የ 2017 ዓ.ም የምዝገባ አስፈጻሚዎች ማሰልጠኛ ሰነድ (በዞን ደረጃ ለሚሰጥ ሥልጠና).pptx

sami774951 0 views 47 slides Oct 09, 2025
Slide 1
Slide 1 of 47
Slide 1
1
Slide 2
2
Slide 3
3
Slide 4
4
Slide 5
5
Slide 6
6
Slide 7
7
Slide 8
8
Slide 9
9
Slide 10
10
Slide 11
11
Slide 12
12
Slide 13
13
Slide 14
14
Slide 15
15
Slide 16
16
Slide 17
17
Slide 18
18
Slide 19
19
Slide 20
20
Slide 21
21
Slide 22
22
Slide 23
23
Slide 24
24
Slide 25
25
Slide 26
26
Slide 27
27
Slide 28
28
Slide 29
29
Slide 30
30
Slide 31
31
Slide 32
32
Slide 33
33
Slide 34
34
Slide 35
35
Slide 36
36
Slide 37
37
Slide 38
38
Slide 39
39
Slide 40
40
Slide 41
41
Slide 42
42
Slide 43
43
Slide 44
44
Slide 45
45
Slide 46
46
Slide 47
47

About This Presentation

Only


Slide Content

የ2016 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም አቅጣጫዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ! ህዳር /201 7 ዓ.ም

የሥልጠናው ይዘት መግቢያ የሥልጠናው ዓላማና የሚጠበቅ ውጤት የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ፣ በምዝገባ አፈጻጸም ያጋጠሙ ችግሮ ች የምዝገባ አፈጻጸም ማንዋል እና የምዝገባ አስፈጻሚዎች ሚና ማጠቃለያና የ ቀጣይ አቅጣጫዎች

ክፍል - አንድ የ2016 ዓ.ም የምዝገባ አፈጻጸም ችግሮች

መግቢያ የተፈታኞች ምዝገባ ለትምህርት ጥራትና ግብአት መሟለት ሂደት መሰረታዊ መረጃዎች የሚሰበሰብበት ወሳኝ ሂደት በመሆኑ በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ ሊፈጸም የሚገባ ተግባር ነው ፤ ምዝገባ ተፈታኞች ለትምህርት ደረጃው የተዘጋጀውን ሥርአተ ትምህርት በተቀመጠው የትምህርት አሰጣጥ መርሃ ግብር መሰረት ተምረው ሲያጠናቅቁና ራሳቸውን ለፈተና ዝግጁ መሆናቸውን ሲያረጋግጡ ፈተናውን ለመውሰድ በተዘጋጀው የፈተና አሰጣጥ መርሃ ግብር ና አይነት (intended exam schedule and Modality) መሰረት ለመውሰድ የሚመዘገቡበት ሂደት ነው ፤ በምዝገባ ሂደት የምዝገባ አስፈጻሚዎች ለምዝገባ የሚያስፈልገውን የምዝገባ ማስፈጸሚያ ግብአትና የተሟላ ግንዛቤ ጨብጠው ወደ ሂደቱ መግባት ካልቻሉ የተፈለገውን የተፈታኝ መረጃ ማግኘት ስለማይቻል ቀጣዩ የፈተና አሰጣጥ ሂደት ችግር ውስጥ እንዲወድቅ ከማድረጉም በላይ ተፈታኞች ለከፋ እንግልትና ስቃይ እንዲጋለጡ ያደር ጋቸ ዋል ፤ የምዝገባ ሂደቱን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የባለፉት ዓመታትን የምዝገባ ሂደት ችግሮች መፈተሽ፣የማስተከከያ እርምጃዎችን መውሰድ፣የአፈጻጸም ሥርዓት መዘርጋትና በቂና ብቁ ፈጻሚዎችን በማዘጋጀት ወደ ትግበራ መግባት ያስፈልጋል ፡፡

የ ውይይቱ ዓላማና የሚጠበቅ ውጤት ደረጃውን የጠበቀ ፣ ውጤታማና ቀልጣፋ የምዝገባ ስርዓት በ መዘርጋት የተፈታኞችን ህጋዊነት በአግባቡ በመለየትና መረጃቸውን በማጣራት የምዘና ሥርዓቱን ና ሰነድ አያያዝን ውጤታማ ለማድረግ ፤ የምዝገባ አስፈጻሚዎችን የመፈጸም አቅም በማሳደግ በአጭር ጊዜ የተፈታኞችን ምዝገባ ለማካሄድና ጥራት ያለው የ ተፈታኞች መረጃ ለመሰብሰብ ፤ የ አስፈታኝ ትምህርት ቤቶችንና የፈተና ማዕከላትን ጥራት ባለው መረጃ ላይ ተመስርቶ የተሟላ ግብአት ፣ በቂና ብቁ የፈተና አስፈጻሚ በመመደብ አስተማማኝ የሆነ የፈተና አስተዳደር ስርአት እንዲኖር ለማድረግ ፤ የተፈታኞች ምዝገባን በበይነ መረብ (online & offline registration) በውጤታማነት በመፈጸም የተጀመረውን የድብልቅ ፈተና አሰጣጥ ( Hybrid Testing System) በማጠናከር በቀጣይ ፈተናውንም ሙሉ ለሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት (online examination) የሚያስችል መሰረት ለመጣል ነው ፡፡

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ግምገማ እና ስልጠና በዞን ደረጃ እዲካሄድ ተደርጓል ፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ በየዞኑ የሚስተዋሉ የ201 5 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮች ገላጭ በሆነ መልኩ ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል ፡፡ ከ201 5 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ግምገማ በተጨማሪ የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞችን ምዝገባን በበይነ መረብ (online and Offline registration) ለማካሄድ የሚያስችል የአሰልጣኞች ሥልጠና በተግባር እንዲሰጥ ተደርጓል ፡፡ በዞን ደረጃ በተሰጠው ስልጠና ላይ የት / ቤት ርእሳና መምህራን ፣ መዝጋቢዎች ፣ የወረዳ ፈተና ጉዳይ እና አይሲቲ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ፡፡ የምዝገባ አስፈጻሚ ሰልጣኝ ቁጥር በ ሀገር አቀፍ ደረጃ በየ አመቱ እየጨመረ መሆኑን እንደሚከተለው መረዳት ይቻላል።

የሶ ስት ተከታታይ አመታት የተፈታኞች ምዝገባ አስፈጻሚዎች ብዛት

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም … የካቲት 3/2016 ዓ.ም በበይነ መረብ( online and offline) የተጀመረው የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ ከተወሰኑ የተለየ ችግር ካለባቸው ውስን አካባቢዎች በስተቀር የካቲት 30/2016 ዓ.ም በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ተደርጓል ፤ የምዝገባ አስፈጻሚዎች በተቆራረጠ የኢንተርኔት ግንኙነትና በኦፍ ላይን ጭምር በመመዝገብ ኢንተርኔት ባለበት አካባቢ በመሄድ ወደ ምዝገባ መተግበሪያ በመጫንና በመላክ 100% በትጋት እንዲሳካ ተደርጓል፤ ተፈታኞችም የምዝገባው ወቅት የአንደኛ ወሰነትምህርት ጨርሰው የእረፍት ግዚያቸው ቢሆንም በወቅቱ በመመዝገብ ከፍተኛ ሚና ተጫው ተዋል፣ የተፈታኞች ምዝገባን በበይነ መረብ በኦንላይንና ኦፍላይን ሁለት አማራጭ ተጠቅመን 100% ባቀድነው መሰረት በማሳካት በቀጣይ አመታትም የተጀመረውን የቅይጥ ፈተና አሰጣጥ ስርአት በማጠናከር ፈተናውንም በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል መሰረት ተጥሏል፡፡ በአጠቃላይ የ2016 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ ለማካሄድ በተያዘው እቅድ መሰረት በሁሉም ክልሎች በበይነ መረብ (ኦንላይን እና ኦፍ ላይን) አማራጭን በመጠቀም ምዝገባውን በወቅቱ ማ ጠ ናቀቅ ተችሏል። የምዝገባ አፈጻጸሙም 701,774 መመዝገብ የተቻለ ሲሆን መረጃውን በማጥራትና በየደረጃው የተፈታኞችን ተገቢነት በማረጋገጥ ውድቅ መደረግ ያለበትን ውድቅ በማድረግ ለ701 , 460 ተፈታኞች የፈተና መግቢያ ካርዳቸውን በተመሳሳይ በበይነ መረብ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮ ች የተመዝጋቢዎችን ተገቢነት አረጋግጦና የምዝገባ ሰነዶችን ቅድመ ምርመራ አካሂዶ ተፈታኞችን መመዝገብ እየተዘነጋና እየቀረ በመምጣቱ ተገቢነት የሌላቸው ተመዝጋቢዎችና ተፈታኞች እየተበራከቱ መምጣት ፣ በተመሳሳይ ህጋዊ ተመዝጋቢዎችን ሳይመዘግቡ በመዝለል በተፈታኞችና ወላጆች ላይ ከፍተኛ እንግልት መፈጠሩ፣ ለ ም ዝ ገባ አስፈጻሚዎች እና ለተመዝጋቢዎች በየደረጃው ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና ፣ ክትትልና ድጋፍ ስራዎች በበቂ ሁኔታ አለመ ተግበሩ ፤ ምዝገባውን በበይነ መረብ ለማካሄድ የሚያስችሉ መሰረታዊ ግብአቶችን ( minimum specification ) በበቂ ሁኔታና በወቅቱ አለማሟላት ፤ Operating system , Web browser, Web camera; Internet connection Power supply

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮ ች … ለፈጻሚዎችና አስፈጻሚዎች የሚሰጡ የስልጠናና የምክክር መደረኮችን በየደረጃው በአግባቡ ባለመከታተልና ባለመተግበር የተለያዩ የአሰራር ችግሮችን መፍጠር ፤ በ በይነ መረብ ምዝገባ ወቅት ለ መዝጋቢዎች የሚያስፈልጉ ግብአቶች በ ሚመለከታቸ አስፈጻሚዎች (Administrator's) ተሟልተው አለመቅረብ ፤ የተወሰኑ የምዝገባ ጣቢያዎች በተሰጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ምዝገባ አለ ማጠናቀቅ ወይም ጊዜን በአግባቡ አለመጠቀም፤ የተመዝጋቢዎች ዝርዝር (School List) በሚመለከተው አካል ቀድሞ ተዘጋጅቶና ተረጋግጦ ለመዝጋቢዎች አለመሰጠቱ፤ በምዝገባው ወቅት ትኩረት ባ ለማድረግ የተነሳ ከግዜ ወደ ግዜ መሰረታዊ የተፈታኞች መረጃ ስህተት እየጨመረ መምጣት ( የ ፆታ ፣ የ ፎቶ፣የ ስም ፣የእይታ፣የእድሜ ፣የዜግነት፣የቤተሰብ ዳራ፣ እና የ ትምህር ት ዘርፍ )

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮ ች … ክልል የቤተሰብ ዳራ (Pastoral/Not Pastoral) የእይታ ( Blind/Not Blind) የትምህርት መስክ ( Natural/Social) የጾታ ( Male/Female ) የዜግነት የስም የፎቶ ድምር (Ethiopian/Non Ethiopia) OROMIA 18,777 4 329 514 625 3,181 455 23,885 SOMALI 18,907   76 25 282 194 65 19,549 AMHARA 15,605 2 113 196 293 1,640 105 17,954 SIDAMA 7,103   42 118 135 780 15 8,193 SOUTH ETHIOPIA 5,187   83 143 229 1,950 25 7,617 CENTRAL ETHIOPIA 3,711 1 53 143 149 1,771 65 5,893 AFAR 5,035   10 7 10 99 2 5,163 GAMBELLA 2,308 1 35 29 1,555 27 3 4,617 TIGRAY 2,833 4 117 248 146 1294 25 4,667 SWEP 1,807 1 37 65 82 584 12 2,588 ADDIS ABABA 1,257 2 28 58 329 843 15 2,532 BENSHANGUL GUMZ 623   20 15 523 282 2 1,465 DRIE DAWA 499   4 3 11 25 2 544 ABROAD         61   - 61 HARAR 12   4   10 11 1 38 Grand Total 83,664 15 951 1,564 4,440 12,681 792 104,107

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮ ች … መደበኛ ከግል ተፈታኝ ፣የግልተፈታኝ ከመከላከያ ተፈታኝ እንዲሁም የማታ ከግልና ከመደበኛ ጋር ቀላቅሎ መመዝገብ ፤ አገልግሎቱ ከተመዝጋቢዎች ( ከርቀት ፣ ከግልና እና ከማታ ተመዝጋቢዎች ) የሚሰበስባቸው የምዝገባ ማስፈጸሚያ ክፍያዎች በአግባቡ እየተሰበሰቡና ክትትል እየተደረገባቸው አለመሆኑ ፣ የፎቶ ጥራት ችግርን ለመቅረፍ ትምህርት ቤቶች በተዘጋጀው የእቃ ዝርዝር መግለጫ መሰረት ዌብ ካሜራ ገዝተው አለመጠቀም፣ ተፈታኞች በበይነ መረብ ሲመዘ ገቡ ና ፎቶ ሲነሱ ተገቢ የሆነ የፎቶ ዳራ (background) አለመጠቀም ፤ ሁለት ተፈታኞች በአንድ ላይ መነሳት፣መቆረጥ፣መቀያየር ፣ተቃቅፎ መነሳት ወዘተ .. ችግሮች ይስተዋላሉ ፡፡

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ የፎቶ ግራፍ ችግሮ ች …

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ የፎቶ ግራፍ ችግሮ ች …

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ የፎቶ ግራፍ ችግሮ ች …

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ የፎቶ ግራፍ ችግሮ ች …

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ የፎቶ ግራፍ ችግሮ ች …

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ የፎቶ ግራፍ ችግሮ ች …

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ የፎቶ ግራፍ ችግሮ ች …

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ የፎቶ ግራፍ ችግሮ ች …

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ የዕድሜ ችግሮ ች …

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ የዕድሜ ችግሮ ች …

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ የዕድሜ ችግሮ ች …

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮ ች … የአስፈታኝ ትምህርት ቤቶችን መረጃ በወቅቱና በሚፈለገው ፎርማት ያለማቅረብ እና በመተግበሪያው ላይ እንዲጫን አለማድረግ ፣ ለአስምዝጋቢ ትምህርት ቤቶች በወቅቱ መዝጋቢ (user) አለመሰየምና ፈጥነው ወደ ስራ እንዲገቡ አለማድረግ ፣ የመብራትና የኢንተርኔት ግንኙነት በተደጋጋሚ መቆራረጥ ፣ የ ተፈታኞችን ዝርዝር ( School List) ከምዝገባ በፊት ቀድሞ በወቅቱና በሚፈለገው ፎርማት አዘጋጅቶ እና አረጋግጦ ለመዝጋቢዎች አለመስጠትና ክትትል አለማድረግ ፣ ከምዝገባ በኃላ ተፈታኞች የምዝገባ መረጃቸውን የሚያረጋግጡበት እና የሚፈርሙበት አሰራር አለመኖር ፤

የ201 6 ዓ.ም የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም ችግሮ ች … የ2016 ዓ.ም የፈተና አስተዳደር ቁልፍ ተግዳሮቶች - የዕቅዱ መነሻዎች በምዝገባ አፈጻጸም ማንዋሉ መሰረት ብቃት እና ከፍተኛ ተነሳሽነት ያላቸውን የምዝገባ አስፈጻሚዎች በወቅቱ መልምሎ፣በቂ ስልጠና ሰጥቶ እና አፈጻጸማቸውን እየተከታተሉ አለመምራት ፤ በምዝገባ አፈጻጸም ማንዋሉ መሰረት ተፈታኞችን አዘጋጅቶ ምዝገባውን በጥራት እና በብቃት ማካሄድ አለመቻል ፤ የተፈታኞች የምዝገባ መረጃ መሳሳት ፣ መለዋወጥ እና በተቀመጠው ጊዜ መፈጸም አለመቻል ፤ ለምዝገባ እና ለፈተና አሰጣጥ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን እና መሰረተ ልማቶችን በሚፈለገው ጥራት እና ጊዜ ማሟላት አለመቻል ፤ ተፈታኞች የሚጠበቅባቸውን መሰፈርት አሟልተው እንዲመዘገቡ አለማድረግ ፤ ሳያሟሉ የተመዘገቡ ተፈታኞችን በምዝገባ ሰነድ ማጣራት ሂደት በአግባቡ ለይቶ ውድቅ አለማድረግ ፤ የአስመዝጋቢ ትምህርት ቤቶችን አደረጃጀት እና አሰራር ተከትሎ ምዝገባ አለማካሄድ እና የተለያዩ ፕሮግራሞችን ቀላቅሎ መመዝገብ ፤ የምዝገባ አስፈጻሚዎችን ክፍያ በተቀመጠው አግባብ እና በወቅቱ መክፈል አለመቻል፤በተለይም የስልጠና ቆይታ ክፍያዎች፣የሂሳብ ሪፖርቶች በወቅቱ በማቅረብ ማወራረድ አለመቻል ፤

ክፍል ሁለት ፡- የተፈታኞች ምዝገባ ማስፈጸሚያ ማንዋል እና የአስፈጻሚዎች ሚና

በአፈጻጸም ማንዋሉ መሰረት ተመዝጋቢዎችን ማዘጋጀት ለተፈታኞች ግልጽ የሆነ ገለጻ በመስጠት በምዝገባ ሂደት ያለቸውን መብት እና ግዴታ በአግባቡ እንዲገነዘቡ ማድረግ ፡- በፈተና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1/2015 በአንቀጽ 11 ከ ንዑስ አንቀጽ 1 እስከ 13 የተመለከቱትን መስፈርቶች አሟልተው የሚቀርቡ አመልካቾች ለፈተናው የመመዝገብ መብት አላቸው ፤ ተመዝጋቢዎች በተቀመጠው ጊዜ ገደብ መሰረት ማናቸውንም ከምዝገባ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስህተቶች ከተፈጠሩ የምዝገባ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት በተመዘገቡበት ጣቢያ ማስተካከያ እንዲደረግላቸው የማስደረግ መብት አላቸው ፤ የግል ፣ የርቀት ፣ የበይነመረብ መስመር የመከላከያ ሰራዊት አባላት ትምህርት ተከታታይ አመልካቾች በአካል በመቅረብ ለመመዝግቢያ እና ለየትምህርት ዓይነቱ የሚከፈለውን የምዝገባ ማስፈጸሚያ ክፍያ እንዲሁም አስፈላጊ የትምህርት ማስረጃዎችን በማሟላት መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን የሚያቀርቧ ቸ ው የትምህርት ማስረጃዎች ዋና ወይም ቅጅ ያልሆኑ መሆን አለባቸው ፤

በአፈጻጸም ማንዋሉ መሰረት ተመዝጋቢዎችን ማዘጋጀት … የትኩረት መስኮች - በአፈጻጸም ማንዋሉ መሰረት ተመዝጋቢዎችን ማዘጋጀት … ለተፈታኞች ግልጽ የሆነ ገለጻ በመስጠት በምዝገባ ሂደት ያለቸውን መብት እና ግዴታ በአግባቡ እንዲገነዘቡ ማድረግ … ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ሲቀርቡማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ እና አካላዊ ገጽታቸውን በትክክል ለመለየት የሚያችል አለባበስ መልበስ አለባቸው ፤ የስም ለውጥ ለማድረግ የሚፈልጉ ተመዝጋቢዎች ከምዝገባ በፊት በህግ ያስቀየሩበትን የፍርድ ቤት ውሳኔ በማቅረብ በተቀየረው ስማቸው መመዝገብ ይኖርባቸዋል ፤ ምዝገባ ከተፈፀመ በኋላ የሚቀርቡ ማንኛውም አይነት መሰረታዊ የስም ለውጥ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም ፣ ሆኖም በስም ላይ መሰረታዊ ለውጥ የማያመጡ የፊደላት ግድፈቶች እና በመዝጋቢ ስህተት የተፈጠሩ ችግሮች በአስመዝጋቢ ት/ ቤቱ በሚቀርብ ደጋፊ ማስረጃ በሚሰጠው የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ውስጥ ብቻ መስተካከል ይችላሉ ፤ ተመዝጋቢዎች ለፈተና የሚቀመጡት የፈተና መግቢያ ካርዳቸውን ከአገልግሎቱ የበይነ መረብ ገጸ ድር ላይ በት / ቤቱ በኩል ታትሞላቸው በመያዝ ብቻ ይሆናል ፡፡

በአፈጻጸም ማንዋሉ መሰረት ትምህርት ቤቶች ኃላፊነታቸውን እና ተግባራቸው እንዲወጡ ማድረግ የትምህርት ቤቱን የተፈታኞች መረጃ ወይም ሮስተር (S student list) በማደራጀት ለወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ይልካል፤ ለሰጠው የተማሪ ዝርዝር ወይም ህጋዊ የተፈታኝነት ማስረጃ ኃላፊነቱን ይወስዳል አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤ በተፈታኞች ምዝገባ ከሚሳተፉ መዝጋቢዎች ጋር ስልጠና ይወስዳል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤ በትምርት ቤት ደረጃ የምዝገባ ግብዓት እና መሰረተ ልማቶች መሟላታቸውን ያረጋግጣል፤ የትምህርት ቤቱን የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ምዝገባ በአግባቡ እንዲካሄድ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፤ ለተፈታኞች ስለምዝገባው አጠቃላይ ሂደት ከመዝጋቢዎች ጋር በመሆን ገለፃ ይሰጣል፣ ሁሉም የትምህርት ቤቱ ተመዝጋቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ብቁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤ የተፈታኞችን ዝርዝር በተመዝጋቢ አይነት መደበኛ እና የማታ ለይቶና አረጋግጦ ለመዝጋቢው ያቀርባል ፤ እንደተመዝጋቢው ብዛትና እንደ ምዝገባ መርሃ ግብሩ ሁኔት በቀን ምን ያህል ተመዝጋቢ መመዝገብ እንዳለበት ለይቶ በማደራጀት ተመዝጋቢዎች ዝግጁ እንዲሆኑ ያደርጋል ፤

በአፈጻጸም ማንዋሉ መሰረት ትምህርት ቤቶች ኃላፊነታቸውን እና ተግባራቸው እንዲወጡ ማድረግ … የተመዝጋቢዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ከመዝጋቢው ቅጂ ወስዶ በማስታወቂያ ቦርድ ላይ በመለጠፍ ተመዝጋቢዎች እንዲያረጋግጡ ያደርጋል ፤ ምዝገባው ሲጠናቀቅ በተሰጠው ሮስተር መሰረት ምዝገባው ስለመከናወኑ ትክክለኛነቱን ከመዝጋቢው ጋር ማረጋገጫ በመፈራረም ፤ የተመዝጋቢዎችን ዝርዝር መረጃ በሚገባ አደራጅቶና አረጋግጦ ለአገልግሎቱ እንዲደረስ ለሚመለከተው ክፍል ያስረክባል ፤ የመደበኛ ተፈታኞችን አጠቃላይ መረጃ ለሚመለከተው አካል በህጋዊ ደብዳቤ እና በወቅቱ በሚፈለገው መረጃ የማስተላለፊያ መንገድ በተዋረድ ያቀርባል ፤ የትምህርት ቤቱን የዘመኑን ተፈታኞች ግለ ታሪክ በሚፈለገው የጥራት ደረጃ አጠናቅሮ ይይዛል ፤ የተመዝጋቢዎችን ሰነድ በአግባቡ እንዲያዝ ያደርጋል፤

በአፈጻጸም ማንዋሉ መሰረት ትምህርት ቤቶች ኃላፊነታቸውን እና ተግባራቸው እንዲወጡ ማድረግ … በትምርት ቤት የሚመዘገቡ ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ብቁ ሆነው እንዲመዘገቡ መረጃዎችን ያቀርባል፣ ሁኔታዎችን ያመቻቻል ፣ ይከታተላል፣ የምዝገባ ሰነዶችንና ሪፖርቶችን አሰባስቦና አደራጅቶ ለወረዳ ትምርት ጽህፈት ቤት ያስረክባል፣ ፈተና ላይ ለመቀመጥ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎችን ከሚመለከተው ጋር በመሆን ለተመዝጋቢዎች ተደራሽ ያደርጋል፣ ከምዝገባ በኃላ ለተፈታኞች በአገልግሎቱ የመለያ ቁጥር ተሰጥቶ የተፈታኞች የተመዝጋቢነት ማረጋገጫ እና የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ በበይነ መረብ ሲለቀቅ ከመዝጋቢው ጋር በመሆን ካርዳቸው ታትሞ እና የት/ቤቱን ማህተም ተደርጎበት እንዲደርሳቸው ያደርጋል፤ ከምዝገባ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ ቅሬታዎችን እና አቤቱታዎችን አደራጅቶ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ በተሰጠው ጊዜ ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ ይኖርበታል፤

በአፈጻጸም ማንዋሉ መሰረት መዝጋቢዎች ኃላፊነታቸውን እና ተግባራቸውን እንዲወጡ ማድረግ ለምዝገባ የተመቻቸለትን የምዝገባ ቦታ ዝግጁ በማድረግና ለተመዝጋቢዎች የምዝገባውን ሂደት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ገለጻ በመስጠት ምዝገባ ማካሄድ ፤ በበይነ መረብ የተመዘገቡትን ተመዝጋቢዎች ሙሉ ዝርዝር መረጃ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲለጠፍ እና ተመዝጋቢዎች ትክክለኛነቱን እንዲያረጋግጡ ከርዕሰ መምህሩ ጋር ማመቻቸት ፤ የትምህርት ቤቱ ተመዝጋቢዎች ሙሉ በሙሉ መመዝገባቸውን ከርዕሰ መምህሩ ጋር በመሆን ማረጋገጥ ፤ መዝጋቢው ሲስተም ውስጥ ባሉት ትምህርት ቤቶች እና በተሰጠው የተመዝጋቢዎች ዝርዝር እንዲሁም በተፈጠረለት የምዝገባ መለያ ስም እና የይለፍ ቃል ብቻ ተጠቅሞ ይመዝግባል ፤ ምዝገባው እንደተጠናቀቀ የምዝገባ ቀሪ ቀናትን ሳይጠብቅ በበይነ መረብ የተመዘገቡትን ተመዝጋቢዎች የምዝገባ ሰነድ አጣርቶና አረጋግጦ ለትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በመፈራረም ያስረክባል ፤

በአፈጻጸም ማንዋሉ መሰረት የወረዳ ትምህርት ጽ/ ቤቶች ኃላፊነት እና ተግባራቸውን እንዲወጡ ማድረግ በትምህርት ዘመኑ ነባር እና አዲስ ፈተና የሚያስፈትኑ ትምህርት ቤቶችን እና አጠቃላይ ቅድመ ፈተና መረጃ እንዲሁም የተፈታኞችን መረጃ ለዞን ትምህርት መምሪያ ያሳውቃል ፣ ከመረጃው ጋር ተያይዞ የሚዘጋጁ ሰነዶችን ትክክለኛነት ያረጋግጣል ፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤ በ ትምህርት ቤት እና በወረዳ ደረጃ ለምዝገባ አስፈላጊ የሆኑ የምዝገባ ግብዓቶች እና መሰረተ ልማቶች ስለመሟላታቸው ክትትል በማድረግ ለዞን ወይም ለከተማ አስተዳደሩ ያሳውቃል፤ የ ተፈታኞች ምዝገባ ላይ የሚሳተፉ መዝጋቢዎች እንዲመለመሉ በማድረግ ስም ዝርዝራቸውን ለሚመለከተው ይልካል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤ በ ተፈታኞች ምዝገባ የሚሳተፉ የምዝገባ አስፈጻሚዎች መዝጋቢዎች ስልጠናውን በአግባቡ እንዲወስዱ ያደርጋል ፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤ ም ዝገባ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ ለተመዝጋቢዎች ስለ ምዝገባው እና ስለ አፈጻጸም መርሃ ግብሩ ተገቢውን መረጃ እና ገለጻ እንዲሰጣቸው ያደርጋል ፤

በአፈጻጸም ማንዋሉ መሰረት የወረዳ ትምህርት ጽ/ ቤቶች ኃላፊነት እና ተግባራቸውን እንዲወጡ ማድረግ … በ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት የሚመዘገቡ የግል ፣ የማታ ፣ የርቀትና የበይነ መረብ መስመር ትምህርት ተከታታይ ተፈታኞች ለምዝገባ ብቁ በሚያደርጉ መስፈርቶች መሰረት እንዲመዘገቡ ሁኔታዎችን ያመቻቻል ፣ ይከታተላል፣ ተ መዝጋቢዎች ለምዝገባ ሲያመለክቱ ለምዝገባ ብቁ የሆኑትን በመለየት የወረዳው የፈተና ክፍል ኃላፊ ወይም ባለሙያ አማካኝነት ለመዝጋቢው ማረጋገጫ እንዲሰጥ ያደርጋል ፤ የ ተመዝጋቢዎችን ዶክመንት አጣርቶ ለዞን ምርመራ ቡድን እንዲቀርብ ያደርጋል ፤ ስለትክክለኛነቱም ኃላፊነት ይወስዳል የ ምዝገባ ሰነዶችንና ሪፖርቶችን አሰባስቦና አደራጅቶ ለዞን ያስረክባል እንዲሁም ከትምህርት ማስረጃ ምርመራ በኃላ ዋና ( ቅጅ ያልሆነ ) ዶክመንቶችን ለተመዝጋቢዎች ይመልሳል ፤ የምዝገባ ሂደቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ እንዲሰራ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል ፤ ከምዝገባ በኃላ ለተፈታኞች በአገልግሎቱ የመለያ ቁጥር ተሰጥቶ የተፈታኞች የተመዝጋቢነት ማረጋገጫ እና የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ በበይነ መረብ ሲለቀቅ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ካርዳቸው ታትሞ እንዲደርሳቸው ያደርጋል ፤ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን እና አቤቱታዎችን አደራጅቶ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ በተሰጠው ጊዜ ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ ይኖርበታል ፤

በአፈጻጸም ማንዋሉ መሰረት የምዝገባ ሰነድ መርማሪዎችን ኃላፊነታቸው እና ተግባራቸውን እንዲወጡ ማድረግ የድጋሚ እና የርቀት ተመዝጋቢዎችን ዝርዝር ማስረጃ ከወረዳ ትምህርት ጽ/ ቤት ይረከባል ፤ በመመሪያውና በማንዋሉ መሰረት የትምህርት ማስረጃዎችን በመመርመርና በማጣራት የተጣራውን የተመዝጋቢዎች ዶክመንት በማረጋገጥ ተቀባይነት ያገኙትን ለዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ያቀርባል ፤ በትምህርት ማስረጃ ማጣራት ወቅት ውድቅ የተደረገባቸው ተመዝጋቢዎች ተቀባይነት ያላገኙበትን ምክንያት በመግለጽ በወረዳ ትምህርት ጽ/ ቤት ፈተና ክፍል ኃላፊ አማካኝነት ተመዝጋቢዎች እንዲያውቁ ያደርጋል ፤ ማወቃቸውንም ያረጋግጣል ለትምህርት ማስረጃ ምርመራ የተሰበሰበው ዋና የትምህርት ማስረጃ በአግባቡ በመያዝ ለወረዳ ት/ጽ/ ቤት በጥንቃቄ ያስረክባል ፤ የወረዳ ትምህርት /ጽ/ ቤትም ለተመዝጋቢዎቹ ይመልሳል ፤ በተጭበረበረ ወይም ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተመዘገቡ ተፈታኞችን መረጃ ለይቶ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል ፤ ክትትል ያደርጋል፤ላረጋገጠውም የትምህርት ማስረጃ ሀላፊነቱን ይወስዳል፡፡

ተመዝጋቢዎች በወጣው ፕሮግራም እና ቦታ እንዲመዘገቡ ማድረግ የትምህርት ዘመኑ የተፈታኞች ምዝገባ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት ከታህሳስ 7 አስከ ጥር 6/2017 ዓ.ም ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተካሂዶ እንዲጠናቀቅ ይደረጋል ፤ የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ምዝገባ በሚማሩበት ትምህርት ቤት እንዲካሄድ ይደረጋል ፤ የግል ፣ የርቀት ፣ የበይነ መረብ መስመር ፕሮግራም ተፈታኞች ምዝገባ በክፍለ ከተማ ፤ በልዩ ወረዳ እና በወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች ይካሄዳል ፡፡

ተመዝጋቢዎች የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው እንዲመዘገቡ ማድረግ የመንግስት መደበኛ ተማሪዎች 8ኛ ክፍል ተፈትነው ያለፉ ፤ ከ 9 ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ተከታታይ አመት “ ትራንስክርፕት ” ማቅረብ የሚችሉ እና 12ኛ ክፍል በመደበኛው ፕሮግራም በመማር ላይ ያሉ መሆን አለባችው ፤ ለዚህም የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ለመዝጋቢው አረጋግጦ መስጠት አለበት ፤ የግል ትምህርት ቤት መደበኛ ተፈታኞችን እንደ መንግስት መደበኛ ትምህርት ቤት ተፈታኞች መረጃቸው በት / ቤቱ ርእሰ መምህር አማካኝነት ተጣርቶ እና ተረጋግጦ ለመዝጋቢው እንዲቀርብ መደረግ አለበት ፤ ትምህርት ቤቱም ተማሪዎቹን ለማስተማር የሚያስችል የእውቅና ፈቃድ የተሰጠው ስለመሆኑ በሚመለከታቸው አካላት የተረጋገጠ መሆን አለበት ፤ ተመዝጋቢዎቹ መንግስታዊ ያልሆኑ መደበኛ ትምህርት ቤት ተማሪ ከሆኑ ትምህርት ቤቶቹ በኢትዮጵያ ስርአተ ትምህርት የማያስተምሩ ከሆኑ የስርአተ ትምህርት አቻ ግምታ አስርተው በማቅረብ እና ፈተናውን ለመውስድ የሚችሉ መሆናቸው በሚመለከተው የመንግስት አካል ማርጋገጫ ካልቀረበ መመዝገብ አይችሉም ፤ በፈተና አስተዳደር መመሪያ አንቀጽ እና በዚህ ማንዋል አንቀጽ 11 ንኡስ አንቀጽ 1 እ ና 2 የተጠቀሱት ዓመታት ተከታታይ ካልሆኑ ላቋረጡበት ምክንያት በቂ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው ፤

ተመዝጋቢዎች የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው እንዲመዘገቡ ማድረግ … በማታ ክፍለ ጊዜ ትምህርታቸውን ተከታትለው ለኢትዮጵያ አጠቃላይ (2ኛ) ደረጃ ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል ) ፈተና የሚመዘገቡ ተመዝጋቢዎች የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያለፉ እና ከ 9 ኛ እስከ 11ኛ ለአንድ የክፍል ደረጃ ሦስት ተርም ተምረው ያጠናቀቁ የ፲፪ኛ ክፍልን የመጀመሪያ “ ተርም ” አጠናቀው የሁለተኛውን ወይም የሦስተኛውን ተርም በማታው የትምህርት ክፍል በመማር ላይ ያሉ መሆን አለባቸው ፤ በርቀት ወይም በበይነ መረብ መስመር መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ (12ኛ) ፈተና የሚመዘገቡ በፈተና አስተዳደር መመሪያ ከአንቀጽ 11(1) እስከ (3) የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ትምህርት ሚኒስቴር ለርቀትና ለበይነ መረብ ትምህርት ፕሮግራም ያስቀመጠውን የትምህርት ጊዜ አጠቃቀም ያሟሉ መሆን አለባቸው ፤ በፈተና አስተዳደር መመሪያ አንቀጽ 6/ በንኡስ አንቀጽ (5) የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የርቀት ትምህርት ተፈታኞች ከሌሎች ፕሮግራምች ጋር ሳይቀላቀሉ በተማሩበት ት/ ቤት ስምና ኮድ መመዝገብ አለባቸው ፤ የመከለከያ ተፈታኞችም ለማታው ክፍለ ጊዜ በተቀመጠው አግባብ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከሌሎች ፕሮግራምች ጋር ሳይቀላቀሉ በተማሩበት ት/ ቤት ስምና ኮድ መመዝገብ አለባቸው ፤

ተመዝጋቢዎች የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው እንዲመዘገቡ ማድረግ … በግል በድጋሚ ፈተና ለመውሰድ ለሚያመለክቱ ተመዝጋቢዎች ቀደም ሲል የተፈተኑበትን ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያላሟሉ መሆን አለባቸው ፤ በአንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ 7 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ተመዝጋቢዎቹ በባለፈው ዓመት በፈተና አስተዳደር መመሪያ ድንጋጌዎች መተላለፍ የተቀጡ እና ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበው በተለያየ ምክንያት ሳይወስዱ የቀሩ ተፈታኞች ለየክልሎቹ በተላለፈው የውጤት መግለጫ ሪፖርት ላይ ዝርዝራቸው ተጣርቶ ሊመዘገቡ ይችላሉ፤ባለፈው ዓመት የተፈተኑበት መለያ ቁጥር በተፈታኝ ዝርዝር መዝገብ ምርመራ ላይ መጻፍ ይኖርበታል ፤ በፈተና አስተዳደር መመሪያ በንኡስ አንቀጽ (7) የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በየዓመቱ የሚወሰነው የከፍተኛ ትምህርት የማለፊያ ነጥብ የሚያገለግልበት የጊዜ ገደብ የትምህርት ሚኒስቴር በሚወስነው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል ፤ ፤

የአስመዝጋቢ ትምህርት ቤቶችን አደረጃጀት እና አሰራር ተከትሎ መስራት አስመዝጋቢ ትምህርት ቤቶችን በቀላሉ ለመለየት የሚያስችል የትምህርት ቤት መለያ ኮድ እንዲሰጥ ይደረጋል ፤ የትምህርት ቤት መለያ ኮድ (school code) ባለ ስምንት አሃዝ ሲሆን የተመዝገቢውን ክልል ፣ ዞን ፣ የተመዝጋቢውን አይነት እና ትምህርት ቤቱ የተከፈተበትን ቅደም ተከተል የሚያመለክቱ ሁለት ሁለት ሆሂያት ናቸው ፤ መደበኛ ተፈታኞች (regular examinees) የሚባሉት ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተፈታኞች ሲሆኑ የመንግስት መደበኛ ትምህርት ቤቶች ፣ የግል መደበኛ ትምህርት ቤቶች ፣ የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች እና የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ት/ ቤቶች ተመዝጋቢዎችን ይመለከታል ፤ ከኢትዮጵያ ስርአተ ትምህርት ውጪ የሚገኙ የሌሎች ሀገራት የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች የስርአተ ትምህርት አቻ ግመታ በሚመለከተው አካል አሰርተው በዚህ ማንዋል ለራሳቸው በተዘጋጀው የተፈታኝ አይነት መለያ ኮድ ሊመዘገቡ ይችላሉ ፤

የአስመዝጋቢ ትምህርት ቤቶችን አደረጃጀት እና አሰራር ተከትሎ መስራት … የማታ ተፈታኞች (night examinees) በማታው ክፍለ ጊዜ ትምህርታቸውን ተከታተለው ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ ተፈታኞችን የሚመለከት ሲሆን በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች በማታው ክፍለ ጊዜ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተፈታኞችን ይመለከታል ፣ የግል ተፈታኞች (private examinees) ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ የተመዘገቡ ተፈታኞችን የሚመለከት ሲሆን በመንግስት ስር ትምህርት ቤቶች ስር በድጋሚ ፈተናውን ለመወስድ የተመዘገቡ ተፈታኞችን ይመለከታል ፤ የርቀት ትምህርት መርሃ ግብር ተመዝጋቢዎች የሚባሉት ከ9-12ኛ ክፍል የሚሰጠውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በርቀት ትምህርት መርሃ ግብር ለመስጠት ህጋዊ እውቅና በተሰጣቸው ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ሲካተተሉ እና ፈተናውን ለመውሰድ የተመዘገቡ ተፈታኞችን ይመለከታል ፤

የአስመዝጋቢ ትምህርት ቤቶችን አደረጃጀት እና አሰራር ተከትሎ መስራት … ተ.ቁ የ ተመዝጋቢው አይነት የትምህርት ቤት መለያ ኮድ የትምህርት ቤቱ ስም RNP Catagory ክልል ዞን የተመ / አይነት የት / ቤት ቁጥር 1 የመንግስት መደበኛ 14 01 01 01 Addis Ketema®           Regular 2 የግል መደበኛ 14 01 02 01 Kidus Raguel® 3 የኢትጵያ ማህበረሰብ ት/ቤቶች 16 01 06 01 RIYADH COMM.SCH.(R)   4 ልዩ/አዳሪ ት/ቤት መደበኛ 14 02 07 01 Gelan Boys Boarding® 5 የሌሎች ሀገራት የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች 14 08 11 01 ICS® 6 የ ድጋሚ ተፈታኝ 14 01 05 01 Addis Ketema (P) Private 7 የመንግስት የማታ 14 01 03 01 Addis Ketema (N)       Night 8 የግል የማታ 14 01 04 01 Kidus Raguel (N) 9 የርቀት ትምህርት ተፈታኝ 11 03 08 06 Arbamich Nice (Dis) 10 የመከላከያ ሰራዊት ተፈታኝ 14 03 09 01 Addis Ababa(D) 11 የበይነ መረብ ተፈታኝ 14 05 10 01 ACT(O)

የተፈታኞችን መሰረታዊ መረጃዎች በጥንቃቄ መሙላት Demographic Characters Option Remark Sex Male/Female  Text-drop list Name Name/ F.Name /G.F Name  Text Age >=17  Number Nationality Ethiopian/Non Ethiopian Text-drop list Sight Blind/Not blind Text-drop list Handicaped Leg/Hand/Both Text-drop list Hearing Imparirment Yes/No Text-drop list Back Bone Problems Yes/No Text-drop list Twins Yes /No Reference No. School code+01,02 Family Background Pastoral/Not pastoral Text-drop list Stream Natural/Social Text-drop list

ማጠቃለያ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ምዝገባው ለመዝጋቢዎች ተገቢውን ሥልጠና በዞን ደረጃ በመስጠት ከላይ በወጣው መርሃ ግብር መሰረት በበይነ መረብ እና ያለበይነ መረብ በተሻሻለው መተግበሪያ ( Eduportal ) እንዲካሄድ ይደረጋል ፤ ለምዝገባው የሚያስፈልጉ ግብአቶች በወረዳ ትምህርት ጽ/ ቤቶችና ትምህርት ቤቶች እንዲሟሉ ይድርጋል፤ክልሎችና ዞኖች የአፈጻጸም ሂደቱን በመከታተል እንዲሟላ ያደርጋሉ ፣ ምዝገባውን በበይነ መረብ በቀላሉ ማካሄድ እንዲቻልና የኢንተርኔት እና የመብራት መቆራረጥ እንዳይኖር አገልግሎቱ እና የክልል መስተዳድሮች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር መስራት ይጠበቅባቸዋል ፣ የ2017 ዓ.ም የተፈታኞች የተፈታኝነት ማረጋገጫ እና የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ (admission card) በተዘጋጀው የበይነ መረብ መተግበሪያ አማካኝነት ተደራሽ እንዲሆን ይደረጋል ፤ የተፈታኞች ምዝገባ የመደበኛው ትምህርት አካል በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት መዋቅሮች ተገቢውን ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ፤

ማጠቃለያ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች … የምዝገባ አስፈጻሚዎች እና ፈጻሚዎች በተሰጣቸው የኃላፊነት ገደብ ውስጥ ብቻ የምዝገባውን ስራ ማከናወን አለባቸው ፡ ከምዝገባ በኃላ የሚቀርቡ የስም ለውጥ ማስተካከያዎች በአገልግሎቱ የአፈጻጸም መመሪያ መሰረት ተቀባይነት እንደማይኖራቸው ግንዛቤ ተወስዶ መሰራት አለበት ፤ ከምዝገባው ጎን ለጎን የፈተና ጣቢያ መረጃዎች በተዘጋጀው መተግበሪያ በበይነ መረብ እንዲሰበሰቡ ይደረጋል ፤ የምዝገባው ሂደት ሲጠናቀቅ ተፈላጊ መረጃዎች እና የምዝገባ ሰነዶች ለአገልግሎቱ እንዲቀርቡ በማድረግ የአፈጻጸም ግምገማ የሚካሄድ ይሆናል ፣ የ2017 ዓ.ም የተፈታኞች የተፈታኝነት ማረጋገጫ እና የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ (admission card) በተዘጋጀው የበይነ መረብ መተግበሪያ አማካኝነት ተደራሽ እንዲሆን ይደረጋል ፤

አ መሰግናለሁ !
Tags