SlidePub
Home
Categories
Login
Register
Home
General
የሰርጋችን ኮተታኮተቶች in Islam - Note and Summary.pdf
የሰርጋችን ኮተታኮተቶች in Islam - Note and Summary.pdf
zeharamohammed2recpl
6 views
18 slides
Apr 18, 2025
Slide
1
of 18
Previous
Next
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
About This Presentation
Weeding Theory of Islam
Size:
812.42 KB
Language:
none
Added:
Apr 18, 2025
Slides:
18 pages
Slide Content
Slide 1
(በዶ/ር ጀማልሙሀመድ)
Slide 2
4
1/16
ኢስላማዊጋብቻክቡርናየአሏህተአምርከሆኑትማህበራዊእሴቶችአንዱነው፡፡ሀያሉ
አሏህበተከበረውቁርአኑእንዲህይለናል፡-
﴿
َ
و ا
َ
ه
ْ
يَلِإ اوُنُك
ْ
سَت
ِ
ل ا
ً
جا
َ
وْزَأ
ْ
مُك
ِ
سُفنَأ
ْ
ن
ِ
م مُكَل
َ
قَل
َ
خ ْنَأ
ِ
ه
ِ
ت
َ
يَآ
ْ
ن
ِ
م
َ
و ًة
َْحْ
َ
ر
َ
و ًة�د
َ
و�م مُكَن
ْ
ي
َ
ب
َ
ل
َ
ع
َ
ج
َ
يََلَ َك
ِ
لَذ ِفِ �نِإ
ٍ
م
ْ
وَق
ِ
ل
ٍ
ت
َنو
ُ
ر�كَفَ ت
َ
ي﴾
"ለእናንተምከነፍሶቻችሁሚስቶችንወደእነርሱትረኩዘንድመፍጠሩ፣በመካከላችሁም
ፍቅርንናእዝነትንማድረጉከአስደናቂምልክቶቹነው፡፡በዚህውስጥለሚያስተውሉ
ህዝቦችተአምሮችአልሉ፡፡"አርሩም፣
ከጋብቻውጭያለግንኙነትበኢስላምክልክልየተደረገ፣የዝሙትተግባርነው፡፡ኢስላማዊ
ጋብቻሙስሊሞችራሳቸውንሀራምከሆነውዝሙትከመጠበቅምአልፈው፣ቤተሰብ
የሚመሰርቱበትናተውሂድንያነገበኢስላማዊህብረተሰብየሚገነቡበትማህበራዊተቋምነው፡፡
በሀገራችንይህማህበራዊተቋምበተስተካከለመሰረትላይእንዳይገነባየሚያደርጉ፣
የተመሰረተውንየትዳርህልውናአደጋላይየሚጥሉ፣ትዳሩከመፍረስቢድንምእንኳንዝቅሲል
ኢስላማዊቤተሰብን፣ከፍሲልደግሞኢስላማዊማህበረሰብንከመገንባትየሚያደናቅፉበርካታ
ኮተቶችተብትበውትይገኛል፡፡በእነዚህየጃህልያው(የድንቁርናው)ስርአት(ritual)
አካልናቅሪትበሆኑኋላቀርኮተቶችተተብትቦከሚከናወንሰርግናጋብቻ፤"በተውሂድየታነፀ፣
በሰለፎችጎዳናያበበትውልድይገኛል"ብሎማሰብየኮባተክል"ሙዝያፈራልኛል"ብሎ
እንደመጠበቅነው፡፡
Slide 3
ኮተት1
የልብስ"ማች"
"የልብስማች"የሚባለው፣ልጅከሚድሩትወገንበመሆንበሰርግላይየሚሳተፉሰዎችን
በልብስአይነትናቀለምየማመሳሰልክንውንነው፡፡የአጀማመሩታሪክሲታይየሙሽራውን
ሚዜዎችተመሳሳይልብስእንዲለብሱበማድረግከሌላውሰርገኛለመለየትስራላይየዋለነው፡፡
ቀስበቀስምህዳሩንበማስፋትየሙሽራውናየሙሽራዋቤተዘመድ፣ወዳጆችናቅርበትያላቸው
ሰዎችሁሉየሰርግአለባበስስርአትእስከመሆንደረሰ፡፡ይህስርአትህፃናትንምያካተተመሆኑ፣
ምንያህልከፍተኛትኩረትየተሰጠውለመሆኑአንድጥሩማስረጃነው፡፡
"ተመሳሰሉ"ወይም"እንመሳሰል"በመባልየሚቆላመጠውይህየአለባበስስርአት፣ገደብ
ከማጣቱየተነሳየሰርጉእለትተመሳሳይአዲስልብስከመልበስአልፎ፣በዋዜማውናበሰርጉቀን
ማግስት(የመልሱእለት)ጭምርሌላአይነትአዲስልብስመልበስንከጨመረቆይቷል፡፡
ሌላውአስገራሚነገር፣የሙሽራውናየሙሽራዋቤተዘመዶች፣ወዳጆችናቅርበትያላቸው
ሰዎችለመመሳሰልየሚያሰፉትወይምየሚገዙትልብስእንዳይመሳሰልየሚደረገውጥንቃቄ
ነው፡፡ባጋጣሚወንዶችወይሴቶችወይምደግሞህፃናትተመሳሳይቀለምያለውልብስለብሰው
እንዳይታዩ፣ሊያሰፉወይምሊገዙስላሰቡትልብስየሁለቱተጋቢወገኖችመረጃይለዋወጣሉ፡፡
ይህምድርጊትከፍተኛትኩረትየተሰጠውመሆኑንየሚያሳይነው፡፡
"የልብስማች"የፈጠረውችግርምንድነው?
ችግርአንድ፡-የአመጣጡንመሰረትስናይከሌላእምነትተከታዮችየተቀዳነው፡፡የሌላእምነት
ተከታዮችስርአትናደንብአድርገውየያዙትንነገርእየኮረጁመከተልናመመሳሰልበኢስላም
የተወገዘነው፡፡የአሏህመልእክተኛﷺ"ህዝቦችንየተመሳሰለከእነሱነው"ብለዋል፡፡
(አህመድ፡5114,አቡዳውድ፡4031,ሐዲሱንአልባኒሶሂህብለውታል“ሶሂህአልጃሚዕ፡6149)
2/16
Slide 4
ከዚህንመሰልድርጊትራሳችንንለማራቅይህሀዲስከበቂበላይነው፡፡
ችግርሁለት፡-"ተመሳሰሉ"የሚልመልእክትከሰራጊዎቹየደረሳቸውቤተዘመዶችናወዳጆች
የግዳቸውንአዲስልብስማሰፋትወይምመግዛትአለባቸው-ለዚያውም3የተለያየአይነት፤
ለሰርጉዋዜማ፣ለሰርጉእለትናለመልሱ፡፡እዚህላይያለውችግርእነዚህበልብስየመመሳሰል
እዳየተጣለባቸውሰዎችያለፍላጎታቸውልብስማሰፋታቸውወይምመግዛታቸውብቻሳይሆን፣
ነገሩአቅማቸውንግምትውስጥያላስገባከመሆኑጭምርነው፡፡ደህናየኢኮኖሚአቅምየሌላቸው
ሰዎች፣የግዳቸውንተጨናንቀውያሰፋሉወይምይገዛሉ፡፡በቂአቅምየሌላቸውሰዎች፣ዳሪዎቹን
"ይከፋቸዋል"ወይም"ይቀየሙብኛል"በማለትበይሉኝታወይምደግሞ"ከማንአንሼ"
በማለትተመሳስለውለመልበስሲሉየግዳቸውንብድርውስጥይገባሉ፡፡ከዚህ"ተመሳሰሉ"
ከሚባልዘመቻየሚድነውየለየለትድሀብቻነው፡፡(ሲጀመርማንነግሮት?)
ደህናየኢኮኖሚአቅምበሌላቸውሰዎችላይየሚያሳድረውተፅእኖከላይየተጠቀሱት
(አንዱተጨናንቆ፣ሌላውተበድሮየመግዛቱናየማሰፋቱጉዳይ)ብቻአይደለም፡፡"የልብስ
ማች"የሚባልፈሊጥበሁለትመንገድየእነዚህንቤተሰቦችጎጆመነቅነቁአይቀርም-የአነቃነቁ
ደረጃእንደየሁኔታውቢለያይም፡፡በአንድበኩልበባልናበሚስትመካከል"እንመሳሰልወይስ
አንመሳሰል?ካልተመሳሰልንቅርይላቸዋል…በምንአቅማችንእንመሳሰል?"፣ወዘተ.የሚል
ንትርክይነሳል፡፡የልብሱጥራትናዋጋውሳይቀርማጨቃጨቁአይቀሬነው…በሌላበኩል
የመመሳሰልልብሶችያስከተሉትየኢኮኖሚጠባሳእስከሚድንድረስየቤተሰቡገቢናወጪእንደ
ተዛባይቆያል፡፡
በሌላአነጋገርአንድሰውልጁንሲድር፣በዙሪያውያሉሰዎች(ቤተዘመዶችናወዳጆች)
ላልተፈገወጭይዳረጋሉ-አቶአባዋራለራሱ፣ለባለቤቱናለልጆቹጭምርሶስትአይነትልብስ
ማሰፋትወይምመግዛትአለበት፡፡"አንዱሊያገባ፣ሌላውገገባ"የሚለውአባባል
አይገልፀውም፡፡
3/16
Slide 5
ችግርሶስት፡-"የልብስማች"አቅማቸውመለስተኛሆኖልጃቸውንለሚድሩወላጆችምከሰርጉ
ድግስበተጨማሪሌላጫናይፈጥራል፡፡
ችግርአራት፡-"የልብስማች"እሚባልየጃህልያፈሊጥጅልባብናአባያንያስወልቃል፡፡ለአሏህ
ብለውጅልባብናአባያየሚለብሱእህቶቻችን፣የልብስ"ማች"ን(የጃህልያስርአትን)
ለማክበርሲሉ፤ቡራቡሬውንም፣ከሰውአይንየሚገባውንምጨርቅበማሰፋትውር-ውር፣ሽር-
ጉድሲሉይውላሉ፤ይከርማሉ፡፡
እርግጥነውአንዳንድባለሀብቶች"ስፖንሰር"በሚልስም"የመመሳሰል"ንወጭ
ይሸፍናሉ፡፡በአቅምማነስምክንያትለሚጨናነቁትናብድርውስጥለሚገቡትሰዎችእፎይታን
ይሰጣል፡፡ሆኖምባለሀብቶቹየሚያለብሱትባሀብቱንጭምርሲሆን፣እስከሚሊየንየሚደርስብር
የሚያወጡእንዳሉሁሉይነገራል፡፡
እዚህላይያለውችግርበቂልብስያለውንባለሀብቱንማልበሳቸውብቻሳይሆን፣ሲጀመርስ
የጃህልያስርአትለፈጠረው"የልብስማች"ለሚባልፈሊጥታዥበመሆን፣ለምንገንዘብ
ያባካናሉ?ስንትናስንትየሚቀይረውልብስ፣የሚያነጥፈውአንሶላ፣የሚደርበውብርድልብስ
የሌለውናየታረዘ፣ስንትናስንትሚስኪንባለበትአገርተቀምጠው፤ስንትናስንትሙስሊሞች
ከሞቀቤታቸውተፈናቅለውድንኳንተጠልለውባለበትአገርተቀምጠውለምንይሆንይሄን
የሚሰሩት?ድህነት፣ጦርነት፣መፈናቀልናርሀብበሙስሊሙህብረተሰብላይያስከተለውና
እያስከተለያለውንውስብስብችግርአያውቁትምን?በዚህበኩልመልካምስራበመስራት
የአኼራንስንቅማዘጋጀትሊወዳደሩበትየሚገባመሆኑንለምንይሆንየዘነጉት?
4/16
Slide 6
ኮተት2
የተጋነነጥሎሽ
ሸሪዓችንበመኸርላይገደብአልጣለም፡፡ሆኖምየተካበደእንዳይሆንይገፋፋል፡፡
መልእክተኛውﷺ"በጣምጥሩውጋብቻበጣምቀላልየተደረገውነው"ይሉናል፡፡(ኢብኑ
ሒባንፊስሶሂህ፡4072,ሐዲሱንአልባኒሶሂህብለውታል“ሶሂህአልጃሚዕ፡3300)
ይህየሚያስተምረንሁሉምአቅሙንመሰረትባደረገመንገድመክፈልእንዳለበትነው፡፡
አሁን፣በተለይጥሎሽንበተመለከተተግባራዊእየተደረገያለውግንየዚህተቃራኒነው፡፡
ለምሳሌበባህርዳርከተማበጥሎሽመልክለሴቷየሚገዛውወርቅናልዩልዩአልባሳትእስከ
መቶሺህመድረሱይሰማል፡፡እዚህላይያለውጥያቄ"ዝቅተኛገቢያለውሰውእንዴትማግባት
ይችላል?"የሚለውነው፡፡መቶወይምሁለትመቶሺህብርወረት(ካፒታል)ያለውሰው
ወይምወጣት፣ከዚህውስጥአስርወይምሀያሺህብርእንኳንለጥሎሽቢሰጥእንዴትነው
የነገውትዳርዘላቂየሚሆነው?በዚህላይሌላውየሰርጉወጭ(አቶየልብስ"ማች"ን፣ግጥ-
ግጥንጨምሮ)ሲታሰብ፣አብዛኛውወጣት፣"የእምነትግማሽነው"(ሐዲሱንአልባኒ
ሐሰኑንሊገይሪሂብለውታል“አስሶሂህ፡625)
ተብሎበሀዲስየተነገረንንትዳርቢሸሽወይምእጅግቢያዘገየውበማንነውየሚፈረደው?
የጥሎሽማጋነንበትዳርላይየሚፈጥረውንአሉታዊተፅእኖበተመለከተኸሊፋው
ኡመር አንድሰውበሚያገባትሴትላይቂምእስኪሚይዝድረስጥሎሽመጨመርጥሩ
አለመሆኑንበማመላከት፣ከጋብቻበኋላ"ያለኝንሁሉአስከፍለሽብዙችግርፈጠርሽብኝ"
እንደሚላትመናገራቸውንኢብኑማጃህዘግበዋል፡፡
5/16
Slide 7
ኮተት3
ልክያጣድግስ
ጋብቻይፋመሆንአለበት፡፡ይፋሲሆንደግሞሰዎችንበመጋበዝ፣ደስታንበመግለፅጭምርነው፡፡
መልእክተኛውﷺ"በአንድበግእንኳንምቢሆንግብዣአድርጉ"(ቡኻሪ፡6082,ሙስሊም፡
1427)
ብለውአዘውናል፡፡አሁንችግሩ፣ሶስትናአራትበግሳይሆንአንድበሬምአልበቃማለቱነው-
ያለምንምጥርጥርአንድበሬበመቶዎችየሚቆጠሩሰዎችንማስተናገድየሚችልቢሆንም፡፡
የተሻለሀብትያላቸውሰዎችመቶዎችንሳይሆንብዙመቶዎችንወይምሺዎችንሰርግ
ለመጥራትበማቀድ፣ሁለትወይምሶስትበሬዎችንሳይሆንአምስትናስድስት፣እስከአስርና
ከዚያምበላይበሬዎችንያርዳሉ፡፡ባጭሩ"ሀብትአለን"የሚሉሰዎች፣በሰርግ"መወዳደር
ጀምረዋል"ማለትየተሻለነው፡፡
በሰርግላይየተያዘውፉክክር፣ቢያንስሶስትችግሮችንበማስከተልላይነው፡፡ብክነትአንዱ
ነው፡፡አሏህሀብትንሰጥቶናልማለት፣እንደፈለግንእንድናውለውፈቅዶልናልማለትአይደለም፡፡
በተከበረውቁርአኑእንዲህይለናል፡-
﴿
َ
م
َ
دآ ِنِ
َ
ب
َ
يَ
َ
ي
ِ
فِر
ْ
س
ُ
مْلا �ب
ِ
ُيُ َلا
ُ
ه�نِإ ْاوُفِر
ْ
سُت َلا
َ
و ْاو
ُ
ب
َ
رْشا
َ
و ْاوُلُكو﴾
"የአዳምልጆችሆይ!…ብሉም፤ጠጡም፤አታባክኑም-እርሱአባካኞችን
አይወድምና፡፡"አልአዕራፍ፣
ሼህኡሰይሚንእንዲህይላሉ፡-"ውድጥሎሽናከመጠንበላይየሠርግድግስማድረግከሸሪዓ
ጋርየሚቃረኑነገሮችናቸው።በጣምየተባረከጋብቻበተመጣጣኝወጭየሚደረገውነው፤
ወጪዎቹባነሱቁጥርበረከቱይበዛል።"
አላስፈላጊፉክክርናቅናትበሌሎችላይመፍጠሩሁለተኛውችግርነው፡፡መጠነኛሀብትያላቸው
6/16
Slide 8
ሰዎች፣"ከማንአንሼ"በማለትፉክክርውስጥእንዲገቡናየማይችሉትደግሞቅናት
እንዲያድርባቸውያደርጋል፡፡በዚህበኩልብዙውንጊዜየሴቶችድርሻከፍተኛመሆኑንሼህ
ዑሰይሚንይናገራሉ-"የእነእከሌየሰርግድግስእንዲህ፣እንዲህነበር"በማለትበባሎቻቸው
ላይከፍተኛጫናንይፈጥራሉ፡፡በዚህጊዜ"ከሰውላለማነስ"በሚልኋላቀርአስተሳሰብ፣
የኢኮኖሚአቅምንበሚያደቅሁኔታ፣ብድርበመግባትጭምርባለአነስተኛአቅሞችከፍተኛ
ድግስውስጥይገባሉ፡፡በጎችንሳይሆንበሬዎችንያርዳሉ፡፡አንድበሬአርዶሰርግመደገስ፣
የድህነትመገለጫተደርጎሳይታይየቀረአይመስልም፡፡
ሶስተኛውችግር፣ከልክበላይየተዘጋጀውድግስእንዲብበላበማሰብጭምር፣ከልክበላይየሆነ
ሰውስለሚጠራ፣የሰርጉክንውንከቁጥጥርውጭየመሆንእድሉሰፊይሆናል፡፡በዚህምየተነሳ
ልቅየሆነየወንድናየሴትቅልቅልያለጥርጥርይከሰታል፡፡ይህብቻአይደለም፡፡የጃህልያው
(የድንቁርናው)ስርዓትአባዜያልለቀቃቸውሰዎችትርምሱንእንደመልካምአጋጣሚ
በመጠቀምቴፕ/ብሉቱዝአስርገውበማስገባትወይምሞባይላቸውንበመጠቀምዘፈን
ይከፍታሉ፡፡ሰዎችንሰብሰብአድርገውዘፈኑንናድለቃውንያቀልጡታል፡፡አዝማሪዎችምወደ
ሰርጉዳስበመምጣትካልዘፈንብለውእስከማስቸገርሊደርሱይችላሉ፡፡
ይህሁሉከምንየመጣነው?ከተጋነነናልክካጣየሰርግድግስ!ሀብትያላቸው
ሙስሊሞች"አምስትበሬዎችአረደ፤አስርፍሪዳጣለ፤አገሩንአበላው"ወዘተ.ከሚል
የአንድሰሞንየጆሮቀለብከሆነወሬብዙምለማይዘልየሰርግድግስገንዘባቸውንከመከስከስ፣
ምናለየውዱእውሀለሚቸገሩመስጂዶችየጉድጓድውሀቢያስወጡበት?ምንአለመስጊዶችን
ቢያድሱበት፣መርከዞችንቢደጉሙበት?በከተማናበገጠርአካባቢዎችበኑሮውድነትአለንጋ
እየተገረፉላሉየሱናኡስታዞችናሸሆችየወርደመወዝበመቁረጥቢደጉሙበት?…ምናለአሏህ
የሰጣቸውንሀብትለአሏህበማበደርየአኼራአገራቸውንቢገዙበት?የተከበረውቁርአን
ሙእሚኖችንእንዲህበማለትይመክራል፤ያበረታታል፡-
7/16
Slide 9
﴿
َ
عْضَأ
ُ
هَل
ُ
هَف
ِ
عاَض
ُ
يَ ف اًن
َ
س
َ
ح ا
ً
ض
ْ
رَ ق
َ
للّا
ُ
ضِرْق
ُ
ي ي
ِ
ذ�لا اَذ ن�م
ْ
يَلِإ
َ
و ُط
ُ
س
ْ
ب
َ
ي
َ
و
ُ
ضِبْق
َ
ي
ُ
للّا
َ
و ًة
َ
ير
ِ
ثَك اًفا
ِ
ه َنو
ُ
ع
َ
ج
ْ
رُ ت﴾
"ያለአሏህመልካምብድርንየሚያበድር(በአሏህመንገድገንዘብየሚያወጣ)
እና(አሏህ)ለእርሱብዙእጥፎችአድርጎየሚያነባብርለትማነው?አሏህም
(ሲሳይን)ያጠብባል፤ያሰፋልም፤ወደእርሱምትመለሳላችሁ፡፡"አልበቀራህ፣
8/16
Slide 10
ኮተት4
"ፖስታው"
የሙሽራይቱ"ክብረንፅህናተገኘ፤አልተገኘ?"የሚለውጭቅጭቅሌላውየጃሂልያስርአት
መገለጫመሆኑይታወቃል፡፡በተለይትንሽቀደምባለውጊዜ፣"ክብረንፅህናአልተገኛትም"
ማለትለትዳሩመፍረስብቻሳይሆን፣ለሙሸራይቱናለሙሽራውቤተሰቦችጥልናጥላቻ፣ከዚያም
አልፎበአንዳንድአካባቢዎች"ልጂቱንእከሌነውያባለጋት"በሚልመነሻእስከደምመፋሰስ
የሚያደርስየአምባጓሮመናኻሪያሆኖመኖሩይታወቃል፡፡"ክብረንፅህናተገኛት"ማለትደግሞ
እስከልጂቷቤትበመሄድ፣"አሳየውየደሙንሸማ…"እየተባለጭፈራየሚካሄድበትናገንዘብ
የሚሰበሰብበት"ቢዝነስ"ይሆናል፡፡
ወደኋላላይከተማናትምህርትቤትእየተስፋፋሲመጣ፣ልቅነቱምበዚያውልክሲጨምር
"ክብረንፅህናአልተገኛትም"በማለትጭቅጭቅውስጥላለመግባት፣ሆኖምደግሞከዚህ
ከበሰበሰየጃሂልያየባህልማነቆላለመውጣት፣የከተማኋላቀሮች(በነሱቤትጩልሌሆነው
ሞተውነው)አንዲትዘዴቀየሱ-ክብረንፅህናተገኘምአልተገኘምዶሮአርደውምሆነ
ጣታቸውንበምላጭበመብጣትደሙንሻሽጨርቅላይበመቀባትእየጨፈሩገንዘብመቀበል፡፡
ይሄቆሻሻየጃሂሊያስርአትበአሊሞችናኡስታዞችሲወገዝጊዜ፣በብዙከተሞችአካባቢ
ለተወሰነጊዜድምፁንአጥፍቶቆየ፡፡ከጥቂትአመታትወዲህግንጃኬቱንቀይሮብቅብሏል፡፡
"ሀያእ"የጠፋበት፣ብልግናየነገሰበት"ብርአምባርሰበረልዎ"በባዶፖስታተተክቶይገኛል፤
እናምለሙሽራውናለሙሽራዋቤተሰቦችናቤተዘመዶችበመልሱእለትባዶፖስታ
ይታደላቸዋል፡፡"የብርአምባርሰበረልዎውንብርከፖስታውውስጥእያስገባችሁአምጡነው"
መልእክቱ፡፡ተቀባዮቹምይገባቸዋል፡፡
ባጭሩ"ብርአምባርሰበረልዎ"በማለትበሚደረገውጭፈራ፣እልልታናእስክስታየሚጠየቀው
ብርበድምፅአልባውፖስታተተክቷል፡፡ይህለውጥየቅርፅለውጥነው፡፡ይዘቱ-ማለት"ክብረ
9/16
Slide 11
ንፅህናዋተገኝቷልናገንዘብአምጡ"የሚለውመልእክት-ግንአሁንምአለ፡፡የጃህልያው
የበሰበሰስርአትከነኮተቱናግማቱእንደተጀነነአሁንምአለ፡፡ይህየሆነውደግሞየጃህልያውን
ስርአትብልግናውንከጨዋነት፣ግማቱንከሽቶየሚቆጥሩሰዎችስላሉነው፡፡
10/16
Slide 12
ኮተት5
ሀብታሙ ለሀብታም
በቅርቡከአንድሰርግላይያገኘኋቸውየአንድባለሀብትአባት፣ሰርግለሚደግስሰውፍየልወይም
በሬመስጠትችግርእየፈጠረመሆኑንአጫወቱኝ-በተለይበወረዳአካባቢዎችበሽማግሌ
እስከመካሰስመደረሱንበመጥቀስጭምር፡፡
"እንዴት?"በማለትጠየኳቸው፡፡
"'እሱልጁንሲድርፍየልወስጃለሁ፤እኔስድርግንአላመጣም'በማለትነው"አሉኝ፡፡
"የሚሰጣጡትነገርእንደብድርስለሆነ፣ያልተሰጠውሰውመክሰሱትክልልመሰለኝ"
አልኳቸው፡፡
"እሱማትክክልነው፡፡ግንባልሰጠውምሰውመፍረድያስቸግራል"አሉኝ፡፡
"ለምን?"አልኳቸው፡፡
"የመጀመሪያውሰውሲሰጥየነበረውየአንድሙክትፍየልዋጋዛሬግልገልአይገዛም፡፡ሰው
ሙክትገዝቶመስጠትእየከበደውመጣ፡፡እናምስጦታውአሁንወደብርቢቀየርጥሩነበር"
አሉኝ፡፡(የገንዘብግሽበትያለውንተፅእኖረስተውትከመሰላችሁተሸውዳችኋል፡፡)
ሀብታሙለሀብታምይሰጣል፡፡ለእሱንመሰልሀብታምየሚሰጠውስለቸገረውሳይሆን፣
የ"እከክልኝ፣ልከክልህ"ንመርህበመከተልነው-"ያለውንያለውወደደው፣እያበላውነው
እያጎመደው"እንደሚባለው፡፡ከፍየልናከበግአልፈውበሬሁሉገዝተውየሚሰጡሞልተዋል፡፡
ተቀባዩምደብተርላይእየመዘገበነውየሚቀበል፡፡ለምን?ብድርነዋ!
ከዚያየተሰጡትንአብዛኛውንየእርድእንስሳትለነጋዴያስረክባል(ይሸጣል)፡፡
በመቀጠልየሰጡትሰዎችልጅበዳሩቁጥር፣መዝገቡንእያየተመሳሳዩንየእርድእንስሳገዝቶ
ይሰጣል-ውሀቅዳ፣ውሀመልስ፡፡ባጋጣሚተበዳሪውበአካባቢውከሌለ፣ሌላሰውበማስቸገር
11/16
Slide 13
ገዝቶእንዲሰጥለትያደርጋል…አንዳንዶቹ፣ምናልባትምብዙዎቹሰጪዎችለማንምንእንደ
ሰጡእየመዘገቡሳይዙምአይቀሩ፡፡በአንድሀብታምቤትሁለትአይነትሰነድሊኖርይችላል-
አንድልጅሲድርከሌሎችየተሰጠበት(የተበደረበት)፣ሁለትሌሎችሲድሩየሰጠበት
(ያበደረበት)፡፡አይስራመፍታት!
"የቀበጡእለትሞትአይገኝም"እንዲሉ፣በዚህመንገድሀብታሙለሀብታምያበድራል፡፡
ስንትናስንትአነስተኛወረትያለውሙስሊምወጣትግንእሚያበድረውአጥቶበአነስተኛገቢ
ይሰቃያል፡፡ከዚህየባሰበትደግሞእቃተሸክሞይዞራል፤በሊስትሮነትኑሮውንይገፋል፡፡ለእነዚህና
ለመሰልበሱናላይቀጥላሉወጣቶችየመቋቋሚያገንዘብበሶደቃመልክከመስጠትባይደርሱ
እንኳን፣በበድርመልክቢሰጧቸውየሚያገኙትየአኼራትርፍስንትናስንትበሆነ?ግን
አልሆነም፡፡ሀብታሙ፣ለእሱቢጤሞልቶለተረፈውሀብታምእያበደረነውያለው፡፡
መዝገቡቢጠፋወይበአጋጣሚባለእዳውቢረሳ"ሳያመጣቀረ"በማለትወይደግሞበሀገራችን
ባለውየገንዘብግሽበትመዘዝየሶስትሺህብሩፍየልስድስትናስምነትሺህ፣የሀያሺህብሩበሬ
አርባናሀምሳሺህብርሲገባ፤አነስያለሲያመጣለት"ግልገል"ወይም"ጥጃአምጥቶ
ወረወረልኝ"በማለትአላስፈላጊውዝግብ፣ጭቅጭቅናእሰጥአገባውስጥመግባት፡፡የጃሂሊያ
ኮተትተቆጥሮመችያልቃል?
12/16
Slide 14
ኮተት6
'መዝናኛ' ቦታ
ሙሽራውናአጃቢዎቹሙሽራዋንከያዙበኋላ፣"ለሽርሽር"በማለትወደጋርደን፣
ሆቴሎችናየተለያዩየመዝናኛቦታዎችመሄዳቸውበርከትያሉብልሽቶችንበማስከተልላይ
ይገኛል፡፡አንደኛነገርለመዝናኛቦታውበአስርሺህዎችየሚገመትብርመክፈልግድነው-
የገንዘብብክነት፡፡አጃቢተብዬውይተረማመሳል-የወንደናየሴትቅልቅል፡፡የሶላትሰአትን
ማሳለፍወይምማዘግየት-ሌላክስረት፡፡ወደአንዱቦታገንጠልብለውጫትየሚቅሙ፤
አንዳንዴም፣በተለይየሌላእምነትተከታዮችበአጃቢነትከተጠሩ፣ቢራየሚጠጡምአይጠፉም
-ሌላጥፋት፡፡ፎቶመነሳት፣ቪዲዮመቀረፅሁሉይኖራል-በጥፋትላይጥፋት፡፡
የባህርዳርአህሉሱናጀማአሰርገኞችብዙውንጊዜእንደሚያደርጉት፣ብልሽት
ወደሚበዘበትመዝናኛቦታበመሄድፋንታ፣ሙሽሮችከእነአጃቢዎቻቸውወደመስጊድቢሄዱና
የሽርሽርፕሮግራሙበዳዕዋቢተካስ?ከላይከተጠቀሱትአሏህንከሚያስቆጡወንጀሎችሁሉም
ይጠበቃሉ-ትርፍአንድ፡፡በዳዕዋውመሰረትየአሏህንቃልናየመልእክተኛውንﷺምክር
ይሰማሉ-ትርፍሁለት፡፡ሁሉምበዳዕዋውውስጥእስካሉድረስመላኢካዎችያጅቧቸዋል-
ትርፍሶስት፡፡የዓሱርንምሆነየመግሪብንሶላቶችበወቅታቸውናበጀመዓይሰግዳሉ-ትርፍ
አራት፡፡
በዚህሁሉመካከል፣አጃቢዎቹናሙሽሮቹ-በአሏህፈቃድ-የልብእርካታንናውስጣዊ
መረጋጋትንይቀዳጃሉ፡-
﴿
َ
مْطَت
ِ
للّا ِرْك
ِ
ذِب َلاَأ
ِ
للّا ِرْك
ِ
ذِب م
ُُبُوُلُ ق �ن
ِ
ئ
َ
مْطَت
َ
و ْاوُن
َ
مآ
َ
ني
ِ
ذ�لا
ُ
بوُلُقْلا �ن
ِ
ئ﴾
"(እነሱም)እነዚያያመኑ፣ልቦቻቸውምአሏህንበማውሳትየሚረኩናቸው፡፡
ንቁ!አሏህንበማውሳትልቦችይረካሉ፡፡"አረረዕድ፣
13/16
Slide 15
ኮተት7
ግጥግጥ
ግጥግጥ፣ከመልሱቀንቀጥሎባሉቀናትውስጥየሚከናወንግብዢያነው፡፡አመጣጡን
በተመለከተየሌላእምነትተከታዮች"ትውውቅ"የሚሉትንበመኮረጅእንደሆነይነገራል፡፡
(ከሌላእምነትተከታዮችስርአትጋርመመሳሰልያለውንአደጋከፍሲልአይተናል)፡፡
ግብዢያውከሙሽራውናከሙሽራይቱዳሪዎች(ወላጆችወይምአሳዳጊዎች)ከተጀመረበኋላ፣
በዝምድናበቀረቡቤተሰቦችጭምርበወረፋየሚደገስነው፡፡ለይስሙላያህል"ትውውቅ"ይባል
እንጂ፣በአብዛኛውበሚተዋወቁሰዎቸመካከልየሚካሄድግብዢያነው፡፡በሌላበኩል
በመጀመሪያው፣ግፋቢልበሁለተኛውግጥግጥወቅትየትውውቁነገርየሚጠናቀቅቢሆንም፣
የግጥግጡስርአት(ግብዢያው)ግንይቀጥላል፡፡የኢኮኖሚአቅሙአነስተኛየሆነዳሪምሆነ
ቤተዘመድ"ከማንአንሼ"በማለትምሆነ፣በይሉኝታይደግሳል፡፡እናምግጥግጡመጋጥወይም
መጋጋጥሆኖበትያርፈዋል፡፡
የግጥግጥትክክለኛአላማውከሰርግበኋለበተንዛዛድግስሰውንመጥመድሳይሆን፣
የሁለቱንተጋቢዎችቤተሰብናቤተዘመድማስተዋወቅከሆነ፣የሰርጉንየመልስግብዢያለዚህ
አላማመጠቀምይቻላል፡፡"ሚዜ"ወይም"አጃቢ"በሚልስምከሀምሳናከመቶበላይ
ወጣቶችንእያንጋጉወደሙሽራዋቤትከመሄድ፣የአጃቢዎቹንቁጥርበጣምቀንሶቤተሰቡንና
ቤተዘመዱንይዞበመሄድየትውውቁንአላማማሳካትናግጥግጥንበዚሁመቋጨትይቻላል፡፡
ከአላማአንፃርሲታይ፣ከሰርጉመልስይልቅግጥግጥየተሻለይመስላል፡፡ግጥግጥን
የሚያስወግዘውመንዛዛቱነው፡፡ለመሆኑየመልስአላማውምንድነው?ለሙሽራይቱየተሰጡ
የስጦታእቃዎችንይዞመመለስ?ይሄእንዴትየመልስድግስአላማይሆናል?የጃሂልያወይም
የአሮጌባህልአንዱ"ችሎታው"ይሄነው-አንዴየተለመደከሆነ፣ማንምቢሆን"ለምን?"
ሳይልይተገብረዋል፡፡ሰው-እየጎዳውምጭምር-የባህሉባሪያከመሆንአይመለስም፡፡
14/16
Slide 16
ኮተት8
የጊዜመባከን
እርግጥነው፣ጊዜንበተመለከተየሚከወንየሰርግስርአትየለም፡፡ሆኖምከላይየተጠቀሱት
ኮተታኮተቶችሁሉበጊዜውስጥየሚከወኑስርአቶችናቸውናበዚህሁሉየድንቁርናስርአት
ሰለባነታችንውስጥየሚባክነውንጊዜአስቡት-የትየሌሌነው፡፡
ባብዛኛውሀበሻዎችዘንድጊዜስሌትውስጥአይገባም፡፡አንዳንድሰዎች፣ሀበሾችጊዜ
ሞልቶየተረፋቸውስለሆኑ፣ለጊዜእንደማይጨነቁይናገራሉ፡፡ጊዜየተረፈውሁሉ፣በድህነት
ውስጥነውየሚኖረው፡፡የተንበሻበሸጊዜያለን፣በስራየሚጠምደንባህልስለሌለንነው፡፡ይህ
ቢሆንኖሮ፣በአለምላይየድህነትንደረጃከያዙአገሮችባልተደመርንነበር፡፡ጊዜከአሏህ
የተሰጠታላቅፀጋነውናአሏህ፣የሰውንልጅጊዜውንለምንእንዳዋለውይጠይቀዋል፡፡
15/16
Slide 17
ማጠቃለያ
አዲስየሰርግስራክንውንበባህርዳርከተማበተለይበአህለሱናጀመአአባላትውስጥ
በመከሰትላይይገኛል፡፡በሚያስደንቅሁኔታወንዶችበሊጥማቡካት፣በሊጥማቅጠንናበወጥስራ
ቀጥተኛተሳታፊበመሆንላይይገኛሉ፡፡ይሄየሚያስመሰግንተሳትፎነው-በስራሴቶችንማገዝም
ሆነ፣ባለጉዳይወንድምንመርዳትየዲናችንአካልነው፡፡
ሆኖምየሴትናየወንድቅልቅልእንዳይፈጠርመጠንቀቅያስፈልጋል፡፡በአንዳንድሁኔታይሄ
ሲከሰትእየተስተዋለነው፡፡በሰርግዳስየተለያየነውን፣በሰርጉየድግስዝግጅትእንድንቀላቀል
በማድረግሸይጧንአላማውንለማሳከትእንደማይተኛልንመዘንጋትየለብንም፡፡
የጃሂልያኮተታኮተትእንደፈረስአዛባቢገትቱት-ቢጎትቱትአያልቅም፤ሽታውምእንደ
ድመትጥንብካልራቁትበስተቀርአይለቅም፡፡የጃሂሊያስርአትአላማውህዝብንእስረኛው
አድርጎቀጥቅጦመግዛትነው፡፡ጥበበኛውናሀያሉአሏህእንዲህይላል፡-
﴿
ِ
قو
ُ
ي
ٍ
م
ْ
وَق
ِ
ل ا
ً
مْك
ُ
ح
ِ
للّا
َ
ن
ِ
م
ُ
ن
َ
س
ْ
حَأ
ْ
ن
َ
م
َ
و َنوُغ
ْ
ب
َ
ي
ِ
ة�ي
ِ
ل
ِ
ها
َ
ْلْا
َ
مْك
ُ
حَفَأ َنوُن﴾
"የመሀይምነትን ፍርድይፈልጋሉን?ለሚያረጋግጡም ሰዎችከአሏህ
ይበልጥፍርዱያማረማንነው?"አልማኢዳህ
የጃሂሊያንኮተትሰባብሮ፣አ-ነካክቶመጣልያስፈልጋል፡፡ለዚህደግሞ-አሏህንለፈራ
ሰው-መድሀኒቱአንድናቀላልነው-ወደእስልምናጥቅልልብሎመግባት፡፡ታላቁጌታችን
አሏህበተከበረውቁርአኑእንዲህይላል፡-
﴿ ًة�فآَك ِمْل
ِ
سلا ِفِ ْاوُل
ُ
خْدا ْاوُن
َ
مآ
َ
ني
ِ
ذ�لا ا
َ
ه� يَأ
َ
يَ﴾
"እናንተያመናችሁሆይ!እስልምናውስጥጥቅልልብላችሁግቡ"አልበቀራህ፣
16/16
Tags
Categories
General
Download
Download Slideshow
Get the original presentation file
Quick Actions
Embed
Share
Save
Print
Full
Report
Statistics
Views
6
Slides
18
Age
234 days
Related Slideshows
22
Pray For The Peace Of Jerusalem and You Will Prosper
RodolfoMoralesMarcuc
35 views
26
Don_t_Waste_Your_Life_God.....powerpoint
chalobrido8
38 views
31
VILLASUR_FACTORS_TO_CONSIDER_IN_PLATING_SALAD_10-13.pdf
JaiJai148317
34 views
14
Fertility awareness methods for women in the society
Isaiah47
31 views
35
Chapter 5 Arithmetic Functions Computer Organisation and Architecture
RitikSharma297999
30 views
5
syakira bhasa inggris (1) (1).pptx.......
ourcommunity56
31 views
View More in This Category
Embed Slideshow
Dimensions
Width (px)
Height (px)
Start Page
Which slide to start from (1-18)
Options
Auto-play slides
Show controls
Embed Code
Copy Code
Share Slideshow
Share on Social Media
Share on Facebook
Share on Twitter
Share on LinkedIn
Share via Email
Or copy link
Copy
Report Content
Reason for reporting
*
Select a reason...
Inappropriate content
Copyright violation
Spam or misleading
Offensive or hateful
Privacy violation
Other
Slide number
Leave blank if it applies to the entire slideshow
Additional details
*
Help us understand the problem better