BPR business process reengineering for city of addis ababa.pptx

ErbanaKassegn 7 views 62 slides Oct 18, 2025
Slide 1
Slide 1 of 62
Slide 1
1
Slide 2
2
Slide 3
3
Slide 4
4
Slide 5
5
Slide 6
6
Slide 7
7
Slide 8
8
Slide 9
9
Slide 10
10
Slide 11
11
Slide 12
12
Slide 13
13
Slide 14
14
Slide 15
15
Slide 16
16
Slide 17
17
Slide 18
18
Slide 19
19
Slide 20
20
Slide 21
21
Slide 22
22
Slide 23
23
Slide 24
24
Slide 25
25
Slide 26
26
Slide 27
27
Slide 28
28
Slide 29
29
Slide 30
30
Slide 31
31
Slide 32
32
Slide 33
33
Slide 34
34
Slide 35
35
Slide 36
36
Slide 37
37
Slide 38
38
Slide 39
39
Slide 40
40
Slide 41
41
Slide 42
42
Slide 43
43
Slide 44
44
Slide 45
45
Slide 46
46
Slide 47
47
Slide 48
48
Slide 49
49
Slide 50
50
Slide 51
51
Slide 52
52
Slide 53
53
Slide 54
54
Slide 55
55
Slide 56
56
Slide 57
57
Slide 58
58
Slide 59
59
Slide 60
60
Slide 61
61
Slide 62
62

About This Presentation

this is Business Process Reengineering


Slide Content

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የመሰረታዊ ስራ ሂደት ለውጥ ጥናት ረቂቅ ሰነድ ሰነድ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ

  ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ መሰረታዊ ስራ ሂደት ለውጥ ጥናት BPR ሰነድ የጥናት ቡድኑ አባላት ስም አማካሪዎች 1. ፋሲል ወ/ ማርያም 2. መሐመድ አብዱራሂማን 3. ኢሳያስ ግርማ

መግቢያ የከተማ አስተዳደሩና በስሩ የሚገኙ አካላትን አደረጃጀትና መዋቅር በየጊዜው ከተማችን ከደረሰችበት የዕድገት ደረጃ አኳያ የተመጣጠነና የከተማዋንም ቀጣይ የለውጥና የልማት እንቅስቃሴ አጠናክሮ በማስቀጠል አስተማማኝ ደረጃ ላይ ለማድረስ እንዲሁም አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ነባራዊ ለውጦችን አጣጥሞ ቀጣይነት ባለው መልኩ አብሮ ለመጓዝ የሚያስችል አደረጃጀትና መዋቅር አጥንቶ ተግባራዊ እያደረገ መምጣቱ ይታወቃል ፡፡

የቀጠለ በዚሁ መስረት በአዲስ መልክ እንዲደራጅ ከተደረጉት አስፈጻሚ አካላት መካከል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አንዱ ሲሆን ቢሮው ሶስት ዘርፎችን በስሩ በማዳራጅት ወደ ስራ የገባ ሲሆን በአዋጅ 74/2014 የተሰጠውን ተግባርና ሀላፊነት ሲያከነውን ቆይቷል ይሁንና በቢሮው ውስጥ የተለየዩ የሥራ ዓይነት ፣ ብዛትና ውስብስብነት ያላቸው የስራ ክፍሎች መኖራቸው እና የተለየያ የሙያ ዓይነት ፣ መረጃ ፣ ግብዓትና ሌሎች ሁኔታዎችን የሚጠይቁ በመሆኑ ተቋሙን እንደገና በመፈተሽ ስልጣንና ተግባሩን መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ እቅድ ተዘጋጅቶል ።

የጥናቱ አላማ የዚህ ጥናት ዓላማ የከተማ አስተዳደሩ የጀመራቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ቀጣይነትና ስኬት ማረጋገጥ የሚያስችል ብቁ ዘመናዊ አደረጃጀት በመፍጠር ጠንካራ ተቋማዊ አቅም እንዲፈጠር ማስቻል ነው ፡፡

የጥናቱ ዝርዝር ዓላማዎች ተልእኮ የሚያሳካ ተጠሪነትንና የስራ ክፍፍልን በግልጽ ሊያሳይ የሚችል ፣ የተቀናጀ ፣ ብቁ ፣ ወጪ ቆጣቢና ረዘም ላለ ጊዜ የሚያገለግል አደረጃጀትና መዋቅር ማዘጋጀት ፣ ውጤታማ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ግልጽ የአሰራር ስርአት እና ብቃት ያለው የሰው ሃይል እንዲኖር ማስቻል ፣

የጥናቱ መነሻ ሁኔታ አሁን ካላንበት ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ከተማችን አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና የሌሎች የዓለማት ሀገራትና ዜጎች የምትማርክ ከተማን በመፍጠር የከተማችንን ብሎም የሀገራችንን ዜጎች ብቁ ተወዳዳሪና ሥራ ፈጣሪ እንዲሆን በከተማ አስተዳደሩ አንዱ የትኩረት አቅጣጫ ሊሆን ይገባል ። ይህንን ከመፈፀም እና ከማስፈፀም አኳያ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ተቋማት የተሻለ አደረጃጀት እና ብቃት እንዲኖራቸው ማደረግ ተገቢነቱ አጠያያቂ አይሆንም ። በመሆኑም ለጥናቱ መነሻ ሁኔታዎችን በዝርዝር ቀርባል ፡-

የጥናቱ መነሻ ሁኔታ አዲጊ የህዝብ ፍላጎት እንደመነሻ የቴክኖሎጂ የጥናትና ምርምር ውጤቶች እንደ መነሻ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እንደመነሻ የቢሮው የአደረጃጀት ፣ የተጠሪነት ፣ ተመጋጋቢ ያልሆኑ የስልጣንና ተግባር በአንድ ላይ መኖር እንደመነሻ

ከጥናቱ የሚጠበቅ ውጤት ግልፅ እና በቂ የቁጥጥር አድማስ ያለው አደረጃጀትና አሰራር በመዘርጋት በብቃት ማስተዳደር የሚችል ተቋማዊ አደረጃጀት፣ የየተቋሙን ተግባርና ኃላፊነት መወሰን፣ ለሚደራጁት የስራ ኃላፊዎችና ክፍሎች ከዓላማ አንፃር የተለዩ ተግባርና ኃላፊነቶች መወሰን፡፡

ከጥናቱ የሚጠበቅ ውጤት ግልፅ እና በቂ የቁጥጥር አድማስ ያለው አደረጃጀትና አሰራር በመዘርጋት በብቃት ማስተዳደር የሚችል ተቋማዊ አደረጃጀት፣ የየተቋሙን ተግባርና ኃላፊነት መወሰን፣ ለሚደራጁት የስራ ኃላፊዎችና ክፍሎች ከዓላማ አንፃር የተለዩ ተግባርና ኃላፊነቶች መወሰን፡፡

የችግሩ ምንጭ  

ከአደረጃጃት አንፃር ያሉ ክፍተቶች

የአሰራር ስርዓት ከመዘርጋት አንፃር ያሉ ችግሮች

የሰው ኃይል የስራ ስምሪትን በተመለከተ ያጋጠሙ ችግሮች በሁለቱ ዘርፎች ያሉ ባለሙያዎች ፕሮፋይል የተለያየ መሆን አንዱ ከአንዱ የሚማርበትና የሚረዳዳበት ምቹ ሁኔታ አለመኖር ፤ ሰራተኞችን አቀናጅቶ የስራ ስምሪት ለመስጠት አመቺ አለመሆን ፤ በሚፈጠረው የደረጃ ዕድገቶች በሁለቱም ዘርፎች ያሉ ባለሙያዎችን ተጠቃሚ ባለማድረጉ በውስጥ ባለ ሰራተኛ መተካት አለመቻልና የሰራተኛውን የስራ ተነሳሽነት የማደግ ተስፋ የሚያጨልም መሆኑ ፤

የአመራር የስራ ስምሪት አሰጣጥ ፣ ክትትልና ድጋፍ በተመለከተ ያጋጠሙ ችግሮች በተገልጋዮች መለያየት የተነሳ አመራሩ ተገልጋይ ተኮር ሆኖ የስራ ስምሪት ለመስጠትና ለመደገፍ መቸገር ፤ የስራ ውጤቶችን በጋራ ለመገምገም መቸገር ፤ በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጡ ተጨማሪ ተልዕኮዎች ለአንድ ዘርፍ ብቻ መስጠትና ጫና መፍጠር ( ለአብነት ያህል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፣ የአረንጓዴ አሻራ ፣ በጦርነቱ የተጎዱ ክልሎችን መልሶ ማቋቋምና የጳጉሜ ቀናት ) ተጃምሎ መሄድ ፤ በአጠቃላይ የከተማ አስተዳደሩ ከቢሮ ከሚጠብቀው ውጤት አንፃር የከተማውን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዕድገት ውጤታማ ማድረግ አለመቻል ፡፡

የቢሮ ስልጣን ተግባርና ሃ ላፊነት 1 . የከተማ አስተዳደሩን ተልዕኮ ሊያሳኩ የሚያስችሉ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር መስኮችን ይለያል፣ከተማዊ የኢኖቨሽንና ቴክኖሎጂ ምርምር ፕሮግራሞችን ያካሄዳል፤ እንዲካሄዱ ያደርጋል፤ ያስተዋውቃል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤ 2. የከተማ አስተዳዳሩን የኢኖቬሽን፣ የስማርት ቴክኖሎጂ ፣ የኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ፣ ስትራቴጂዎች ህጎች፣ እና ፕሮግራም ይቀርጻል፣ለአፈፃፀሙ ዝርዝር ከከተማዊ የልማ አቅጣጫ ጋር የተጣጣሙ መርሀ ግበር ያዘጋጃል፣በሚመለከተው አካል ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤

የቢሮ ስልጣን ተግባርና ሃ ላፊነት ….. 3. በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጡ አገልግሎቶችን የተቀናጀ ለማድረግ ተገቢውን መረጃ ማሰባሰብ፣መተንተን የሚያስችል ከተማ አቀፍ የመረጃ ቋት ያደራጃል ፤ ያስተዳድራል ፤ ቀጣይነቱን ያረጋግጣል ፤ 4. የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የኮምፒውተር መረቦች ፣ አፕሊኬሽኖች ፣ የኔትዎርክ ኮኔክትቪቲ እንዲቀናጁና እንዲናበቡ ያደርጋል እንዲሁም ይቆጣጠራል ፤ 5. ለከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የሶፍትዌር ሲስተም ያለማል ፣ እንዲለማም ያደርጋል ፤ ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል ፤

የቢሮ ስልጣን ተግባርና ሃ ላፊነት ….. 6. በከተማው አስተዳደር ተቋማት የሚለሙና የሚተገበሩ የጂኦ-ኢንፎርሜሽን ሲስተም በተመለከተ የተቋማትንና የከተማ አስተዳደሩን ፍላጎት መሠረት አድርጎ በጋራ ይሰራል ፤ 7. ለከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ያለማል ፣ እንዲለማም ያደርጋል ፤ ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል ፤ 8. በኮምፒውፒተር መረብ ዝርጋታ ፣ በሶፍትዌር ሲሰተም ልማት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ዘርፍ ማማከር ለሚሰማሩ ግለሰቦችና ተቋማት የሙያ ፈቃድ ይሰጣል ፤

የቢሮ ስልጣን ተግባርና ሃ ላፊነት ….. 9 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ፣ አስተዳደር እንዲሁም አጠቃቀም በተመለከተ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ይሰጣል ፣ ያስተባብራል ፤ 10. የአስተዳደሩ የግዥና ንብረት አስተዳደር እና ሌሎች ሕግ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ አግልግሎት መስጠት ያቆሙ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዕቃዎችን ይለያል ፤ ተለይተው አግልግሎት መስጠጥ የሚችሉትን ይጠግናል ወይም እንዲጠገን ያደርጋል ፤ ከአግልግሎት ውጭ የሆኑትን እንዲወገዱ ለሚመለከተው አካል ይልካል ፤ 11. የከተማ አስተዳደሩን መረጃዎች እና ሲሰተሞች ደህንነት ይቆጣጠራል ፣ የደህንነት መቆጣጠሪያ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል ፣ በሲስተሞችና በመሰረተ ልማቶች ላይ የደህንነት ኦዲት ያደርጋል ፤

የቢሮ ስልጣን ተግባርና ሃ ላፊነት ….. 12. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢዝነስ ኃሳብ ያላቸው ግለሰቦችና ቡድኖችን ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል ተግባራዊ ያደርጋል ፤ 13. ለከተማው አስተዳደር ተቋማት የክላውድ ዳታ ሴንተርና የክላውድ አገልግሎት ተግባራዊ ያደርጋል ፤ እንዲሁም የክላውድ አገልግሎት የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል ፤ 14. የአስፈፃሚ ተቋማት አግልግሎት አሰጣጥ በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽ ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆንበ ያደርጋል እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ የለሙ መሰረተ ልማቶችና ሲስተሞች ያስተዳድራል ፤ ይቆጣጠራል ፤ ይመራል ፤

የቢሮ ስልጣን ተግባርና ሃ ላፊነት ….. 15. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከል ያደራጃል ፣ በበላይነት ይመራል ፤ ያስተባብራል ፤ 16. የከተማውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኦዲት በበላይነት ይመራል ፤ ያስተባብራል ፡፡ 17. የኢኖቬሽንና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የጥገና ፣ የቤተ ሙከራ ሰርቶ ማሳያ እና የስልጠና ማእከል ያደራጃል ፣ ያሰለጥናል ፣ በበላይነትም ይመራል ፤

የቢሮ ስልጣን ተግባርና ሃ ላፊነት ….. 18. ሀገር-በቀል ቴክኖሎጂዎችን ለማሻሻል ፣ ለማሳደግና ለገበያ ለማቅረብ የሚደረጉ ጥናቶችን ፤ የምርምርና ስርጸት ሥራዎችን ያበረታታል ፣ ወደ ተግባር እንዲሸጋገሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ፤ 19. የከተማ አስታዳደሩን ሥርዓተ-ትምህርት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት አንፃር መቃኘቱን ለማረጋገጥ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ የትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር ይሰራል ፤

የቢሮ ስልጣን ተግባርና ሃ ላፊነት ….. 20. የከተማ አስተዳደሩን የኢ-መንግስት ልማት እና የዲጂታላይዜሽን ስርዓቶች ለማስተግበር የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል ፣ ተግባራዊ ያደርጋል ፤ 21. በከተማ አስተዳደሩ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማትና ለፈጠራ ሥራዎች ዕድገት አስተዋጽዖ ላበረከቱ ግለሰቦች ወይም ተቋማት ሽልማትና ማበረታቻ የሚሰጥበትን ሥርዓት ይዘረጋል ፣ ተግባራዊም ያደርጋል ፤

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች ራዕይ 2025 የላቀ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለነዋሪዎቿ እና ለጎብኚዎቿ ምቹ የሆነች አዲስ አበባን ማየት ፡፡ ተልዕኮ ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት በማልማት እና ዲጂታል አገልግሎት በማስፋፋት የአዲስ አበባን ከተማ ነዋሪዎች እና የጎብኚዎቿን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ፡፡

እሴቶች በጎ ሕሊናና ቅን ልቦና የላቀ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት አዳዲስ ፈጠራዎችን ማመንጨት የስራ ፍቅርና ትጋት ተጠያቂነት ግልፅኝነት በትብብር መስራት ቀልጣፋና ውጤታማ አግልግሎት

የአደረጃጃት መነሻ መሠረተ-ሀሳቦች ሥራዎችን በዓላማ እና ውጤት ዙሪያ ማደራጀት ሥራዎች ከመነሻ አስከ መድረሻ ባላቸው የፍሰት ሂደት ላይ እንዲያተኩሩ ማድረግ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ተብሎ የተመረጠበት ምክንያት ዓለማቀፍ ፈጣን የቴክኖሎጅ መለዋወጥ በመረጃ ደህንነት ስርዓታችን (የሳይበር ሽብር መበራከት (በመሰረተልማት፣ በሬዲዮ ዌቭ እና በመሳሰሉት ቴክኖሎጅ ) ላይ ስጋት የሚፈጥር እንደመሆኑ መጠን መንግሥት የፖለቲካ አቅጣጫ በትኩረት የሚሰጥበት እንዲሁም ለዘርፉ ልዩ ፖሊስ፣ መመሪያ እና ደንብ የሚያስፈልግ በመሆኑ፣

ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮችና ውጤታቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ውጤት ፡- ጥራትና ደህንነቱን የተጠበቀ የኢንፎርሜሽ ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትና ሲስተም ማሳደግ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኦፕሬሽንና ጥገና ውጤት ፡- ቀልጣፋና ቀጣይነት ያለው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ተደራሽነት ስማርት ሲቲ ውጤት ፡- በጥናትና ምርምር የተለወጠ እና በእንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የዘመነ ከተማ

ዋና ዋና ተግባራት / አገልግሎቶች /… 1. ጥናትና ምርምር ማድረግ 2. ስማርት ቴክኖሎጂ መተግበር 3. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፕሮግራሞችን ፣ስታንዳርድ ማሻሻል እና መተግበር 4. ከተማ አቀፍ የመረጃ ቋት ማልማት 5. ከተማ አቀፍ የመረጃ ቋት ማስተዳደር 6 . የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት አዋጭነት ጥናት

ዋና ዋና ተግባራት / አገልግሎቶች /… 7. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ዲዛይን 8. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ማልማት 9. የሶፍተዌር ሲስተም ልማት አዋጭነት ጥናት 10. የሶፍተዌር ሲስተም ዲዛይን 11. የሶፍተዌር ሲስተሞችን ማልማት 12. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማቀናጀት

ዋና ዋና ተግባራት / አገልግሎቶች /… 13. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ማስተዳደር መቆጣጠር 14. ሶፍተዌር ሲስተም ማስተዳደር 15. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማማከር ፣ የሙያ ፈቃድ መስጠት 16. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የአቅም ግንባታ 17. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረ ተልማት መጠገን ፤ማደስ እና ማሰወገድ

ዋና ዋና ተግባራት / አገልግሎቶች /… 18. የከተማ አስተዳደሩን መረጃዎች እና ሲሰተሞች ደህንነት መቆጣጠር 19. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኦዲት 20. የሳይበር ደህንነት ኦዲት 21. የክላውድ ዳታ ሴንተር አገልግሎት 22. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከል ፤ኢንኩቤሽን ሴንተር ማደራጀት

ዋና ዋና ተግባራት / አገልግሎቶች /… 23. ሀገር-በቀል ቴክኖሎጂዎችን መደገፍ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሽግግር 24. የከተማ አስታዳደሩን ሥርዓተ-ትምህርት በቴክኖሎጂ መደገፍ 25. የኢ-መንግስት እና የዲጂታላይዜሽን መተግበር 26. ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማትና ፈጠራ ሥራዎች እውቅና መሰጠት 27. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትና ሲስተም ጥራት ማረጋገጥ 28. የጂኦግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተም ፕላትፎርም አገልግሎት

የሥራ ሂደቱ መጠሪያ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ደህንነት ዳይሬክቶሬት

የ ሥ ራ ሂደቱ መግለጫ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ደህንነት ዳይሬክቶሬት በከተማ አስተዳደሩ የለሙ የኢንፎርሜሽን ሲስተሞች፣ መሰረተ ልማቶችና የመረጃ ማከማቻዎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን የሳይበር ጥቃት አስቀድሞ ለመከላከልና ስጋቶችን ለመቀነስ እንዲሁም አደጋ ሲደርስ መመለስ የሚያስችሉ ስራዎችን የመስራት ኃላፊነት ያለበት ሲሆን፤ ይህን ለማድረግ የሚያስችለውን በከተማ ደረጃ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ሴኪዩሪቲ ፖሊሲ ያዘጋጃል/ያሻሽላል ተግባራዊ ያደርጋል፣ የደህንነት ስጋቶችን ይለያል ኦዲት ያደርጋል፣ ጥበቃ ያደርጋል፣ የደህንነት አደጋዎችን ይለያል፣ የደህንነት ችግሮች ሲታዩም የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣ ጉዳቶችን በመመለስ የመንግስትና የህዝብ መረጃ ደህንነት እንዲጠበቅ ያ ደርጋል ።

በዳይሬክቶሬቱ ሥር የሚገኙ ቡድኖች 1. የሳይር ደህንት አስተዳደር እና ንቃተ ህሊና ቡድን 2. የሳይበር ደህንነት ኢንጂነሪንግ ቡድን 3. የሳይበር ደህንነት እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኦዲት ቡድን 4. የሳይበር ደህንነት ክስተት ክትትል እና ምላሽ ቡድን

የሥራ ሂደቱ መጠሪያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት

የሥራ ሂደቱ መጠሪያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የቴክኖሎጂ፣ የስማርት ሲቲ ፣ የመሰረተ ልማት ጥናትና ምርምር እንዲሁም የኢኖቬሽንና የኢሜርጅንግ ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር ውጤቶችን የመደገፍ ፣ የማበረታታት፤ የማስረፅ፤ የማማከር፣ የማሸጋገር እንዲሁም የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ከህበረተሰቡ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እንዲስፋፉ ለማድረግ የተቋቋመ ነው፡፡

በዳይሬክቶሬቱ ሥር የሚገኙ ቡድኖች 1. የቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር ቡድን 2. የመሰረተ ልማት / ኢንፍራስትራከቸር ጥናትና ምርምር ቡድን 3. የቴክኖሎጂ ሽግግር ቡድን 4. የስታንዳርድ ዝግጅትና ሪጉላቶሪ ቡድን

የሥራ ሂደቱ መጠሪያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት

የስራ ሂደቱ መግለጫ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት ቢሮ አቅም ግንባታ እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ፣ የሰው እና የተቋማት አቅም ግንባታ ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ስልጠና ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሴሚናሮች እና ወርክሾፖች ዝግጅት ፣ የሳይንስ ኮሙኒኬሽን ፣ ለተመረጡ የፈጠራ ስራዎች የማበረታቻ ሽልማቶችን መስጠት የቴክኖሎጂ ዞን መለየትና ወደ ሰራ ማስገባት ፣ የሳይንስ ካፌዎችን ማደራጀት ፣ ተቋማዊ ዕውቀት መገንባት (Organization Memory)፣ ዕውቀት ማኔጅምንት (Knowledge Management)፣ ዩኒቨርሲዩችና / ኢንዱስትሪ ትስስር ስራዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የተቋቋመ ዳይሬክቶሬት ነው ፡፡

በዳይሬክቶሬቱ ሥር የሚገኙ ቡድኖች 1 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የሰው ሐይል እና አቅም ግንባታ ቡድን 2 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢዝነስ ልማት ቡድን 3 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሙያ ፈቃድ መስጠት ቡድን

የሥራ ሂደቱ መጠሪያ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ፕሮጀክት ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት

የስራ ሂደቱ መግለጫ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ፕሮጀክት ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት የሚተገበሩ የኢንሮርሜሽን ቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው በጀት ፣ ጥራትና ወስን ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት ያለበት ነው ፡፡

በዳይሬክቶሬቱ ሥር የሚገኙ ቡድኖች 1 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ፕሮጀክት ማኔጅመንት ቡድን 2 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ጥራት ማረጋገጥ ቡድን 3 የፕሮጀክት ግምገማና ዶክመንቴሽን ቡድን

የሥራ ሂደቱ መጠሪያ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት እና ዲዛይን ዳይሬክቶሬት

የስራ ሂደቱ መግለጫ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት እና ዲዛይን ዳይሬክቶሬት በዓለም አቀፍ ስታንዳርድ መሰረት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማቶችን ለመገንባት የመሰረተ ልማት ግንባታ የክፍተት አዋጪነት ጥናት በማድረግና በመተንተን ተስማሚ ቴክኖሎጂ በመምረጥ ዲዛይን በማዘጋጀት የመረጃ መረብ ፣ የዳታ ማዕከል ፣ የኮሙኒኬሽን ፣ የኮምፒዩቲን ( ሰርቨር ፋሲሊቲ )፣ የሴኪዩሪቲ መሰረተ ልማት ይዘረጋል ። መሰረተ ልማቶቹ ተገንብተው ከተጠናቀቁ በኋላ የአጠቃቀም ስልጠና እንዲሰጥ ያደርጋል ፡፡ ዳይሬክቶሬቱ የከተማ አስተዳደሩን የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ዘመናዊ ለማድረግ የአገልገሎት አሰጣጥን ለማዘመን በሚያስችል መልኩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ሽፋንን ያሳድጋል ፣ ማንኛውንም አዲስ የመሰረተ ልማት ግንባታ የመገንባት ፣ የማሻሻያ ፣ ወደ አዲስ ቴክኖሎጂ የማሸጋገር ተግበር የዚህ ዳይሬክቶሬት ኃላፊነት ነው ፡፡

በዳይሬክቶሬቱ ሥር የሚገኙ ቡድኖች 1 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ቢዝነስ አናሊሰት ቡድን 2 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት አርክቴክቸራል እና ዲዛይን ቡ ድ ን 3 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ግንባታ 4 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ቅንጅት ደህንነት እና ፍተሻ ቡድን

የሥራ ሂደቱ መጠሪያ የሶፍትዌር ልማት ዳይሬክቶሬት

የስራ ሂደቱ መግለጫ የሶፍትዌር ልማት ዳይሬክቶሬት ከተማ አቀፍ የሶሉሽን አርክቴክቸራል ፍሬምወርክና አለም አቀፍ ስታንዳርዶችን የተከተሉ ሶፍትዌሮችን የማልማት ፣ የሶፍትዌር ልማት የአዋጪነት ጥናት የማድረግና የመተንተን ፣ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን የመምረጥና የሲስተም ዲዛይን የማዘጋጀት ፣ የተለያዩ የሶፍትዌር ሲስተሞች ፣ ፖርታል / ድረ-ገጽ ፣ ዳታ ቤዝ / ዳታ ዌርሃውስ ፣ ሞባይል አፕልኬሽን ፤ የኢ-ትምህርት ልማት (E-learning)፤ የጂኦግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተም ፕላትፎርም ፤ ኦፕን ዳታ ፖርታል የማልማት እንዲሁም የኢ-መንግስት መረጃዎችን ዲጂታላይዝ የማድረግና የለሙ ሲስተሞች ተቀናጅተው እንዲሰሩ የማድረግ ኃላፊነት የተሰጠው ከፍል ነው ፡፡

በዳይሬክቶሬቱ ሥር የሚገኙ ቡድኖች 1 ቢዝነስ አናሊስስ (business analysis) 2 ሶሉዩሽንዲዛይንናአርክቴክቸር ቡድን (Solution design and architecture) 3 ሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት ቡድን (Software Development Team) 4 ሶፍትዌር ደህንነት ልማትና ዴቭኦፕ ቡድን (Software security development and deveope Team)

የሥራ ሂደቱ መጠሪያ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኦፕሬሽንና ጥገና ዳይሬክቶሬት

የስራ ሂደቱ መግለጫ ይህ ዘርፍ የከተማ አስተዳደሩን የአገልግሎትና ኦፕሬሽን እንዲሁም የጥገናና እድሳት ስራዎችን በበላይነት ለመምራት እና በመንግስት ተቋማት ጥራታቸውን ጠብቀው የተዘረጉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ፣ የኔትወርክ ሲስተሞች እና ኮኔክቲቪቲ፣ሶፍትዌሮች ፣ የሶፍትዌር ሲስተሞች ፣ ፖርታሎች እና ደህረገጾች ፣ ሞባይል አፕሊኬሽኖችን ከአልሚው ክፍል በመረከብና በተገቢው በማስተዳደር ፣ በመከታተል እና ችግሮችን እየፈቱ ቀጣይነት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ለመምራት ፣ ለማስተዳደር የተቋቋመ የስራ ከፍል ነው ፡፡

በዳይሬክቶሬቱ ሥር የሚገኙ ቡድኖች 1 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኔትዎርክ መሰረተ ልማት አስተዳደር ቡድን 2 የሶፍትዌር ሲስተም አስተዳደር ቡድን 3 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ጥገና ፣ እድሳት እና ማስወገድ ቡድን 4 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሄልፕ ዴስክ

የሥራ ሂደቱ መጠሪያ የዳታ ማዕከልና የክላውድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

የስራ ሂደቱ መግለጫ ፡- የዳታ ማዕክልና የክላውድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በአልሚ ክፍሎች የለሙ መሰረተ-ልማትና ሲስተሞችን በኃላፊነት በመረከብና ከተቋማት የሚቀርቡ የአገልግሎት ጥያቄዎችን መሰረት በማድረግ ወይም ፍላጎት እንዲያሳዩ በማነሳሳት የመሰረተ ልማት አገልግሎት (IaaS) ፤ የፕላትፎርም አገልግሎት (PaaS) ፤ የሶፍትዌር አገልግሎት (SaaS) ፤ የሆስቲንግ አገልግሎት ፤ የአክቲቭ ዳይሬክተሪ አገልግሎት ፤ የስቶሬጅ አገልግሎት ፤ የኮርፖሬት ኢሜል    አገልግሎት ፤ የቪዲዮ ኮንፈረንስ አገልግሎት ፤ የባክ አፕ አገልግሎት ፤ የዳታቤዝ አገልግሎት ፤ የዳታ / የመረጃ አገልግሎት ፤ የቨርቸዋል ዲስክ ቶፕ አገልግሎት ( VDI ) ፤ የጂኦ - ኢንፎርሜሽን አገልግሎት የሚሰጥ ዳይሬክቶሬት ሲሆን ዳይሬክቶሬቱ ተቋማት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ የስራ አካባቢ እንዲኖራቸውን አሰራራቸውን እንዲያዘምኑ የማድረግ ኃላፊነት የተሰጠው ነው ፡፡

በዳይሬክቶሬቱ ሥር የሚገኙ ቡድኖች 1. የክላውድ እና የጂኦግራፊካል አገልግሎት ቡድን 2. የመረጃ ቋት አገልግሎት ቡድን 3. የመረጃ ቋት ፋሲሊቲ አስተዳደር ቡድን

የክፍለ ከተማ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተልማት እና ዳታ ማእከል አስተዳደር ቡድን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጥገና እና እድሳት ቡድን ሶፍትዌር ልማት አስተዳደር ቡድን የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ቡድን በክፍለ ከተማ

የክፍለ ከተማ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ ቤት ወረዳ የኢ.ቴ መሰረተ ልማት አስተዳደር እና ጥገና ቡድን የወረዳ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ ቤት በወረዳ