le balemuya ena ameraru yetezegaje silitena sened.pptx

kalebalemayehu1 4 views 49 slides Sep 01, 2025
Slide 1
Slide 1 of 49
Slide 1
1
Slide 2
2
Slide 3
3
Slide 4
4
Slide 5
5
Slide 6
6
Slide 7
7
Slide 8
8
Slide 9
9
Slide 10
10
Slide 11
11
Slide 12
12
Slide 13
13
Slide 14
14
Slide 15
15
Slide 16
16
Slide 17
17
Slide 18
18
Slide 19
19
Slide 20
20
Slide 21
21
Slide 22
22
Slide 23
23
Slide 24
24
Slide 25
25
Slide 26
26
Slide 27
27
Slide 28
28
Slide 29
29
Slide 30
30
Slide 31
31
Slide 32
32
Slide 33
33
Slide 34
34
Slide 35
35
Slide 36
36
Slide 37
37
Slide 38
38
Slide 39
39
Slide 40
40
Slide 41
41
Slide 42
42
Slide 43
43
Slide 44
44
Slide 45
45
Slide 46
46
Slide 47
47
Slide 48
48
Slide 49
49

About This Presentation

This ppt prepared on new proclamation to give training for employees and revenue collection methade


Slide Content

በአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ የገቢ አሰባሰብ ስልቶችና የትኩረት አቅጣጫ ነሀሴ 2017 ዓ.ም አ/ ምንጭ

የሰነዱ ይዘት ከፍል አንድ ፡- የመደበኛ ታክስ አሰባሰብን በተመለከተ ክፍል ሁለት ፡- የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ አሰባሰብ ክፍል ሶስት ፡- የፈፃሚ ውጤታማነትና የባለ ድርሻ አካላት ቅንጅትና ሚና ክፍል አራት ፡- ማጠቃለያ

መግቢያ ፡- ግብር በመመሪያ እና ደንብን መነሻ በማድረግ ዘጎች ሰርተው ካተረፉት ፡ እንዲሁም የከተማ አገልግሎት ላይ ያሉ የገቡ አማራጮችን በመጠቀም የከተማው ም/ ቤት የክልሉን ደንብ ለማስፈፀም የወጡ የታርፍ ውሳኔዎችን በማፀደቅ ገቢ ይሰብስባል ፡፡ ከዚህም የተነሳ መ/ ቤታችን በ2018 በጀት ዓመት ከመደበኛ ታከስ 2.3 ቢሊዬን ብር እና ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ገቢ 1.2 ቢሊዬን ብር በጥቅሉ 3.5 ቢሊዬን ብር ለመሰብሰብ ዕቅድ ተይዞ ወደ ሥራ ገብታል ፡፡ በመሆኑም ይህንን ዕቅድ ከግብ ደማድረስ ከወትረው በተለዬ ሁኔታ ግብር የሚስበስብበትን ስልትና አማራጮችን ማመላከት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ተዘጋጅ ቷ ል ፡፡

ከፍል አንድ የመደበኛ ገቢ አሰባሰብ ሥራዎች እና እይታ በዚህ በጀት ዓመት ከመደበኛ ገቢ 2.3 ቢሊዬን ብር መሰብሰብ አቅደን ወደ ሥራ ገብተናል ፡፡ ይህ የገቢ ዕቅድ በዋና ዋና የገቢ መደቦች እና ይሄንን ለማሳካት ልንከተላቸው የሚገባን ስልት እና አተያይ እንደሚከተለው ቀርባል ፡፡ ቀጥተኛ ታክስ ዕቅድ 659,889,753 ቀጥተኛ ያልሆነ ታክስ ዕቅድ 1,350,100,247 ታክስ ያልሆኑ ገቢዎች ዕቅድ 220,000,000 የቴምበር ቀረጥ እና ሽያጭ ዕቅድ 70,000,000

1.1 የቀጥተኛ ታክስ ገቢን ለማሳካት መከተል የሚገባን መንገድ ከተማችን ወደ ከተማው የገቡ የክልል ተ ቋ ማት ሥራ ግብር በአግባቡ በመሰብሰብ ( የማረምያ ፣ ጤና ሳይንስ ኮሌትጅ ፣ የአ /ም መ/ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ፣ የሆስፒታሎችን ) ሥራ ግብር በአግባቡ መሰብሰብ በከተማው ውስጥ እየሰሩ ካሉ የንግድ ተ ቋ ማትና ኃላፊነቱ የተወሰ የግል ማህበራት የሥራ ግብር አ ሟ ጦ በመሰብሰብ አድስ የኑሮ ውድነትን ለመ ቋቋም መንግስት ያደረገው የደመወዝ ጭማሪ የፈጠረውን በጎ ጎን በመጠቀም ገቢን መሰብሰብ የሮያልት ገቢን በእግባቡ በመሰብሰብ የሎተሪ ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችን በአግባቡ ገቢ በመሰብሰብ የማህደር ምርመራ ሥራዎችን በስፋት በማከናወን

የቀጠለ ---- 1395/2017 ተሻሽሎ በፀደቀው የገቢ ግብር አዋጅ ላይ መሰረት ወደ ሥራ በመግባት ( ለአብነት -) የዚህ ግብር አዋጅ መሰረታዊ ዓላማዎች ፡- የግብር መሰረቱን ማስፋት የአነስተኛ ግብር ከፋዮች የግብር ጫናን መቀነስ ለግብር ስወራ መንስኤ የሆኑ አሰራሮችን መከላከል ግብር ሳይከፍሉ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገኙትን ግብር ማከፈል ኢንቨስትመንትን ማበረታታት ናቸው ፡- ከዚህ በመነሳት በግብር አሰባሰባችን ላይ ያለውን ፋይዳ እንደሚከተለው መረዳት ይቻላል ፡፡

የቀጠለ ----- ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ከግብር ከ2000 ብር በታች ነፃ የተደረገ መሆኑ የግብር ከፋዮች ደረጃ መሻሻል የደረጃ ለ ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ገቢያቸው ከ 2 ሚሊዬን ብር በታች የደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች ድርጅቶችና ዓመታዊ ገቢያቸው ከ2 ሚሊዬን ብር በላይ የሆኑ ገቢን ስለማጣመር የሂሳብ መዝገብ የሚይዙ ግብር ከፋዮች የተለዩ ገቢ ሰንጠረዥ ውስጥ የሚካተቱ ገቢዎችን ሲያገኝ ተጣምሮ ግብር ይከፍላል ፡፡ አማራጭ አነስተኛ ግብር ሥራ ላይ ማዋል በጥሬ ገንዘብ የሚደረግ ግብይት ላይ ገደብ ስለማስቀመጥ ግብርን አስቀድሞ ስለመክፈል በሰንጠረዥ መ ገቢዎች ማስከፈያ መጣኔ ላይ ማስተካከያ ማድረግ 10-25 በመቶ መሆኑ

1.2 ቀጥተኛ ያልሆኑ ገቢዎችን ለማሳካት መከተል ስለሚገባን መንገድ የዴስክ ኦዲት ሥራዎችን ማጠናከር የግብር ከፋይ ድጋፊና ክትትል ሥራዎችን መሥራት ኃላፊነቱ የተወሰኑ የንግድ ድርጅቶችንም በደረሰኝ ቁጥጥሩ ማካተት ግብር ከፋዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጅ ተጠቃሚ እንድሆን ማድረግ ( የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ) ደረጃ ያደጉ ግለሰቦች ደረሰኝ በጊዜው እንድጠቀሙ ማድረግ የደረሰኝ ቁጥጥርን ስልታዊ በሆነ መልኩ መምራት

የቀጠለ ----- 1.2.1 የደረሰኝ ቁጥጥር ስለሚደረግብት መንገድ የትርፍ ህዳግን ማስላት የዴስክ ኦዲት ሥራዎችን ማጠናከር ደረሰኙ የተቆረጠበት ቀንና ሰዓትን ማጣራት የተጫኑ ጭነቶች ሁሉ ደረሰኝ ላይ እንደሰፈሩ ማረጋገጥ የአሳቻ እና የምሽት ቁጥጥሮችን ማጠናከር የኦፕሬሽን ሥራዎችን ማካሄድ የተቆጣጣሪዎችን ደንነት መፈተሸና ማረም የከተማውን አንድ ትዕዛዝ አንድ ደረሰኝ ሥርዓት ማስቀጠል ህጋዊ እና አስተዳደሪያዊ እርምጃ መውሰድ

የቀጠለ ---- 1 . የግብር ከፋይ ደረጃዎች የደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች ፡ - ሽያጭያቸው 2 ሚሊዬን እና ከዚያ በላይ የሆኑ የደረጃ ለ ግብር ከፋዮች ፡- አመታዊ ሽያጭያቸው ከ2 ሚሊዬን ብር በታች የሆኑ 2. ከ መቀጠር የሚገኝ ገቢ ከ2000 ብር በታች ያሉ ደመወዝተኞች ከታክስ ነፃ እንዲሆኑ ተደር ጋ ል ፡፡ 3.

1.3 ታክስ ያልሆኑ ገቢዎችን ለማሳካት መከተል ስለሚገባን መንገድ የድጋፍና ክትትልን ማስፋት ጠቅላለ የገቢ አማራጮች እንድ መዘገቡ ማድረግ አገልግሎት አሰጣጥን በማስፋት ተፈላጊነትን በመጨመር የተሻለ ገቢ እንድገኝ ማድረግ የአገልግሎት ክፍያዎች ታሪፍ ከፍ በማድረግ የተሻለ ገቢ መሰብሰብ

1.4 የቴምበር ቀረጥ እና ሽያጭ ገቢዎች ለማሳካት መከተል ስለሚገባን መንገድ የቴምበር ሽያጭ በሙላት መፈጸም የቴምበር ቀረጥ አዋጅን በአግባቡ መጠቀም ፤ ለዚህም ከተማው ራሱን መቻሉ በፍትህ መምሪያ ከውልና ማስረጃ ከማጸደቅ ጋር የተያያዙ ሥራዎች ከአገልግሎት ክፍያ በተጨማሪም የቴምበር ቀረጥ አዋጅ መሰረት መፈፀም ለአብነትም -

ክፍል ሁለት የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ አስባሰብ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ለመሰብሰብ የከተማችን ህዝብ ም/ ቤት የተለያዩ አምስት መመሪያዎችን በማውጣት ወደ ሥራ መገባቱ ይታወቃል ፡፡ ይህ በእንድህ እንዳለ የከተማችን ደረጃ ማደጉ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ በ2018 ዓ.ም 1.2 ቢሊዬን ብር ለመሰብሰብ በ48 የገቢ ኮዶች ላይ እንድት እና ከማን በምን አይነት መንገድ መሰብሰብ እንዳለበት ማሳየት በማስፈለጉ ከታች እንደሚከተለው ቀር ቧ ል ፡፡

2.1 የህንፃ ግብር -1701 በበላፈው አመት መረጃቸው ከተሰበሰበ በኃላ የተገነቡ ህንፃዎችን መረጃ በአግባቡ በመውሰድ ምንም እንካን የመረጃ አሰባሰብ ክፍተት ያለባቸው እንደ ኖክ ሳይት ያሉ አከባቢዎችን በማጥራትን ከፍ ያከ ገቢ በመሰብሰብ በማሰፋፊያ አከባቢ ያሉ በነባርም በህገ ወጥ ተመዝገብው ያሉ ነዋሪዎች በቁርጥ የህንፃ ግብር እንድከፍሉ በማድረግ ዝቅተኛ መነሻ ከ500 ብር ቢሆን በ32000 ነዋሪዎችን ቢናካትት ተጨማሪ 16 ሚሊዬን ብር ገቢ ማግኘት እንችላለን ፡፡

2.2 አሹራ ከመስጠት 1702 ይህ የገቢ አማራጭ በስመ ንብረት ዝውውር ተከተትሎ የሚሰበሰብ የገቢ አማራጭ ሲሆን በዚህን ጊዜ የቴምበር ቀረጥ 1292 የሽያጭ ታክስ 1293 የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር 1168 እና የሊዝ ቅድሜ ክፍያ እንደዬ አግባብነታቸው እየተሰሉ በአንድነት ክፍያ ይፈፀማል ከዚህ ዘርፍ ከ54 ሚሊዬን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ግብ ሰንጥል በሁሉም ቀበሌያት ደረጃ ገቢ እንደምሰበሰብ በማሳዬት ነው ፡- ይህንን ለማሳካት የክልሉ ፍትህ ቢሮ የምሰጡ ውክልናዎች ሀብቱ ባለበት አከባቢ እንድሆን የሚያደርግ ሰርኩላር እንድያፈጥን በማድረግ ከከተማ እውቅና ዉጪ ውክልና ያገኙትን በአስገዳጅ ሁኔታ በማገድ እና ወደ ስም ዝውውር እንድመጡ በማድረግ እንዲሁም በየአከባቢው የተሸጡ ቤቶች ወደ ስም ዝውውር እንድመጡ ማድረግ በማስፋፊያ አከባቢ ያሉ እና ከፋተኛ ቁጥር ያላቸው የስም ዝውውር የሚያስፈልጋቸውን በጥንቃቄ በማዞር

የመዝናኛ ገቢን በተመለከተ 1703 ከ500 ብር በላይ ገቢ ያላቸው አልጋ ቤቶች ደረሰኝ አሳትመው ከኪራያቸው ላይ 4 በመቶ ገቢ እየሰበሰቡ እንድያቀርቡ በማድረግ ከዚህ የተነሳ በከተማችን የሚገኙ ግብር ከፋዮች አልጋ በሚያከራዩበት ጊዜ በመመሪያው መሰረት ከደንበኞች የተሰበሰበ ገቢን በየወሩ እያሳወቁ የሚከፍሉበት አግባብ ማመቻቸት

የነባር የቦታ ኪራይ ገቢ 1721 የነባር ቦታ ግብር ከፋዮች ወደ ሊዝ ስሪት ያልገቡ በከተማ ነባር ቦታ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተሰጠ የከተማ ግብርና ይዞታዎች ክፍያን በአግባቡ መቀበል የግብርና ኢንቨስትመንት የቦታ ኪራዮችን በአግባቡ በመሰብሰብ ውዝፍ ክፍያዎችን አ ሟ ጦ በመሰብሰብ ከመ / ቤቱ ውጪ የፊት አመራሩን ውሳኔ ድጋፍ የሚፈልጉ ጉሳዮች ላይ መግባባት ላይ በመድረስ ወ.ዘ.ተ

1722፣ 1723 ፣1724 እና 1725 ገቢዎችን በተመለከተ ውል እድሳትን ተከትሎ የዕድሳት ክፍያዎችን በአግባቡ መሰብሰብ ተከራዮች በመመሪያው መሰረት በተገቢው ሁኔታ መሰብሰብ የሼቻ ገቢያን ደረጃን በማሳደግ ክፍት ቦታዎች መደብ እንድያገኙ በማድረግ ተጨማሪ ገቢ በመሰብሰብ የገቢያ መደብ የለላቸው እና ጉልት ከምመስሉ ገቢያዎች በመመሪያው መሰረት ገቢ መሰብሰብ ( ሁሉም ቀበሌያት ) ከማህበራት ጋር ተያይዞ የማምረቻ እና የመሸጫ ቦታዎች ኪራይን በተገቢው ሁኔታ መሰብሰብ የዶሮ ነጋዴዎችን መመዝገብ በየወሩ 300 ብር ማስከፈል

1726 የበረት ኪራይ እና 1728 የተሸከርካሪ ኪራይ የበረት ኪራይን በተመለከት ይዞታውን ማጽናትና ማጠናከር ከበረት ውጪ ግብይት ስፈፀንም እርምጃ መውሰድ የከተማው ተሸከርካሪ ያለገበድ ማከራዬት አገልግሎቱን ሰፋ በማድረግ ወደ ኢንተርፕራይ ማሳደግ

ሊዝ ክፍያዎችን በተመለከተ - 1731 በዚህ የገቢ አማራጭ ማንኛው ይዞታ ወደ ሊዝ ስሪት የገባ ሁሉ የሚሰበሰብበት ነው ለአብነትም የጨረታ ሊዝ ኢንቨስትመንት መነሻ ሊዝ ህገ ወጥ ሊዝ ፡- ይህ ክፍያ ስፈፀም በዘገየበት ወለድ የወቅቱን የባንክ የማበደሪያ መጣኔ መነሻ ተደረጎ የሚወሰንና የመክፈያው ጊዜ ስያልፍ 3 በመቶ ቅጣት ይከፍላል ፡፡ በዚህ ሂደት የይዞታ ቆጠራ አስፈላጊ የሚሆንባቸው ሁኔታዎች ይስተዋላሉ ውዝፍም በይበልጥ ከሚገኝባቸው የማዘጋጃ ቤታዊ ክፍያዎች አንዱና ዋነኛው ነው የምሰጡ የክፍያ ደብዳቤዎችም ቢሆኑ ቀጣይ እርምጃ ለመውሰድ የሚረዱ መሆን አለባቸው

የድጋፍ ገቢዎች 1732-1734 በሁሉም ቀበሌያት ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በመለየት ደብዳቤ በማድረስ ለከተማው ልማት ያልተገደብ ድጋፍ እንድያደርጉ በማድረግ ደረሰኝ መስጠት ግለሰቦችን በተለያዩ ማህበራዊ መሰረታቸው አማካይነት የከተማ አስተዳደሩ በሚያከናውናቸው መሰረተ ልማቶች ላይ በይበልጥ ተሳትፎ እንድያደርጉ ማደረግ እና ተሳትፎያቸውን በተገቢው ሁኔታ መመዝገብ ( ለስቴዲየም ፣ ለማህበራዊ ተቃማት ግንባታ እና ማስፋፊያ አከባቢዎችን ላይ መሰረተ ልማቶችን ለማድረስ ወ.ዘ.ተ ) በህብረተሰብ ደረጃ የሚደረጉ ድጋፎችን በማስተባበር የመተግበር እና ማስተዳደር ( የተለዩ ልማቶች ለተለዩ ቡድኖች በመስጠት )

የንግድና ሙያዊ አገልግሎት ክፍያዎች 1741 አናጽ ፣ ግንበኛ ፣ የባንባ ሰራተኛ እና ቀለም ቀቢዎች ከመነኸሪያ ዉጪ ትራንስፖርት የሚሠጡ ተቃማት ክፍያ የንግድ ድረጅቶች በአመታዊ ጠቅላላ ሽያጫቸው መሰረት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበራት ክፍያዎች ባንኮች እንሹራንሶች የህብረት ሥራ ማህበራት

የግንባታ ፍቃድ 1742 ይህ የገቢ አማራጭ ከተማው ውስጥ የሚገነቡ ግንባታዎች ህጋዊ ቅርጽ እንድኖራቸው በማድረግ ገቢ የሚሰበሰብበት ነው ፡፡ ከዚህ የተነሳ በየመንደሩ የምገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ፍቃድ ስለመኖሩ እና አለመኖሩ መከተታተል እና ማራት ያስፈልጋል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በህገወጥ መልክ ተገንብተው ህጋዊ የሆኑ ይዞታዎች ኤግዝስትንግ የግንባታ ፍፈቃድ እንድያገኙ በማድረግ - የአጥርና ህንፃግንባታ ፍቃድ - የፕላን ስምምነት - የፕላን መገምገምያ ክፍያዎችን ማስከፈል ህገወጥ ስገኝ መቅጣት

የአፈር መድፊያ ፍቃድ 1743 በዚህ የገቢ አማራጭ በመንገድ ላይ የሚቀመጡ የግንባታ ቁሳቁሶች ፣ የአፈርና ፍሳሽ ቆሻሻዎች መድፊያ ቦታ ፣ መንገድ ላይ የሚደረጉ ኩነቶች ክፍያ ያካትታል ፡፡ በመሆኑም በመንገድ ላይ የግንባታ ቁሶሰችን ለማራገፍ በቢያጆ ፍቃድ ለ7 ቀን በተሰጠው ቀን ቁሶችን አንስቶ ባይጨርስ በያዘው ካሬ ልክ በመሰረተ ልማቱ አይነት እየተባዛ በተጨማሪነት ይከፈላል ምንም ፍቃድ ሳይሰጥ በተራገፈ የግንባታ ቁስ ስገኝ ያረፈበት ካሬ በ50 ብር ተባዝቶ ይቀጡ እና ለሚያቆዩበት ጊዜ በመሰረተ ልማት ዓይነት ክፍያ ይፈጽማሉ ከሀዘን ዉጪ መንገድ ላይ ድንካን ለመትከል የአፈር መድፊያ ቦታ ፍቃድ ወ.ዘ.ተ

1744 እና 1745 በተመለከተ የተከለከለ ቦታ ለማለፍ በተቀመጠለት የክፍያ ስታንዳርድ መሰረት የሚፈጸም መሆኑ የትራፍክ ቅጣትን በተመለከተ ከመደበኛው የትራፍክ ቅጣት በተጨማሪ በከተማ አስተዳደሩ በወጡ መተግበር ባለባቸው ( የግንባታ ቁሶችን ሸራ ሳይሸፊኑ ማለፍ ) እንዲሁም ትብብር የሚፈልጉ ማለትም የግብር ግዴታቸውን ሳይወጡ የሚያሽከረክሩ ተሸከርካሪዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ ዕቅዶችን ለማሳካት መስራት ያስፈልጋል ፡፡

የደንብ መተላለፍ ቅጣቶች 1746 በመመሪያው መሰረት የተለያዩ የደንብ ጥሰት ክፍያዎች ይመዘገባሉ ቅጣትና ወለድም በዚህ የገቢ ርዕስ ይሚመዘገቡ ይሆናል በዚህ ገቢ ርዕስ ስር የሚሰበሰበውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ የመ / ቤቶች ቅንጅት ወሳኝ ነው

የመነኸሪያ አገልግሎት ክፍያ 1747 ይህ ክፍያ በምልልስ የሚከፈል መሆኑ አዳሪ ተሸከርካሪዎች የአዳር ክፍያ እንደሚፈጽሙ የተጠና እና ወደ ሥራ እንደገባ ለመንገድና ትራንስፖርት የተሰጠ ቢሆንም ለመትግበር ፍቃደኛ ያለመሆን ሌሎች በዚህ ዘርፍ የተጠኑ ጥናቶች የአመዘጋገብ ችግር መኖር ተሸከርካሪዎች የግብር ግዴታቸውን መወጣት አለመወጣታቸውን ለማረጋገጥ መቸገር

ለአካባቢ ጥበቃ ክፍያ (1748 ) የተፈጥሮ አካባቢን የሚበክሉ እና ጉዳት የሚያደርሱ የንግድ ስራዎች ለምሳሌ ፤ ሬድ አሽ ማውጣት ፣ ድንጋይ ማውጣት ፣ ድንጋይ መፍጨት እና ሴሌክት ማውጣት የመሳሰሉትን ተሸከሪካሪዎች ጭነው ሲውጡ በጫኑት ሜትር ኩብ ልክ ክፍያ ይፈጸማል ፡፡ ፋብርካዎች / ኢንዳስትሪዎች ሆስፒታሎች ክልንኮች በቁርጥ በዓመት ክፍያ ይፈጸማል

1751 ቆሻሻዎች ከተለያዩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ይመነጫል ፡፡ በመሆኑም የመነጨው ቆሻሻ አከባቢ ላይ አሉታዊ ጫና እንዳያሳድር በተቀናጀ መልኩ ማስወገድ ተገቢ ይሆናል ፡፡ ከዚህ በመነሳት በከተማችን ከግለሰቦች እና ከድርጅቶች የሚመነጨውን ቆሻሻ ወራዊ ቁርጥ ክፍያ በማስቀመጥና እንዲሁም አከባቢን በብናኝ በተለያዩ ቆሻሻዎችን የሚያመነጩ ቁርጥ አመታዊ ክፍያ ተዘጋጅቶላቸዋል ፡፡ በመሆኑም ፡- በልዩ ሁኔታ መታየት ያለባቸው ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ ቆሻሻ በማመንጨት በከተማዋ ጽዳት ላይ ጫና ለሚፈጥሩት (እንደ የጠጠር ማምረቻ )የጂፕሰም ምርት አምራች የመሳሰሉት ) አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ወይም መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች አግሮ ( የዱቄትና የመሳሰሉ ፋቭሪካዎች ) ወፍጮ ቤቶች በቃት በዓመት ብር

የመሐንድስ አገልግሎት ገቢ 1752 ማዘጋጃ ቤቱ የመሐንዲስ አገልግሎት በከተማው በሚከናወኑ ግንባታዎች ፣ የድንበር ግጭት ፣ ይዞታ ይዋሃድልኝ እና ይከፋፈልልኝ እንድሁም ሌሎች በማዘጋጃ ቤቱ ላይ በሚሰጡት የቴክኒክ አገልግሎት ላይ የሚሰበሰብ ገቢ ነው ፡፡ ይህ ክፍያ ሌሎች ክፍያዎች ጋር በጋራ የሚፈጸም ይሆናል ለምሳሌ የማዕዘን ድንጋይ ለማስቀመጥ የተለያዩ የድጋፍ ደብዳቤ ስፃፍ የካዳስተር ካርታ ተዘጋጅቶ ስሰጥ የቦታ ርክብክብ ስደረግ ወ.ዘ.ተ

የህንፃ ጥራትና ቁጥጥር 1753 ማዘጋጃ ቤቱ በከተማው በሚከናወኑ የግንባታ ስራዎች ላይ የግንባታ አፈፃፀሙን መሰረት በማድረግ የግንባታ ቁጥጥርና የመስክ የክትትል በህንፃ ምድብ መሰረት የመሐንድስ አገልግሎት ጋር በጋራ የሚከፈል ክፍያ ነው ፡፡ በዚህን ጊዜ የግንባታ ፍቀድ ሳይሰጥ እየሰሩ ያሉ ይቀጣሉ የህንፃ ጥራትና ደረጃ ላይ በሚታዩ ክፍተቶች በቅጣት እርምት ይደረግባቸዋል በግንባታ ወቅት በለጠፍ የሚባቸው መረጃዎችን በተገቢው ሁኔታ መገኘታቸውን ይረጋገጣል ወ.ዘ.ተ

የዲዛይና ጨረታ ሰነድ ሽያጭ 1754 የማዘጋጃ ቤቱ በሚያዘጋጀው ዲዛይን ለሚከናወን ግንባታ ከጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚሰበሰብ ገቢ ነው ፡፡ በማዘጋጃ ቤት ለሚከናወኑ የተለያዩ ግንባታ ፕሮጀክቶች ጨረታ ሰነድ ሽያጭ ላይ የሚሰበሰብ ገቢ ( በአንድ የጨረታ ሰነድ ላይ ) ለገቢዎች ለባንክ የህፃ ግምት ዋጋ በማሰወጣት ለእርጅና ቅናሽ የህንፃ ግምት አውጡቶ ለምመለከተው ለመላክ ከግንባታ ዋጋው በመቶና በግለሰቡ ፣ በተለያዩ ተቋማት ጥያቄን መነሻ በማድረግ የተገነቡ ግንባታዎች ዋጋን ፕላን ወይም ዲዛይን ጥናት ዋጋ ዝርዝር ( ለፍ / ቤት ፣ ወ.ዘ.ተ

የመንገድ መጠቀሚያ 1756 ይህ ክፍያ የከተማ አስተዳደሩ ባስገነባቸው መሰረተ ልማት ላይ የሚጠቀሙ ተሸከሪካሪዎች በዓመት በቁርጥ እና በምልልስ የሚከፈልበት ስርዓት ነው ፡፡ በተሸከርካሪዉ አይነት እና የመጫን አቅምን መነሻ በማድረግ ተግባራዊ ይደረጋል ፡፡ በዚህ አግባብ ለማስከፈል በሚከድበት ጊዜ የቅንጅት ሥራዎችና የመረጃ ክፍተቶች ፈታኝ ናቸው ፡፡

የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ክፍያ 1759 የከተማው ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ጽ/ ቤት በዚህ ዘርፍ ለሚደረጉ ሥራዎች በአደጋ ወቅት አስከፍሎ አገልግሎት መስጠት የማይቻል መሆኑ ግልጽ ነው ፡፡ ከዚህ የተሳ በዚህ የገቢ ርዕስ ሥር የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግት ግብር በሚከፍልበት ወቅት ነዋሪዎች ከግብራቸው ጋር ተደምሮ የሚከፈል ስሆን አገልግሎቱም ያለ ገደብ መስጠት እና የሰፋ አደጋ ከመከሰቱ በፍት መታደግን አላማ አድርጎ ይከወናል ፡፡ በመሆኑም በከተማችን ማስፋፊያን ጨምሮ 34,000 የመኖሪያ ይዞታዎች ቢኖሩ 3,400,000 ብር ገቢ እና 4,000 የሚሆኑ የንግድ ይዞታዎች ብኖሩ 1.200,000 ብር በጥቅሉ 4.6 ሚሊዬን ብር ከግብር ጋር አብሮ መሰብሰብ ይቻላል ፡፡

የፓርክን አገልግሎት 1769 በከተማው ውስጥ በመንገድ ላይ እና ለዚህ አገልግሎት በተለየ እና በተመረጡ ቦታዎች ተሽከርካሪ የሚያቆም አካል የሚፈጽመው አገልግሎት ክፍያ ነው ፡፡ ይህ ክፍያ በተሽከሪካራች ዓይነት ፣ የመጫን አቅም ከቆይታ ጊዜያቸው ጋር በማጣጣም በቁርጥ የሚከፍል ክፍያ ነው ፡፡ ይህ የክፍያ ሁኔታ በይበልጥ ተመክሮበት ሥርዓት የሚይዝበት ሁኔታ ቢመቻች መልካም ነው ወ.ዘ.ተ

የቦታ ማግኘት ምዝገባ አገልግሎት (1773 ) ማዘጋጃ ቤቱ መሬትን በኢንቨስትመንት ፣ በጨረታ ፣ በምደባ እና በተለያዩ ውሳኔዎች መሬት ለመኖሪያ ፣ ለድርጅት እና ለሌሎች ሲያስተላለፍ ለመመዝገብ የሚፈጸም አገልግሎት ክፍያ ነው ፡፡ ይህ የክፍያ ታሪፍ በመኖሪያ በምደባ -1000 ለድርጅት 1500 ብር ያስከፍላል በመሆኑም የህንን መጣኔ ታሪፍ በማስፋፊያ አከባቢ ብቻ እን ካ ን ያለውን የገቢ አማራጭ ስናይ ከ28 ሚሊዬን ብር በላይ አቅም እንዳላ ያሳያል ሌሎች

፡- የመሬት ይዞታ ካርታ ፣ የቤት ባለቤትነት ደብተር ፣ የካርታ እና ቤት ዕድሳት አገልግሎት ክፍያ መጣኔ ታሪፍ ( ተመን ) 1774 በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ለመኖሪያ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ቤት ለንግድ አገልግሎት ለውጥ ሲያደርግ የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ እንድሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች የተላለፉ ይዞታዎች ካርታ እንድሰጣቸው ስደረግ የሚከፈል ክፍያን ያካትታል ፡፡ በዚህ የማስከፈያ መጣነ የይዞታ ማረጋገጫ ( ካርታ ) አዘጋጅቶ መስጠት ( በሰርተፍኬት ወረቀት ላይ የይዞታው ስዕላዊ መግለጫ ፣ ማህበተም ማድረግ ለማዘጋጀት ይከፈላል ተካቶ ይከፍላል ) በሌላ መልኩ የካዳስተር ሥራዎችን ተከትሎ የሚከፈሉ ክፍያዎች በዚህ የምመዘገቡ ሲሆን በያዝነው በጀት ዓመት ሁሉም ዲጅታል ካርታ እንድያገኝ በማድረግ ከፍተኛ ገቢ መሰብሰብ ያስችላል በተጨማሪም በማስፋፊያ አከባቢዎች ሁሉም ህጋዊ ባለ ይዞታዎች 1000 ሺህ ብር እየከፈሉ እንድያገኙ በማድረግ ከ 30ሚሊዬን ብር በላይ ገቢ ማግኘት ይቻላል

ከእዳ እገዳ ፣ ምዝገባና ስረዛ ፣ የሀራጅ ትዕዛዝ ባለሙያ የመላክ አገልግሎት (1775 ) ከዕዳ እገዳ የድጋፍ ደብዳቤ ለመስጠት የፍርድ ቤት እግድ ማስያዝ እና ማስነሳት በተናጥል በባንክ ፣ ፍርደ ቤት እና በመሳሰሉት ትዕዛዝ የሚደረግ የንብረት ግምት የሀራጅ ትዕዛዝ አገልግሎት ከባንክ የሚመጣ ብድር እግድ ለመመዝገብ ተቆራጭ ገንዘብ ሌሎች -------

የቄራ እርድ አገልግሎት (1777 ) የእንስሳት እርድን በማከናወን የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ መሆኑ በሙሉ አቅሙ እና ብቃቱ ያለመስራቱ ፍዬልና በግ እርድ ያለመጀመራችን ህገ ወጥ እርድ መበራከት ዋነኛ ፈተናዎች ናቸው ከዚህ የተነሳ ማስተካከያ መንገዶች ላይ ዛሬ መክረን አቅጣጫ ማስቀመጥ ይኖርብናል ፡፡

የመጫንና ማራገፍ አገልግሎት (1778 ) አንዳንድ ጊዜ ይህንን የክፍያ ታሪፍ ቀጥታ በየሰፈሩ ከምጭኑና ከሚያራግፉ እንድሁም ከመጫኛ መኪኖች ጋር ያገናኛሉ ነገር ግን የከተማ ልማት ሚንስተር ምከረ ሀሳብን ተከትሎ ይህ ክፍያ ከመንገድ መጠቀሚያ ጋር በመሆን ማንም ይጫን ያራግፍ ፣ የሚራገፈው ዕቃ የከተሞች ንጽህና ላይ ጫና ስለሚያሳድር እሱን ለማጽዳት የከተማ አስተዳደሩ ለሚሰራቸው ሥራዎች ስለሚውል ነው ፡፡

ከሚለጠፍ ፣ ከሚንጠለጠል ፣ ከሚተከል እና በማንኛውም መንገድ ከሚደረግ የማስተዋወቅ ሥራ 1782 የማስታወቂያ ፍቃድ ለመስጠት የውጪ ማስታወቂያ ህጋዊነት ማረጋገጥ ግለሰቦች በግል ይዞታቸው ላይ የሚለጠፍ ፣ የሚንጠለጠል ፣ የሚተከል እንድሁም የሚሰቀል በዓመት በቁርጥ በማንኛውም ቦታ ተለዋወጭ ገጽ ያው ማስታወቂያ ከፍያ በዓመት በቁርጥ ግለሰብ በመንግስት ይዞታዎች ላይ የሚለጠፍ ፣ የሚንጠለጠል ፣ የሚተከል እንድሁም የሚሰቀል በካሬ ሜትሪ በዓመት ድርጅቶች በግለሰብ ይዞታዎች ላይ የራሳቸውን ምርት ስያስተዋዉቁ በካሬ ሜትሪ በዓመት ድርጅቶች በመንግስት ይዞታዎች ላይ የራሳቸውን ምርት ስያስተዋዉቁ በካሬ ሜትሪ በዓመት በከተማ ውስጥ የማስታወቂያ ፓምፕሌቶችን ፣ ስትከር ፣ ፍላየር ፣ መበተን እና መለጠፍ በቀን በተሽከርካሪዎች ላይ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን መጻፍ ፣ መለጠፍ በዓመት በቁርጥ

የቀጠለ ----- በጊዜያዊነት ከሚለጠፈ እና ከተሰቀሉ ማስታወቂያዎች ( በቀን ) በማንኛውም ቦታ በሚተከል በሚስል ፣ በድምጽ በዲጂታል ቴክኖሎጅ የሚታዩ ማስታወቂያ ቁርጥ በዓመት በግርግዳ እና ጣሪያ ላይ የሚሳል ማስታወቂያ በካሬ ሜትሪ በዓመት በማንኛውም ቦታ በሶስት ምስል ማስታወቂያ በካሬ ሜትሪ በዓመት የበረንዳ ጥላ ፣ በፌርማታ ፣ ነዳጅ ማደያ እና ሌሎች መሰል ማስታወቂያዎች በቁርጥ በዓመት የከተማው ግብር ከፋይ ሆኖ በተሸከሪካርዎች ምርትና አገልግሎቶችን እየዞሩ መሸጥ እና ማስተዋወቅ በቀን ከከተማው ግብር ከፋዮች ዉጪ በተሸከሪካሪ ምርትና አገልግሎቶችን ለመሸጥ በብር በቀን በድምጽ ማጉያ መሳሪያ ወይም በድምጽ በካሴት የሚሰራጭ ማስታወቂያ በቀን ቁርጥ

ክፍል ሶስት ፡- የፈፃሚ ውጤታማነትና የባለ ድርሻ አካላት ቅንጅትና የቅንጅት አግባቡ ሚና 3.1 የፈፃሚ ውጤታማነት በገቢ መ/ ቤት የፈፃሚ ውጤታማነት በቀጥታ ከምሰበሰበው ገቢ ጋር ተያያዝ ይሆናል ፡፡ በመሆኑም በ2018 በጀት አመት የአንድ ፈፃሚ ውጤታማ ነው የሚባለው ከ26 ሚሊዬን ብር በላይ ስሰበስብ ነው ፡፡ በሌላ መልክ የሚሰበሰበው ገቢ አስተዳደሪያዊ ወጪ ቆጣቢ መሆኑ መረጋገጥ ይገባዋል ፡፡ በዚህ መሰረት አንድ መቶ ብር ለመሰብሰብ ከ3 ብር በታች የሆኑ ወጪዎችን ማዉጣት ይመከራል ፤፡ በጥቅሉ የፈፃሚን ውጤታማነት ለማሳደግ የሰው ሀብታችን ምርታማነት ወሳኝ ይሆናል ፡፡ ከዚህ የተነሳ ፈፃሚው 8 ሰዓት ሊያሰራ የሚችሉ ስራዎችን ላይ ማሰማራት ቆጥሮ ሰጥቶ ቆጥሮ መቀበል ፣ መመዘን ፣ መሸለምና ፤ ማረምና ማስተማር ማዳበር ወሳኝ ይሆናል ፡፡ በጥቅሉ የመሪነትን ሚና ማጉላት ያስፈልጋል ፡፡

3.2 የባለ ድርሻ አካላት የቅንጅት መስክ ሀ. ግንዛቤ በመፍጠሩ ረገድ እንዳዬነው የሁሉም ነገር ቁልፍ እውቀት መሆኑ አያጠያይቅም ፡፡ ምክንያቱም በአመለካከቱ የተቃና ዜጋ ለልማት አጋር ስለሆነ ፡፡ በመሆኑም ከመረሀ ግብር በዘለለ መልኩ በፓርቲ የምመራ ከቀበሌ እስከ መንደር ተደራሽ የሆኑ የግንዛቤ ፈጠራ እና መግባቢያ ውይይቶች ያስፈልጋሉ ፡፡ ይህም ውይይት ሳይቆራረጥ በጠንካራ ሰዎች መመራት አለበት ፡፡ ርዕሶቹም የወጡ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ታሪፎች አከፋፈል ሁኔታ እና ስልቶች በግብይት ወቅት ደረሰኝ ጠይቆ የመውሰድና ራስን ከሌቦች መከላከል ዙሪያ ደረሰኝ ቁጥጥር አደራረግ ስርዓትና አስፈላጊነት ውዝፍ ግብር አመላለስና ህግ የማስከበር ሥራዎች ህገ ወጥ ግብይት እና ኮንትሮባንድ ቁጥጥር በተመለከተ ወ.ዘ.ተ

የቀጠለ --- ለ. ደረሰኝ ቁጥጥር ላይ መስራት ደረሰኝ ቁጥጥር ለማድረግ ቁርጠኛ እና ንጽህናቸው የተረጋገጡትን በመለየት በልዩ ፓከጅ ሥራዎችን መከወን ሥራዎችን ስልታዊ እና ስትራቴጅክ በሆነ መልኩ መምራት አስተማሪ እርምጃዎችን መውሰድ ሐ. ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ አሰባሰቡ ላይ ያልተገደብ ድጋፍ ማድረግ ያሉ የገቢ አማራጮችን በመለየት በሙላት እነድሰበሰቡ ማድረግና ማረጋገጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን እና የአሰራር ማነቆዎችን ለይቶ እንድፈታ ማድረግ ተጨማሪ የገቢ አማራጮች ላይ መስራት

የቀጠለ --- መ. ህግን የማስከበር ሥራዎች ላይ መሥራት ደንብ የተላለፉትን መቅጣት ከፍትህ መዋቅሮች ጋር በቅርበት መሥራት ህገ ወጥ እና ባለተፈቀደ ቦታ ግብይትን መከላከል በግብር ዕዳ ምክንያትን አካውንት ማገድ ፣ ተመጣጣኝ ንብረት ማስከብር እንዲሁም ሸጦ ዕዳውን መሸፈን በጥቅሉ የታክስ ህግን ማስከበር ያስፈልጋል ፡፡

3.3 የባለ ድረሻ አካላት የቅንጅት አግባብ የባለ ድርሻ አካላት ቅንጅትን ስንመለከት መድረክ ላይ ከምኖር መግባባት በዘለለ በተግባር ልገለጽ ይገባል ፡፡ ይህም ማለት በየተ ቃ ማቱ የሚከወኑ ተግባራት ለግብር አሰባሰቡ ያላቸውን አስተዋጽዎ ማጉላት ሥራዎች ተያያዥና ተመጋጋቢ መሆናቸውን መረዳት እና በሙላት መፈጸም ( ፖሊስ ፣ ንግድና ገቢያ ልማት ፣ ትራንስፖርት ፣ ፍትህ ፣ ኢንተርፕራይዝ ) ችግር ፈች የሆኑ ድጋፍ ማድረግ ቅንጅታዊ ሥራው ያመጣውን ፋይዳ መገምገም ወ.ዘ.ተ

ክፍል አራት ማጠቃለያ በጥቅሉ የገቢ ሥራዎችን በስኬት ለማጠናቀቅ የባለ ድርሻ አካላት ትብብር እና ድጋፍ አስፈላጊ ይሆናል ፡፡ ከዚህ በመነሳት በትብብር የሚሰሩ አካላትም ቢሆን ከተማው ያለውን እምቅ አቅም ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በዕውቀት መከወን አስፈላጊ በመሆኑ እንደዛሬው አይነት መደረኮችን በማስፋት ፤ የራስ ጥረትን በመጨመር መፈጸም እና ዕቅዳችንን ማሳካት ያስፈልጋል ፡፡

አመሰግናለው !!.