፈታኞች የፈተና መግቢያ ካርዳቸውን በተመሳሳይ በበይነ መረብ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም …

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮ ች የተመዝጋቢዎችን ተገቢነት አረጋግጦና የምዝገባ ሰነዶችን ቅድመ ምርመራ አካሂዶ ተፈታኞችን መመዝገብ እየተዘነጋና እየቀረ በመምጣቱ ተገቢነት የሌላቸው ተመዝጋቢዎችና ተፈታኞች እየተበራከቱ መምጣት ፣ በተመሳሳይ ህጋዊ ተመዝጋቢዎችን ሳይመዘግቡ በመዝለል በተፈታኞችና ወላጆች ላይ ከፍተኛ እንግልት መፈጠሩ፣ ለ ም ዝ ገባ አስፈጻሚዎች እና ለተመዝጋቢዎች በየደረጃው ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና ፣ ክትትልና ድጋፍ ስራዎች በበቂ ሁኔታ አለመ ተግበሩ ፤ ምዝገባውን በበይነ መረብ ለማካሄድ የሚያስችሉ መሰረታዊ ግብአቶችን ( minimum specification ) ያሟላ በበቂ ሁኔታና በወቅቱ አለማሟላት ፤

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮ ች … ለፈጻሚዎችና አስፈጻሚዎች የሚሰጡ የስልጠናና የምክክር መደረኮችን በየደረጃው በአግባቡ ባለመከታተልና ባለመተግበር የተለያዩ የአሰራር ችግሮችን መፍጠር ፤ በ በይነ መረብ ምዝገባ ወቅት ለ መዝጋቢዎች የሚያስፈልጉ ግብአቶች በ ሚመለከታቸ አስፈጻሚዎች (Administrator's) ተሟልተው አለመቅረብ ፤ የተወሰኑ የምዝገባ ጣቢያዎች በተሰጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ምዝገባ አለ ማጠናቀቅ ወይም ጊዜን በአግባቡ አለመጠቀም፤ የተመዝጋቢዎች ዝርዝር (School List) በሚመለከተው አካል ቀድሞ ተዘጋጅቶና ተረጋግጦ ለመዝጋቢዎች አለመሰጠቱ፤ በምዝገባው ወቅት ትኩረት ባ ለማድረግ የተነሳ ከግዜ ወደ ግዜ መሰረታዊ የተፈታኞች መረጃ ስህተት እየጨመረ መምጣት ( የ ፆታ ፣ የ ፎቶ ፣ የ ስም ፣የእይታ፣የእድሜ ፣ የዜግነት፣የቤተሰብ ዳራ፣ እና የ ትምህር ት ዘርፍ )

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮ ች … ክልል የቤተሰብ ዳራ የእይታ የትምህርት መስክ የጾታ የዜግነት የስም የፎቶ ድምር OROMIA 18,777 4 329 514 625 3,181 455 23,885 SOMALI 18,907   76 25 282 194 65 19,549 AMHARA 15,605 2 113 196 293 1,640 105 17,954 SIDAMA 7,103   42 118 135 780 15 8,193 SOUTH ETHIOPIA 5,187   83 143 229 1,950 25 7,617 CENTRAL ETHIOPIA 3,711 1 53 143 149 1,771 65 5,893 AFAR 5,035   10 7 10 99 2 5,163 GAMBELLA 2,308 1 35 29 1,555 27 3 3,958 TIGRAY 2,833 3 57 131 100 669 15 3,808 SWEP 1,807 1 37 65 82 584 12 2,588 ADDIS ABABA 1,257 2 28 58 329 843 15 2,532 BENSHANGUL GUMZ 623   20 15 523 282 2 1,465 TIGRAY PREPARATORY   1 60 117 46 625 10 859 DRIE DAWA 499   4 3 11 25 2 544 ABROAD         61   - 61 HARAR 12   4   10 11 1 38 Grand Total 83,664 15 951 1,564 4,440 12,681 792 104,107

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮ ች …

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮ ች … መደበኛ ከግል ተፈታኝ ፣የግልተፈታኝ ከመከላከያ ተፈታኝ እንዲሁም የማታ ከግልና ከመደበኛ ጋር ቀላቅሎ መመዝገብ ፤ አገልግሎቱ ከተመዝጋቢዎች ( ከግልና እና ከማታ ተመዝጋቢዎች ) የሚሰበስባቸው የምዝገባ ማስፈጸሚያ ክፍያዎች በአግባቡ እየተሰበሰቡና ክትትል እየተደረገባቸው አለመሆኑ ፣ የፎቶ ጥራት ችግርን ለመቅረፍ ትምህርት ቤቶች በተዘጋጀው የእቃ ዝርዝር መግለጫ መሰረት ገዝተው አለመጠቀም፣ ተፈታኞች በበይነ መረብ ሲመዘ ገቡ ና ፎቶ ሲነሱ ተገቢ የሆነ የፎቶ ዳራ (background) አለመጠቀም ፤ ሁለት ተፈታኞች በአንድ ላይ መነሳት፣መቆረጥ፣መቀያየር ፣ተቃቅፎ መነሳት ወዘተ .. ችግሮች ይስተዋላሉ ፡፡

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮ ች … የአስፈታኝ ትምህርት ቤቶችን መረጃ በወቅቱና በሚፈለገው ፎርማት ያለማቅረብ ፣ ለአስምዝጋቢ ትምህርት ቤቶች በወቅቱ መዝጋቢ (user) አለመሰየምና ፈጥነው ወደ ስራ እንዲገቡ አለማድረግ ፣ የመብራትና የኢንተርኔት ግንኙነት በተደጋጋሚ መቆራረጥ ፣ የ ተፈታኞችን ዝርዝር ( School List) ከምዝገባ በፊት ቀድሞ በወቅቱና በሚፈለገው ፎርማት አዘጋጅቶ እና አረጋግጦ ለመዝጋቢዎች አለመስጠትና ክትትል አለማድረግ፣ ከምዝገባ ቡኋላ ተመዝጋቢዎች የምዝገባ መረጃዎቻቸውን እንድያረጋግጡና እንዲፈርሙ አለመደረጉ፤

የተወሰዱ መፍትሔዎች ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ምዝገባውን ያልጨረሱ የምዝገባ ፕሮግራሙን በማ ራዘም ሁሉም ተፈታኞች በወቅቱ እንዲመዘገቡ ጥረት ተደርጓል ፤ ከማዕከል እስከ ክልልና ዞን ድ ረስ በስልክ ፣ በኢሜልና በማህበራዊ ሚዲያ ፈጣን የመረጃ ልውውጥ በማድረግ የ ሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት ተደርጓል ፤ በሚፈለገው ፎርማትና አግባብ ያልመጡ የተፈታኞች ዝርዝር( School List) ተመላሽ በማድረግ በድጋሚ ተስተካክለው እንዲመጡ ተደርጓል ፤ በምዝገባ ወቅትና ምዝገባ ከተጠናቀቀ ቡኋላም ለአስፈጻሚዎች ተደጋጋሚ ግብረ መልስ በመስጠት ስህተቶች እንዲስተካከሉ ተደርጓል፣ በ ምዝገባ አስፈጻሚዎች፣ መዝጋቢዎችና ተመዝጋቢዎችም ጭምር በሰሩት ስህተት የተማሪዎች ዶክመንት ተበላሽቶ እንዳይቀር መመሪያው በሚፈቅደው ልክ ተደጋጋሚ የተፈታኞች መሰረታዊ መረጃ ማስተካከያ እንዲሰራ ተደርጓል፣

የተወሰዱ መፍትሔዎች

ማጠቃለያና የቀጣይ አቅጣጫዎች በአጠቃላይ የ2016 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ ከባለፉት አመታት አኳያ ሲታይ በተለይ የኦንላይንና ኦፍላይን አማራጮችን የያዘ ስለነበር በተወሰነ መልኩ የአስፈጻሚዎችንና ተሳታፊዎችን ጭንቀትና እንግልት የቀነሰ ነበር፣ ለአሰልጣኞች ስልጠና የመጣው ተሳታፊ ለመዝጋቢዎች ተገቢውን ሥልጠና በዞን ደረጃ ለ መስጠት ፣ለመከታተል፣ ለመደገፍና እና በወጣው መርሃ ግብር መሰረት በበይነ መረብ እና ያለበይነ መረብ በተሻሻለው መተግበሪያ ( Eduportal ) እንዲካሄድ ለማድረግ የሶስት ቀን ቆይታችንን በአግባቡ መጠቀምና በቂ የሆነ እውቀትና አቅጣጫ መያዝ ፤ መዝጋቢዎች ቀድሞ የተዘጋጀና በሚመለከተው የተረጋገጠ የተፈታኞች ዝርዝር( School List) ሳይረከቡና ሳይዙ ምዝገባ እንዳይካሄድ ማድረግና ለሚፈጠሩ ስህተቶች በየደረጃው የአስፈጻሚዎችን የተጠያቂነት ስርአት መዘርጋት ፤

አመሰግናለሁ !
Tags