SlidePub
Home
Categories
Login
Register
Home
Education
2 DAY 4 time mgt new slids 2 for managers and leaders.pptx
2 DAY 4 time mgt new slids 2 for managers and leaders.pptx
dawityeshiwas1
2 views
72 slides
Sep 24, 2025
Slide
1
of 72
Previous
Next
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
About This Presentation
training materials for leadership
Size:
2.93 MB
Language:
none
Added:
Sep 24, 2025
Slides:
72 pages
Slide Content
Slide 1
ቀን አራት
Slide 2
የጊዜ አጠቃቀም ስራ አመራር
Slide 3
ክለሳ የአገልግሎት አሰጣጥ ዕድገት ( አገልግሎትን አላማ ያደረገ እድገት ፣ ተገልጋይን አላማ ያደረገ እድገት እንዲሁም ጥራትን አላማ ያደረገ እድገት ) የተገልጋይ እርካታ ማሻሻያ ስትራቴጂዎች - ተገልጋይ ተኮር መሆን ፣ ቅሬታን መፍታት ፣ የማስፈፀምና የመፈፀም አቅምን ማሳደግ ፣ የስራ ተነሳሽነትን ማሳደግ የተገልጋይ ቅሬታ ማስተናገጃ ስልቶች - ለተገልጋይ ያለን አመለካከት መለወጥ ፣ ቅሬታዎችን ወድያውኑ ፊት ለፊት ተነጋግሮ መፍታት ፣ የቅሬታ ማስተናገጃ ስልቶችን መዘርጋትና በአግባቡ መተግባር ፣ ቅሬታዎቹን የሚፈቱበት ጠንካራ የክትትልና ግምገማ ስርአት መዘርጋት የተገልጋይ አያያዝ ጥበብ - ቁጡ ተገልጋዮች ፣ ያልረኩ ተገልጋዮች ፣ ግራ የተጋቡ ተገልጋዮች
Slide 4
የጊዜ አመራር ፅንሰ-ሃሳብ ጥያቄና መልስ ከግል ሕይወት ተሞክሯችሁም ሆነ ከምትሰሩት ስራ አኳያ ጊዜ እና የጊዜ አመራር ምንድነው ? ጊዜ ፡ 10 ደቂቃ
Slide 5
ጊዜ እና የጊዜ አመራር ምንነት ጊዜ ምንድን ነው? የሰው ልጅ በዚ ህ ምድር ካለው ሀብቶች ውስጥ ምንም አይነት ልዩነት ሳይኖር ለሁሉም በእኩልነት የተሰጠ ብቸኛ ሀብት ነው፡፡ ይህ ሀብት ከሌሎች ሀብቶች ለየት የሚያደርገው በቁጥጥራችን ስር ባለመሆኑ ምክንያት እንደፈለግን ማ ድረግ አለመቻላችን ነው፡፡ ከቁጥጥራችን ውጭ የሆነውን ይህን ሀብት እንዴት መጠቀም እንችላለን የሚለው ጥያቄ ነው። ይህ ጥያቄ በሌላ በኩል የጊዜ አመራር ክህሎት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያመላክተናል ማለት ነው።
Slide 6
የጊዜ አመራር ምንነት…የቀጠለ በህይወታችን ከሚያስፈልጉን ክህሎቶች መካከል የጊዜ አጠቃቀም ክህሎት አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም በግል ህይወታችንም ሆነ በተሰማራንበት የስራ መስክ ተግባራዊ የምናደርገው እና ለስኬታማነታችን አስተዋፅኦ ካላቸው ጉዳዮች መካከል በአብይነት የሚጠቀስ ጭምር መሆኑን ነው፡፡ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ልናገኘው የምንችለውን ጥቅም ወይም ስኬት በየቀኑ ብቻ ሳይሆን በየደቂቃው የሚኖረን ጊዜ በተገቢው ሁኔታ ስራ ላይ ማዋል ስንችል እንደሆነ ግልፅ ነው።
Slide 7
የቀጠለ … ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም ሲባል አስፈላጊና ጠቃሚ የሆኑ እና ያልሆኑ ሥራዎችን መለየትና ከጠቀሜታቸው አንፃር በቅደም ተከተል ማስቀመጥና መፈፀም ማለት እንደሆነ እንረዳለን። የጊዜ አመራር ሲባል በጊዜ መዘውር ውስጥ ቅድሚያ መስጠት ለሚገባን ቅድሚያ በመስጠት ጊዜን በተገቢው አግባብ መጠቀም ነው።
Slide 8
የቀጠለ … የጊዜ አመራር - ጊዜ አባካኝ የሆኑ ልማድና አሰራሮችን መቀየር ወይም ማውጣት መቻልን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው ። አንድ ሰው ሌሎች ሀብቶችን በሚቆጣጠርበት መንገድ ጊዜን በቀጥታ ሊቆጣጠረው ባይችልም በተዘዋዋሪ ግን ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም መቆጣጠር እንደሚቻል ነው ። ( ሮይ አሌክሳንደር (2009) የጊዜ አመራር እንደሌሎቹ የሥራ አመራር የትምህርት መስኮች ሊተነተንና በእቅድ ሊመራ የሚችል ነው ።
Slide 9
የቀጠለ … ራሳችንን ከጊዜ ጋር በመልካም ሁኔታ ለማስኬድ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን መለየትና የእነዚህን ችግሮች መንስኤ ማወቅ ይገባናል። የጊዜ አጠቃቀም ተከታታይ በሆነ ስልቶችና ቴክኒኮች የተዋቀረ ነው። ስለዚህ ማንም ሰው ደጋግሞ በመስራት ሊማረው፣ ሊለማመደውና ራሱን በማብቃት ጥሩ ሙያተኛ መሆን የሚቻልበት ክህሎት ነው።
Slide 10
የጊዜ አጠቃቀም ስነ-ልቦና የስነ-ልቦና ተዛማጅ ፅሁፎች እንደሚያስረዱን የኑሮ ደረጃችንና የህይወት ዘይቤያችን ከሚወስኑት ጉዳዮች መካከል ስለራሳችን የሚኖረን ስሜት አንዱ ነው። ለራሳችን የምንሰጠው ግምት “ ራ ሳችንን ምን ያህል እንወደዋለን ?” ለሚለው ጥያቄ የሚኖረን ምላሽ ነው ።
Slide 11
የቀጠለ … ሥራችንን ውጤታማ በሆነ መንገድ መስራት ስንችል ለራሳችን የምንሰጠው ግምት ከፍ የሚል ሲሆን አፈፃፀማችን ከዚህ በተቃራኒው ከሆነ ደግሞ ለራሳችን የሚኖረን ግምት እየወረደ ይሄዳል ( ተፈራ ፣ 2017 )። በጊዜ አጠቃቀም ስነ-ልቦና መሰረት የሚያደርገው የቁጥጥር ህግ /Law of Control/ በሚባል በሚታወቀው ቀላል መርህ ነው ።
Slide 12
የቀጠለ …. በዚህ መርህ መሰረት ምርታማ ፣ ተወዳዳሪና የተሻለ የመስራት ችሎታ እንዳለን በተሰማን ቁጥር ለራሳችን የምንሰጠው ግምት ከፍ ያለ ይሆናል ። የራሳቸውን ጊዜ በተገቢው የሚመሩ ሰዎች ለራሳቸው አዎንታዊ ስሜትና የራስ መተማመን እንዲኖራቸው እና ለራሳቸው ህይወት ኃላፊነት የሚሰማቸው ይሆናሉ ( ተሬስ ፣ 2013)።
Slide 13
የቀጠለ … በዚህ ህግ መሰረት አንድ ሰው ስለራሱ በሚሰማው አሉታዊ የሆነ ስሜት ልክ የራሱን ህይወትና የተሰማራበትን የሥራ መስክ በቁጥጥሩ ስር ማድረግ እንዳልቻለ ይሰማዋል ( ተፈራ ፣ 2017 )።
Slide 14
የጊዜ አጠቃቀም ማሻሻያ ስልቶች በህይወታችን ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት ለውጥ ሊመጣ የሚችለው አንድን ነገር በተለየ መንገድ ለማከናወን ግልጽ እና ፍላጎታችን ስሜታችንን ሊገልጽ የሚችል ውሳኔ መስጠት ስንችል ነው (ተሬስ፣2013)። የተሬስ አራት የጊዜ አጠቃቀም ማሻሻያ ነጥቦችን መሰረት አድርገን የጊዜ አጠቃቀማችንን ማሻሻል ከቻልን ህይወታችንም በዚያው ልክ ለመለወጥ የሚያስቸሉን ናቸው ። እነሱም ፦
Slide 15
የቀጠለ ፍላጎት ፦ ህይወታችንን ለመቀየር አሁን ባለን የጊዜ አጠቃቀም ልንቆጭና ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ከልብ የመነጨ ፍላጎት ሊኖረን ይገባል ። ወሳኝነት ፡- አሁን ያለንን የጊዜ አጠቃቀም ችግር በመቀየር ውጤታማ የሆነ የጊዜ አመራር ቴክኒኮችን የህይወታችን አካል ወይም ልማድ እስክናደርጋቸው ድረስ ለመለማመድና በየቀኑ ለመተግበር ውሳኔ ላይ መድረስ ያስፈልጋል ።
Slide 16
የቀጠለ … 3.ቁርጠኝነት ፡- የነበረንን ደካማ የጊዜ አጠቃቀም ለመቀየር ፍላጎቱ ካለንና ውሳኔ ላይ ከደረስን ቀጥሎ የሚመጣው ነገር በውሳኔያችን መጽናት ነው ። ውሳኔያችንን በተግባር ለመተርጎም ቁርጠኛ ልንሆን ይገባል ። 4.ዲሲፕሊን ፡- ዲሲፕሊን ማለት የጊዜ አመራር የህይወታችን አካል የእድሜ ልክ ተግባራችን ወይም ልማድ እንዲሆን ራሳችንን ማስገዛት ነው ። ዲሲፕሊን መስራት የሚገባህንና የምታውቀውን ነገር ብትፈልገውም ባትፈልገውም ፣ ለመስራት ሞራሉ ቢኖርህም ባይኖርህም ራስህን ለዚሁ ተግባር ማስገዛት ነው ።
Slide 17
የጎን ለጎን ውይይት- 6.3.1 ዓላማ፡ የጊዜ አጠቃቀም ክህሎትን ማሳደግ፡፡ አካሄድ፡ በጎን ለጎን አቀማመጥ 2 ወይም 3 አባላት ያለው ቡድን መመስረት፣ አቀራረብ፡ በአንድ ቡድን አባል አማካኝት በቃል ሪፖርት ማቅረብ ጊዜ፡ ለውይይት 15 ደቂቃ፤ ለማቅረብ 5 ደቂቃ 1.ስነ-ልቦና በጊዜ አጠቃቀም ላይ ያለው ተፅዕኖ ምንድነው? 2.አራቱን የጊዜ አጠቃቀም ማሻሻያ መንገዶች በመለየት ተንትኑ::
Slide 18
ደካማ የጊዜ አጠቃቀም ምልክቶች ደካማ የጊዜ አጠቃቀም በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ጥምር ምልክቶች የሚገለጽ ነው ፡፡ ደካማ የጊዜ አጠቃቀም የሚታይባቸው መሪዎችና ሰራተኞች እነዚህን ምልክቶች በራሳቸው በመረዳት ወዲያውኑ አስፈላጊ የሆነ የእርምት እርምጃ መውሰድ ይገባቸዋል (ተፈራ፣2017 እና ስራ አመራር ስልጠና ልማት ፣2010 )
Slide 19
ደካማ የጊዜ አጠቃቀም ምልክቶች … 1. በተደጋጋሚ መዘግየት ፡- ስራዎችን በተደጋጋሚ የምናዘገይ ከሆነ በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ የሆኑ የጊዜ ገደቦችን መጠበቅ የሚያስቸግረን ደረጃ ላይ ሊያደርሰን ይችላል፡፡ 2. ቀጠሮን ያለማክበር:- ቀጠሮን በተደጋጋሚ የማናከብር ከሆነ ከአቅም በላይ የሆነ ብዙ ስራ ተቀብለናል ካልሆነም ደግሞ ለተግባራቱ በቂ የሆነ ጊዜ አልመደብንላቸውም ማለት ነው።
Slide 20
ደካማ የጊዜ አጠቃቀም ምልክቶች … 3 . ደካማ የሥራ አፈጻጸም ፡- ጊዜን በተገቢው ጥቅም ላይ ማዋል ካልቻልን፣ ቀጠሮዎችን በተደጋጋሚ የማናከብር ከሆነ፣ ተግባራትን በተደጋጋሚ የምናዘገይ ከሆነ ስራዎች እየተገፉና እየተጠራቀሙ ይሄዳሉ። በመጨረሻም የሥራ አፈፃፀማችንን ዝቅተኛ ይሆናል ። 4. መጣደፍ :- መቸኮል ወይም መጣደፍ በራሱ ችግር ነው ብሎ መውሰድ ባይቻልም በተደጋጋሚ ሲከሰት እና ከአንድ ቀጠሮ ወደ ሌላ ቀጠሮ፣ አንደኛውን አንጠልጥለን ወደ ሌላኛው የምንሯሯጥ ከሆነ ደካማ የሆነ የጊዜ አጠቃቀም ያለን መሆኑን ያሳያል፡፡
Slide 21
ደካማ የጊዜ አጠቃቀም ምልክቶች … 5. ትኩረት ማጣት :- ሁሉም ነገሮች በአጣዳፊ ሁኔታ እንዲከናወኑ በሚፈለግበት ጊዜ በቀላሉ ቅደም ተከተል አውጥተን ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ሊሰሩ የሚገባቸውን ስራዎች ትኩረት ሰጥተን ለመስራት አቅም እያጣን እንሄዳለን ፡፡ 6 . ሁሉንም ነገር በራስ ለማከናወን መፈለግ ፡- አንደኛውና ዋነኛው የደካማ የጊዜ አጠቃቀም መገለጫ ሁሉን ስራ በራስ ለማከናወን የሚደረግ ጥረት ነው ። በራሳችን የግል ሥራ የምንተዳደርም ይሁን ተቀጣሪ በውክልና የምናስተላልፈው ሥራ ሁልጊዜም ይኖራል ።
Slide 22
ደካማ የጊዜ አጠቃቀም ምልክቶች … 7. አይሆንም ያለማለት ፡- ሌሎችን መርዳት መቻል ትልቅ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜ ሰዎችን ለመርዳት ጥረት በምናደርግበት ጊዜ ቅድም-ተከተል አውጥተን ለመስራት ያቀድናቸውን የራሳችን ተግባራት ሳንሰራ እንቀራለን ፡፡ ስለዚህ የራስን የጊዜ አጠቃቀም ሂደት ለማሻሻል የሚጠቅመን አንዱና ዋነኛው መንገድ " አይሆንም " የሚለውን አባባል መልመድ ነው፡፡
Slide 23
ደካማ የጊዜ አጠቃቀም ምልክቶች … 8. ፍጹማዊነት:- አንዳንድ ጊዜ ስራዎቻችንን እንከን የለሽ እና ፍጹማዊ በሆነ መንገድ ለመስራት ራሳችንን ከማዘጋጀት ጀምሮ በምናደርገው ጥረት ብዙ ጊዜያችንን እናቃጥላለን፡፡ በዚህ ሂደት ስራዎችን ከመስራት እንታቀብና ሳይሰሩ ይቀራሉ ወይም ደግሞ በሚያስደንቅ ሁኔታ ይጓተታሉ ፡፡ እውነታውን ካየን ግን ያለምንም ስህተት ሊሰሩ የሚችሉ በጣም ጥቂት ስራዎች ሊኖሩ ይችላሉ።
Slide 24
ምንጭ፡- ስራ አመራር ስልጠና ልማት (2010)
Slide 25
የጊዜ አጠቃቀም ተግዳሮቶች 1 . በእቅድ ያለመመራት ችግር :- ለውድቀት የሚያቅድ ሰው የለም። ነገር ግን አለማቀድ በራሱ ውድቀት ስለሆነ ሰዎች ራሳቸውን በእቅድ መመራት ካልቻሉ ውድቀት ያጋጥማቸዋል ። እቅድ ከሌለን ትኩረታ ችን ንና ጊዜያችንን ከፊት ለፊታችን የሚታየው/የምናገኘው ነገር ይወስድብናል።
Slide 26
የጊዜ አጠቃቀም ተግዳሮቶች … የቀጠለ 2. አስቸኳይና ደራሽ በሆኑ ሥራዎች መጠመድ ፡- አስቸኳይ ፣ ጠቃሚና አስፈላጊ ያልሆኑ ተግባራትን መለየት ባለመቻላችን ምክንያት ጠቃሚና አስፈላጊ የሆኑ ሥራዎች ወደ ጎን ተትተው ጠቃሚ ያልሆኑ ተግባራት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የመከናወን እድል ሊያገኙ ይችላሉ። 3. ስራን ለነገ ማለት ወይም ማዘግየት :- ሥራን ወደ ነገ እንደ መግፋት የሚቀል ነገር የለም። ችግሩ ግን ሥራዎች ወደ ነገ እየተገፉ ሄደው መጨረሻ ላይ ለጥድፊያና ውጥረት የሚያጋልጡን መሆናቸው ነው።
Slide 27
የጊዜ አጠቃቀም ተግዳሮቶች … የቀጠለ ተግባራት የማጠናቀቂያ ጊዜያቸው ሲደርስ ወደ አስቸኳይ ተግባርነት ይቀየራሉ። በዚህ ሂደት ትኩረታችን አስቸኳይ በሆኑ ሥራዎች ላይ ብቻ እየሆነ ይሄዳል። 4.የአደናቃፊዎች መኖር :- ከ አደናቃፊዎች መካከል ከኮምፒውተራችን የቻት ወይም ኢ-ሜል ጥሪ፣ የስራ ያልሆኑ የስልክ ጥሪዎች ፣ ያልታቀዱ ስብሰባዎች፣ ሰዎች ለወሬ ወደ እኛ ቢሮ ሲመጡ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
Slide 28
የጊዜ አጠቃቀም ተግዳሮቶች … የቀጠለ በውጭ ሀገር የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት 50 ከመቶ የሚሆነው የሥራ ጊዜ ሰራተኞች በስራ ቦታቸው ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በሚያደርጉት ጫዎታና ወሬ ይባክናል፡፡ 5 . ስራን ለሌሎች ሰዎች ያለማካፈል:- ሁሉንም ሥራ በራስ ለመስራት መፈለግ ወይም መሞከር ጊዜችንን በሌሎች ወሳኝ ተግባራት ላይ እንዳናተኩር በማድረግ ጊዜያችን እንዲባካን ያደርጋል።
Slide 29
የጊዜ አጠቃቀም ተግዳሮቶች … የቀጠለ ብዙ ው ን ጊዜ እንደምክንያት ተደርጎ የሚነሳው ጉዳይ እኔ ልሰራው ባሰብኩት መንገድ ሊሰራልኝ አይችልም የሚል ስሜት መኖር ሲሆን ይህን ስጋት ለመቀነስ ምሁ ራንን የሚመክሩት ጠቅላላ መርህ “ ስራውን እንደራስህ አድርጎ 80% ያህሉን ለሚያከናውን ሰው ውክልና ስጥ ፡፡
Slide 30
የጊዜ አጠቃቀም ተግዳሮቶች … የቀጠለ 6 .የተዝረከረከ የስራ አካባቢ :- በርካታ ሰዎች የሚጠቅማቸውንም ሆነ የማይጠቅማቸውን ነገሮች በዙሪያቸው ሰብስበው መያዝ ይወዳሉ፡፡ ጠረጴዛቸው ላይ ያለው ነገር ከመብዛቱና በተገቢው ያልተደራጀ በመሆኑ ምክንያት የሚፈልጉትን ነገር በቀላሉ ፈልጎ ለማግኘት ሲቸገሩ እንመለከታለን። 7 . አይሆንም ማለት ያለመቻል :- አመራሩም ሆነ ፈፃሚው አይሆንም ማለትን መድፈር ያለመቻል አንዱና ዋነኛው የጊዜ አባካኝ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
Slide 31
የጊዜ አጠቃቀም ተግዳሮቶች … የቀጠለ 8 . ደካማ የስብሰባ አመራር ፡- ስብሰባ ከተግባቦት መሳሪያዎች አንዱ ሲሆን በግልፅ የተለየ አጀንዳና ዓላማያለው እንዲሁም በጊዜ ገደብ የተወሰነ መሆንይኖርበታል ፡፡
Slide 32
የጊዜ አመራር ተግዳሮቶች … በሌሎች የተግባቦት መንገዶች በቀላሉ መተላለፍ የሚችሉ መልዕክቶችን የሚደረጉ ስብሰባዎች የጊዜ ገደብ የሌላቸው ፣ ተመሳሳይ ሃሳቦች የሚነሱበት ፣ ከአጀንዳ ውጭ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩባቸው ናቸው ፡፡
Slide 33
የቡድን ውይይት-2.2.7 ዓላማ ፡ የጊዜ አጠቃቀም ተግዳሮቶችን በመለየት ጠንካራ የጊዜ አጠቃቀም እንዲኖር ማስቻል ፡፡ አካሄድ ፡ ከ4-8 አባላት ያለው ቡድን መመስረት ፣ አቀራረብ ፡ ፍሊፕ ቻርት በመጠቀም በአንድ ተወካይ አማካኝት ማቅረብ ጊዜ ፡ ለውይይት 2፡00 ሰዓት ፤ ለማቅረብ 15 ደቂቃ ፤ ለክፍል ውይይት 1 ሰዓት በመ / ቤታችሁ ያሉ ጠንካራና ደካማ የጊዜ ስራ አመራር ምልክቶችን በመለየት ዘርዝሩ ፣ በመ / ቤታችሁ ያሉ የጊዜ አጠቃቀም ተግዳሮቶች በመለየት ተንትኑ ፡፡ ከኬዝ-2 የጊዜ አጠቃቀም መነሻነት ፡- የቀረበው ኬዝ-2 የጊዜ አጠቃቀም ከአመለካከት አንፃር ያለው ቁርኝት ምንድነው ? ከቀረበው ኬዝ ምን እንማራለን ?
Slide 34
የቪዲዮ መወያያ (09፡50 ደቂቃ ) ስብሰባ ላይ ናቸው በሚል ርዕስ ለ09፡50 ደቂቃ የቀረበ ቪዲዮ ከቪዲዮው ምን ትምህርት ወሰዳችሁ?
Slide 35
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች 1. የጊዜ አጠቃቀማችንን መፈተሽ ውጤታማ የጊዜ አመራርንን ተግባራዊ ለማድረግ የመጀመሪያው እርምጃ የነበረንን የጊዜ አጠቃቀም መፈተሽ ወይም መገምገም ይሆናል ፡፡ የዕለት ተግባራት አፈፃፀም መመዝገቢያ ቅጽ በቀን ውስጥ ያከናወንናቸውን ተግባራት ሁሉ ማለትም ፦ ለጉዞ ፣ ጋዜጣ ለማንበብ ፣ ምግብ ለመመገብ ፣ ስልክ ለማናገር ወዘተ . የተጠቀምንበትን ጊዜ ሁሉ ሳይቀር ከሥራ መጀመሪያ እስከ ማጠናቀቂያ ጊዜ ድረስ ያለውን ተግባራችንን በቅደም ተከተል መመዝገብ ያስፈልጋል ።
Slide 36
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች ለምሳሌ ፡- በሳምንቱ ውስጥ ጠቃሚ ለሆኑ ሥራዎች ያዋለው የጊዜ መጠን 15 ሰዓታት ቢሆንና በሳምንቱ ውስጥ ጠቅላላ በሥራ ላይ የነበረበት ጠቅላላ ጊዜ 48 ሰዓት ቢሆን የጊዜ አጠቃቀም ሬሽዮ 31.25 ከመቶ (15/48 X 100) ይሆናል። የተገኘው ውጤት ከነበረው ወይም በሳምንቱ ካለን 48 ሰዓት ውስጥ ጠቃሚ ለሆኑ ጉዳዮች ምን ያህሉን እንዳዋልን የምንረዳበት ስሌት ነው፡፡
Slide 37
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች የተገኘው ውጤት ከነበረው ወይም በሳምንቱ ካለን 48 ሰዓት ውስጥ ጠቃሚ ለሆኑ ጉዳዮች ምን ያህሉን እንዳዋልን የምንረዳበት ስሌት ነው ፡፡ 2. የጊዜ አጠቃቀም እቅድ ማዘጋጀት ውጤታማ መሪዎች በእቅድ ዝግጅትና አጠቃቀም ላይ የተሻለ ልምድ ያላቸው ናቸው ማለት ይቻላል ። ምክንያቱም ተግባራትን ከማከናወናቸው በፊት ዋናና ጥቃቅን በሚል ግቦችን በዝርዝር ለይተው ያስቀምጣሉ።
Slide 38
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች ከዚያም ተግባራትን ቅደም ተከተል በጠበቀ ሁኔታ በዝርዝር በጽሁፍ ያሰፍራሉ። ያለእቅድ የሚከናወን ተግባር ሁሉ ለውድቀት መንስኤ ነውና ። “ ለእቅድ ዝግጅት የምናውላት እያንዳንዷ ደቂቃ በትግበራ ወቅት የምንጠቀምበትን ጊዜ በአስር ደቂቃ ለመቆጠብ ታስችላለች ።” የሚባል ህግ አለ። ልናከናውነው ስለምንፈልገው ተግባር አስቀድመን እንዴት መስራት እንዳለብን ለማሰብና ለማቀድ የምናደርገው ጥረት በተግባር ወቅት የምናጠፋውን ሀይል በእጅጉ ሊቀንስልን ይችላል።
Slide 39
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች ቀንህን አስቀድመህ በማቀድ ጀምር። በዕለት የምታከናውናቸውን ተግባራት በዝርዝር ለያቸው። ከዚያም በቀን ውስጥ ለምታከናውናቸው ተግባራት የድርጊት መርሐ ግብር አዘጋጅላቸው። ይሄውም ለእያንዳንዱ ተግባር ምን ያህል ጊዜ እንደሚያስፈልግ መመደብ ማለት ነው። ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውና ቅድሚያ ሊሰጡ የሚገባቸው ተግባራት ከላይ መፃፍ ሲገባቸው ዝቅተኛ ጠቀሜታ ያላቸው ነገር ግን መሰራት የሚገባቸው ተግባራትን ደግሞ ከታች በቅደም ተከተላቸው ማስቀመጥ ይኖርብናል።
Slide 40
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች በተቻለ መጠን አንድ ተግባር ከጀመርህ ለማጠናቀቅ ሞክር። የጀመርከውን ሥራ ሳታጠናቅቅ አዲስ ሥራ አትጀምር። አንዱን ሥራ ስታጠናቅቅ በዕለት ዕቅድ መዝገብህ ላይ ምልክት አድርግ።
Slide 41
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የዕለት እቅድ ለማዘጋጀት የሚረዱን ነጥቦች 1 . በየቀኑ የምታከናውናቸውን ተግባራት በመለየት የዕለት እቅድ የማዘጋጀት ልምድ ይኑርህ፣ 2 . በጊዜ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ ውስንነቶችን በመረዳት ለተግባራት ተገቢ የሆነ ጊዜ ስጥ፣ 3. በቀን ውስጥ ልታከናውነው ከምትችለው በላይ የሆኑ ተግባራትን ለማቀድ አትሞክር፣
Slide 42
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … 4. በሰራሃቸው/ በተጠናቀቁ ተግባራት ልክ አዳዲስ ተግባራትን በየጊዜው በእቅድህ ማካተት ፣ 5. እያንዳንዱን ተግባር ከማከናወንህ በፊት “ የግድ እኔ መስራት ይኖርብኛል ? ” የሚለውን ጥያቄ ለራስህ ማንሳትና የሚቻል ከሆነ በሌሎች ሰዎች እንዲከናወን ውክልና መስጠት፣ 6. ተመሳሳይነት ያላቸውን ተግባራት በአንድ ላይ መሰ ብ ሰብ ናቸው ።
Slide 43
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች 3. እቅዳችንን መፈተሽ እቅድ በየቀኑ የምናከናውናቸው ተግባራትን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ነው ። እነዚህን ዝርዝሮች መፈተሽና አስፈላጊና ጠቃሚ መሆናቸውን ማረጋጥ ያስፈልጋል ። ይህንን ለማድረግ ቀጥሎ የተቀመጡ ነጥቦችን ልንጠቀም እንችላለን ። አስፈላጊነት ፦ እያንዳንዱ ተግባር ጠቃሚ ስለመሆኑ መመርመር ጠቃሚ ነው።
Slide 44
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች ተስማሚነት ፦ ተግባራቱን የሚያከናውነው ማነው? ተቋሙ ወይም የሥራ ክፍሉ ይህንን ተግባር ማከናወን አለበት ወይ? የሚለውን የሚያሳየን ሆኖ ከራሳችን እውቀትና ክህሎት በላይ የሆኑ ተግባራትን በሌሎች እንዲሰሩ ማድረግም የበለጠ ጠቀሜታ ያለው ነው። ውጤታማነት ፦ ይህ ተግባር አሁን መከናወን ያለበት ነው? ከዓላማችንና ግቦቻችን ጋር ግንኙነት አለው? ቅድሚያስ ልንሰጠው የሚገባው ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን የሚመልስ መሆን ይኖርበታል።
Slide 45
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች 4.ግብ ማስቀመጥ :- ግብ ማስቀመጥ ራሳችን እና ሌሎች ፈፃሚዎችን ለማበረታታት እና ለማሳመን እንደ አንድ ትልቅ መሳሪያ ልንጠቀምበት እንችላለን። ግቦቻችንን ስናረጋግጥ የአሳክቸዋለሁ ስሜት የሚፈጥርብን ከመሆኑም ሌላ በያዝነው መንገድ እንድንቀጥል የሚያበረታታን ይሆናል። ግቦችን ስናስቀምጥ በትክክለኛው መንገድ ማስቀመጥ የሚኖርብን ሲሆን ግልጽ፣ በተግባር ሊተረጎሙ የሚችሉና በጊዜ የተገደቡ ከሆኑ ከየት ተነስተን የት መድረስ እንደምንፈልግ በግልጽ የሚያሳየን ይሆናል፡፡
Slide 46
48
Slide 47
ሪፖርት ላይ ያሉ ክፍተቶች ለአንባቢው የማይገቡ አላስፈላጊ ቴክኒካል ቃላት መጠቀም አላስፈላጊ ገላጮችን በመጠቀም ውጤቱን አለመጻፍ ፡፡ ለምሳሌ ፡- አበረታች ውጤት እየተመዘገበ ነው አጥጋቢ ደረጃ ነው ማለት ይቻላል መነሳሳቶች ይስተዋለሉ ቁርጠኝነት እየጨመረ ነው ቁጥሩ ቀላል የማይባል … ከምንፈልገው አንጸር ይቀረዋል በጥሩ ቁመና ላይ … ነን . የአመራሩ መሰጠት እየተሻሻለ ነው
Slide 48
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች ….. ውክልና ሲሰጥ ፡ - “ የ80% ህግ” በመባል የሚታወቀውን ተግባራዊ ማድረግ የስራ ተነሳሽነት ፣ ተግባራትን በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ ያለው ፍላጎት እና ሙያዊ ብቃት መሰረት አድርጎ መሆን ይኖርበታል። ማስታወሻ ፡-ውክልና ከመስጠታችን በፊት “ ስህተት ቢፈጠር ምን ያህል ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ?” በሚል ራሳችንን መጠየቅ ያስፈልጋል። ስህተት የመፈጠር እድሉ ሰፊ ከሆነና ስህተቱም ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ከሆነ ውክልናውን አለመስጠቱ ይመረጣል። የግድ ከሆነም የቅርብ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል።
Slide 49
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ ከዚህ ጋር ተያይዞ አሌክሳንደር እና ዱብሰን የለዩአቸው ብዙ የሥራ መሪዎች ሥራዎችን ለሌሎች ሰዎች ማካፈል ወይም በውክልና ለማሰራት ከማይፈልጉባቸው ምክንያቶችን መካከል የተወሰኑትን ቀጥሎ እንመለከታለን። እነሱም፦ 1. “ እኔ በተሻለ ልሰራው እችላለሁ”፦ ሥራውን አንተ በተሻለ ልትሰራው ትችል ይሆናል። ቢሆንም ግን በውክልና ማሰራቱ የበለጠ ጠቃሚ ነው።
Slide 50
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ 2 . “ ሥራው በትክክል ላይሰራ ይችላል”፦ በተቋም ውስጥ በሚሰሩ ሥራዎች ጥቂት ስህተቶችን ለመታገስ የሚያስችል እድል መፈጠር አለበት። ያለምንም ድካም ስኬት እንደማይኖር ሁሉ ያለምንም ስህተት የሚመጣ ውጤት የለም ። 3 .“ ውክልና መስጠት አይመቸኝም”፦ ብዙ ጊዜ ከለመድናቸውና በጣም ቀላል ከሆኑ የዕለት ከዕለት ሥራዎች ራሳችንን ማራቅ በጣም ከባድ ፈተና ይሆንብናል።
Slide 51
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ 4. “ ይህ ሥራ ከእኔ ቁጥጥር ውጭ እንዲሆን አልፈልግም ”፦ ተግባራትን ራሳችን ስለምንሰራቸው በቁጥጥራችን ስር እንደሆኑ ሌላው ከሰራቸው ከቁጥጥራችን ውጭ እንደሆኑ አድርጎ ማሰብ የዋህነት ነው። 5. “ ከሥራው አስፈላጊነት አኳያ በላቀ ጥራት መከናወን አለበት”፦ ይህ ሀሳብ ጥሩ ቢመስልም በውስጡ ሁሉም ስራዎች ፍፁም ስህተት የለሽ መሆን አለባቸው ወደሚል አስተሳሰብ የሚያመራን ነው። ይህም ለአላስፈላጊ ቁጥጥርና በመጨረሻም ለውድቀት ሊዳርገን የሚችል ነው።
Slide 52
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ አራቱ የውክልና ህጎች ታጋሽ ሁን ፦ ውክልናውን የሚወስደው ሰው ስለ ስራው ለማወቅ ጊዜ ያስፈልገዋል። ሥራን ቀስ በቀስ መድብ ፦ ፈፃሚዎች ወይንም የበታች አመራሮች በአንድ ጀምበር ከባድ ኃላፊነት እንዲጣልባቸው ማድረግ አይገባም። ውክልናን አስቀድመህ የመስጠት ልምድ ይኑርህ ፦ ውክልና የምትሰጣቸው ሰዎችን ችግር ውስጥ በሚያስገባ መልኩ ውክልናን አትስጥ። በተቻለ መጠን የሥራውን አንድ ክፍል ሳይሆን ሙሉ ሥራውን መስጠት ፦ ይህንን በማድረግ ውክልና ተቀባዩ በሥራው ወቅት ሊፈጠር ከሚችለው ግራ መጋባት ወይም የግልጽነት ችግር ማዳን ትችላለህ።
Slide 53
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ 6. የተግባራትን ቅደም ተከተል መለየት ልናሳካው ከምንፈልገው ዓላማ አንፃር ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ተግባራትን መለየት ያስፈልጋል። በቅደም ተከተል መለየት ስንል- በጣም ጠቃሚና አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን ብዙ ጊዜ እንዲመደብላቸው ለማድረግ እና አስፈላጊነታቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ሥራዎች ደግሞ እንደዚሁ ተመጣጣኝ የሆነ ጊዜ በመመደብ የራሳችንን ምርጫና ውሳኔ መቆጣጠር ማለት ነው።
Slide 54
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ የስቴፈን ኮቬይ የጊዜ ማትሪክስ ይህ ማትሪክስ ተግባራትን ከጠቀሜታቸው እና አስቸኳይነታቸው አኳያ በአራት ክፍሎች ከፋፍለን እንድናይ የሚያስችለን ስዕላዊ መግለጫ ሲሆን የትኛውን ተግባር አስቀድመን መስራት እንደሚገባን ፤ የትኛውን ራሳችን እና የትኛውን ደግሞ በሌሎች ማሰራት እንደሚገባን በቀላሉ የሚያስረዳን ነው ።
Slide 55
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ የስቴፈን ኮቬይ የጊዜ ማትሪክስ
Slide 56
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ የስቴፈን ኮቬይ የጊዜ ማትሪክስ ክፍል አንድ /Q-I/፦ የሚወክለው አስቸኳይና ጠቃሚ የሆኑ ስራዎችን ሲሆን ይህ ክፍል “ እሳት ማጥፋት ” ብለን የምንጠራውን ዓይነት ስራዎች የሚገኙበት ክፍል ነው ። በዚህ ክፍል ያሉ ስራዎች የማጠናቀቂያ ጊዜያቸው የተቃረበ በጣም አስፈላጊና በፍጥነት መጠናቀቅ ያለባቸው እንደመሆናቸው ብዙ ጫና እና ውጥረትን ይፈጥራሉ ። የዚህ ዓይነት ስራዎችን አንተው እንድታከናውናቸው ይመከራል ። ክፍል ሁለት /Q-II/፦ ይህ ክፍል በጣም ጠቃሚ ነገር ግን አስቸኳይ ያልሆኑ ተግባራት የሚገኙበት ክፍል ሲሆን እነዚህ ስራዎች ለዓላማችን መሳካት ካላቸው ጠቀሜታ አንፃር በቂ ጊዜ ተመድቦላቸው እና ዕቅድ ተዘጋጅቶላቸው በተገቢው ሊከናወኑ ይገባል ።
Slide 57
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ እነዚህ ተግባራት ለዓላማችንና ለግቦቻችን መሳካት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው ቢሆኑም የግድ አሁኑኑ መሰራት የሚገባቸው አይደሉም ። ክፍል ሶስት /Q-III/፦ በዚህ ክፍል ያሉ ተግባራት ጠቃሚ ያልሆኑ ግን ደግሞ አስቸኳይ ተግባራት ናቸው ። ክፍል አራት /Q-IV/፦ የሚወክለው አስቸኳይም ጠቃሚም ያልሆኑ ተግባራትን ሲሆን ከጊዜ ብክነት በቀር ለዓላማችን መሳካት ምንም ዓይነት ፋይዳ የሌላቸው ናቸው ።
Slide 58
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ የABC ትንተና ዘዴ ፦ ይህ የትንተና ዘዴ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በቢዝነስ አመራር በርካታ መረጃዎችን ለመለየትና ለማደራጀት ሲጠቀሙበት የነበረ ቴክኒክ ነው ። ይህ ዘዴ ተግባራትን እንደየጠቀሜታቸው በደረጃ የመለየትና በቡድን የመመደብ ዘዴ ሲሆን እነዚህን ቡድኖችም A፣ B እና C ብለን እንሰይማቸዋለን ። A- ተግባራት ፦ በጣም አስቸኳይና ጠቃሚ ጊዜ ሳይሰጣቸው የግድ ሊከናወኑ የሚገባቸው ተግባራትን የሚያቅፍ ነው ። B- ተግባራት ፦ ጠቃሚ ነገር ግን አስቸኳይ ያልሆኑ ተግባራት ሲሆኑ ከA-ተግባራት ቀጥሎ ሊከናወኑ የሚገባቸው ናቸው ።
Slide 59
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ C- ተግባራት ፦ A እና B ተግባራት እስኪጠናቀቁ ሊጠብቁ የሚችሉ ፣ ለተወሰነ ጊዜ ቢቆዩ ብዙ ችግር የማያስከትሉና ዘግይተው ሊሰሩ የሚገባቸው ተግባራት ይሆናሉ ። D- ተግባራት ፦ በውክልና በሌሎች ሰዎች ሊሰሩ የሚችሉ ነገር ግን የቅርብ ክትትል የሚጠይቁ ሥራዎች ሊሆኑ ይችላሉ ። E- ተግባራት ፦ አሉታዊ ተፅዕኗቸው የበዛ ወይም እንቅፋቶች ሲሆኑ ሊወገዱ የሚገባቸው ተግባራት ናቸው ፡
Slide 60
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ የፓሪቶ ትንተና ዘዴ ይህ የትንተና ዘዴ “ የ80/20 ህግ ” በመባልም ይታወቃል ። በዚህ ህግ መሰረት 80 ከመቶ የሚሆነው የስራችን ውጤት የሚገኘው 20 ከመቶ ከሚሆኑ ተግባራት ነው ። የ“80/20” ህግ በጊዜ አመራር እይታ 80 ከመቶ የሚሆኑ ሥራዎች 20 ከመቶ ጥቅም ላይ በምናውለው ጊዜ(ሰዓት) ሊጠናቀቅ ይችላል። ቀሪው 20 ከመቶ ሥራዎች 80 በመቶ የሚሆነውን ጊዜ ሊጠቀሙ ይችላሉ የሚል ነው።
Slide 61
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ 66 ይህ መርህ ሥራዎችን በሁለት ክፍሎች ከፍለን እንድናይ የሚያስችለን ነው ። በዚህም መሰረት በቡድን አንድ ስር የሚካተቱት 80 ከመቶ የሚሆነውን ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ ነገር ግን በጣም ጥቂት (20 ከመቶ) ተግባራትን በመለየት ይሆናል። በቡድን ሁለት ስር የሚካተቱት ደግሞ ለውጤታችን 20 ከመቶ አስተዋጽኦ ያላቸው ነገር ግን 80 ከመቶ የሚሆኑ ሥራዎች ሲሆኑ በአተገባበር ወቅት ከጠቀሜታቸው አኳያ በቡድን አንድ ከተቀመጡት ቀጥሎ የሚታዩ ናቸው።
Slide 62
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ 7. የድርጊት መርሐ ግብር ማዘጋጀት ተግባራትን ከጠቀሜታቸውና አስቸኳይነታቸው አንፃር ከለየን በኋላ ቀጣዩ ተግባር ለተለዩ ተግባራት የአፈፃፀም መርሐ ግብር / የጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀት ነው ። የምናዘጋጀው የጊዜ ሰሌዳ ዕለታዊና ሳምንታዊ በሚል መከፋፈል ይኖርበታል ። ሳምንታዊ እቅዳችን የተግባራት አጠቃላይ ስኬት / ውጤት ለማሳየት የሚጠቅመን ሲሆን ዕለታዊ እቅድ ግን የየዕለቱን አፈፃፀማችንን ለመፈተሽና በእቅዳችን መሰረት እያከናወንን መሆናችንን ለማረጋገጥ የምንጠቀምበት ነው ።
Slide 63
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ የድርጊት መርሐ ግብር ዝግጅት አማራጮች ውጤታማ የድርጊት መርሐ ግብር ስናዘጋጅ በአጭር ፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ተከፋፍሎ ሊዘጋጅ እንደሚገባ ማወቅ ተገቢ ይሆናል ። የረጅም ጊዜ መርሐ ግብር ፦ ብዙውን ጊዜ ከሩብ ዓመት እስከ አንድ ዓመት የሚደርሱ እቅዶችን ለማዘጋጀት የምጠቀምበት ሲሆን የረጅም ጊዜ ግቦቻችንን ለማሳካት የሚረዳን ይሆናል ። የመካከለኛ ጊዜ መርሐ ግብር ፦ በአብዛኛው ከሳምንታዊ እስከ ወርሃዊ የሚደርስ የድርጊት መርሐ ግብር በዚህ ክፍል የሚካተት ነው ። የአጭር ጊዜ መርሐ ግብር ፦ ብዙውን ጊዜ የአጭር ጊዜ መርሐ ግብር የምንለው የየዕለት ፕሮግራማችንን ነው ።
Slide 64
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ 8. እረፍት መውሰድ ለራስ ተገቢ የሆነ ጊዜ መውሰድ አንዱ የጊዜ አጠቃቀም ወሳኝ ክፍል ነው ። ይህንን ማድረግ አዕምሯችን እንዲነቃቃና በአዲስ መንፈስ ለሌላ ሥራ ዝግጁ እንዲሆን ለማድረግ ይረዳናል ። ሰዎች ልክ እንደ ማሽን የተሰራን ስላልሆነ የድካም ስሜት ሳይሰማንና ሳናርፍ አንድን ነገር ደግመንና ደጋግመን መስራት አንችልም ። አንዳንድ ሰዎች በጣም ትንሽ የእረፍት ጊዜ ቶሎ ቶሎ መውሰድ የበለጠ በትኩረት እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል ። እንደነዚህ አይነት ሰዎች ሰውነታቸውን ለማፍታታት ፣ ዘና ለማለት ወይም ባሉበት አካባቢ የተወሰነ እንቅስቃሴ ለማድረግ በየሰዓቱ ከ5-10 ደቂቃዎችን ይወስዳሉ ።
Slide 65
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ በርካታ ስኬታማ ሰዎች የተለየ የሰዓት አጠቃቀም ስልት አላቸው። ይሄውም ያላቸውን ጊዜያት በሶስት የተለያዩ ቀናት ማለትም የትኩረት ቀናት፣ የዝግጅት ቀናትና የነፃ/የእረፍት ቀናት በሚል ከፋፍለው የሚጠቀሙ መሆኑ ነው። የትኩረት ቀናት ፦ የሚባሉት የጊዜያችንን 80 ከመቶ የሚወስዱ ፣ ዋና ዋና የሚባሉና የበለጠ ጠቀሜታ ያላቸው ሥራዎችን የምናከናውንበት ጊዜ ነው ። በእነዚህ ቀናት የምናከናውናቸውን ዋናና ጠቃሚ የምንላቸው ሥራዎች በቅድሚያ መለየትና እነዚሁ ላይ ትኩረታችንን አድርገን መስራት ውጤታማ ያደርገናል ።
Slide 66
ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስትራቴጂዎች … የቀጠለ 2. የዝግጅት ቀናት ፦ የሚባሉት በትኩረት ቀናት ለምናከናውናቸው ዋናና ጠቃሚ ሥራዎች ቅድመ ዝግጅት የምናደርግባቸው ቀናት ናቸው ። ቅድመ ዝግጅቱ አዳዲስ ክህሎቶችን በመማር ወይም በማንበብ ሊሆን ይችላል ። 3.የእረፍት ቀናት ፦ የሚባሉት ከሥራ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የማናደርግባቸው ቀናት ናቸው ። በእነዚህ ቀናት አደጋ ካላጋጠመ በስተቀር ወደ ስራ ቦታ አንሄድም ፣ የሥራ ስልክ አንቀበልም ፣ ስብሰባዎች አይኖሩንም ወዘተ የረፍት ቀናት የሚያስፈልጉት ብርታት እና የታደሰ አእምሮን ይዘን ወደ ሥራ ለመመለስ ነው ።
Slide 67
የቡድን ውይይት-2.2.7 ዓላማ ፡ የጊዜ አጠቃቀም ተግዳሮቶችን በመለየት ጠንካራ የጊዜ አጠቃቀም እንዲኖር ማስቻል ፡፡ አካሄድ ፡ ከ4-8 አባላት ያለው ቡድን መመስረት ፣ አቀራረብ ፡ ፍሊፕ ቻርት በመጠቀም በአንድ ተወካይ አማካኝት ማቅረብ ጊዜ ፡ ለውይይት 2፡00 ሰዓት ፤ ለማቅረብ 15 ደቂቃ ፤ ለክፍል ውይይት 1 ሰዓት 1. በመ / ቤታችሁ ያሉ ጠንካራና ደካማ የጊዜ አጠቃቀም ምልክቶችን ና መንስኤዎቻቸው በመለየት ዘርዝሩ ፣ 2. የጊዜ አጠቃቀም ለማሻሻል የሚረዱ ምክረ ሀሳቦችን አስቀምጡ 3.ከኬዝ-2 የጊዜ አጠቃቀም መነሻነት ፡- የቀረበው ኬዝ-2 የጊዜ አጠቃቀም ከአመለካከት አንፃር ያለው ቁርኝት ምንድነው ? ከቀረበው ኬዝ ምን እንማራለን ?
Tags
Categories
Education
Download
Download Slideshow
Get the original presentation file
Quick Actions
Embed
Share
Save
Print
Full
Report
Statistics
Views
2
Slides
72
Age
79 days
Related Slideshows
11
TLE-9-Prepare-Salad-and-Dressing.pptxkkk
MaAngelicaCanceran
42 views
12
LESSON 1 ABOUT MEDIA AND INFORMATION.pptx
JojitGueta
35 views
60
GRADE-8-AQUACULTURE-WEEKQ1.pdfdfawgwyrsewru
MaAngelicaCanceran
56 views
26
Feelings PP Game FOR CHILDREN IN ELEMENTARY SCHOOL.pptx
KaistaGlow
52 views
54
Jeopardy_Figures_of_Speech_Template.pptx [Autosaved].pptx
acecamero20
31 views
7
Jeopardy_Figures_of_Speech.pptxvdsvdsvsdvsd
acecamero20
32 views
View More in This Category
Embed Slideshow
Dimensions
Width (px)
Height (px)
Start Page
Which slide to start from (1-72)
Options
Auto-play slides
Show controls
Embed Code
Copy Code
Share Slideshow
Share on Social Media
Share on Facebook
Share on Twitter
Share on LinkedIn
Share via Email
Or copy link
Copy
Report Content
Reason for reporting
*
Select a reason...
Inappropriate content
Copyright violation
Spam or misleading
Offensive or hateful
Privacy violation
Other
Slide number
Leave blank if it applies to the entire slideshow
Additional details
*
Help us understand the problem better