የዛፍ ዘር ምንጭ አለማም፣ ዘር አለቃቀምMonas 2 2019.pptx

Zerihun98 3 views 36 slides Sep 09, 2025
Slide 1
Slide 1 of 36
Slide 1
1
Slide 2
2
Slide 3
3
Slide 4
4
Slide 5
5
Slide 6
6
Slide 7
7
Slide 8
8
Slide 9
9
Slide 10
10
Slide 11
11
Slide 12
12
Slide 13
13
Slide 14
14
Slide 15
15
Slide 16
16
Slide 17
17
Slide 18
18
Slide 19
19
Slide 20
20
Slide 21
21
Slide 22
22
Slide 23
23
Slide 24
24
Slide 25
25
Slide 26
26
Slide 27
27
Slide 28
28
Slide 29
29
Slide 30
30
Slide 31
31
Slide 32
32
Slide 33
33
Slide 34
34
Slide 35
35
Slide 36
36

About This Presentation

Curriculum relevance and its appropriateness to develop higher order thinking skills
have been a subject of discussion in Ethiopia for many years. Various studies have
been conducted to identify and propose reform ideas to the general education
quality and efficiency problems. The main and most comp...


Slide Content

የዛፍ ዘር ምንጭ አለማም የኢትዮጵያ የአካባቢና የደን ምርምር ኢንስቲትዩት

ይዘት መግቢያ የዘር ምንጭ አይነቶች የዘር ምንጮችን ስለማቋቋም የዘር ምንጭ ደኖች ምዝገባ የዘመናዊ የዘር ምንጭ ደኖች አለማምና አያያዝ

መግቢያ ሀገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ አይነት ዘፎችና ደኖች ሀገር ናት :: በሀገሪቱ እስከ አንድ ሺህ የሚደርሱ ልዩ ልዩ የአገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች የገኛሉ ተብሎ ይገመታል :: በተጨማሪም እስከ 300 የሚደርሱ ልዩ ልዩ የዛፍ ዝርያዎች ከውጭ ሀገር ገብተው በተለያየ ደረጃ ለምተው እንደሚገኙ ይታመናል :: እነዚህ ዛፎች ፈርጀ ብዙ የሆነ ጠቀሜታ በመስጠት ላይ ይገኛሉ :: በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ገብተውና በስፋት ለምተው የሚገኙ የነጭ ባሕርዛፍና የቀይ ባሕርዛፍ ለኮንስትራክሽን : ለኢንዱስትሪ ግብዐትነት ለማገዶነት የሚሰጡት ሰፊ የሆነ አገልግሎት እንደ አብነት ሊጠቀስ የሚችል ነው :: እንደ ዋንዛ : ኮሶና ጥድ የመሳሰሉትም የዛፍ አይነቶች በጣውላ ምርት ፣ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ባላቸው ጠቀሜታና በሌሎች ልዩ ልዩ የደን ውጤቶች የሚታወቁ ናቸው :: በአፍሪካ ደረጃ በወይና ደጋ አከባቢ የመሬትን ለምነት በማዳበር ተጠቃሽ የሆነው ገርቢ ዛፍ በኢትዮጵያ በስፋት የሚገኝ አገር በቀል ዝርያ ነው :: አንዲሁም የግራር ዝርያዎች እጅግ በስፋት በማገዶ እንጨትነት በከሰልነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ ::

ዛፎች ከላይ የተገለፁትን የመሳሰሉና ሌሎች በርካታ ጠቀሜታዎች የሚሰጡ ቢሆንም ልማታቸውን በተመለከተ እንደ አገር የተጓዝንባቸው ርቀቶች አመርቂ አይደሉም :: ለዚህም አብዛኛዎቹ የዛፍ ዝርያዎች በተፈጥራዊ መንገድ ከመራባታቸው ዉጭ በሰው ሠራሽ መንገድ በዘራቸዉና በሌሎች የእፀዋት ክፈሎች በመጠቀም ተባዝተው የለሙበትና ለአገልግሎት የበቁበት መንገድ እምብዛም ስለሆነ ነው :: የአገራችንም ሰፊው ባለትናንሽ የመሬት ይዞታ አርሶ አደርና ከፊል አርብቶአደሩ ተክሎ ያሳደጋቸው የዛፍ ዝርያ አይነቶች ቁጥራቸው ቢሰላ እዚህ ግባ የሚባል አይሆንም :: በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ የልማት አካላትም በሚካሄደው የችግኝ ጣቢዎች እየተዘጋጁ የሚተከሉ የዛፍ ዝርያ አይነቶች ከአርባ እሰከ ስልሳ የማይበልጡ እንደሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ :: ይህም ካለን የሀገር ውስጥና የዉጭ የዛፍ ዝርያ ቁጥር ጋር ሲነፃፀር ከ1% በታች እንደሆነ ማስላቱ ቀላል ነው :: መግቢያ …..

በችግኝ ጣቢያ ተዘጋጅተው በሚተከሉት የዛፍ ዝርያ አይነቶችም ውስጥ ቢሆን በዝርያዎቹ ውስጥ የሚገኘውን አካባቢያው (provenance ) ተለያይነት ያማከለ ዘመናዊ የአመራረጥ ስራቶች ገና ያልተዘረጉ በመሆኑና እስከአሁን የተደረጉ ጥረቶችም አጥጋቢ ባለመሆናቸው የተገኝውን ዓይነት ዘር በመጠቀም ችግኞች መዘጋጀታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው :: ይህም በሚተከለው ተከላ ዉጤታማነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊኖረው የሚችል አሠራር በመሆኑ ይህንን ለማረም በየዝርያው ውስጥ ያሉ አካባቢያዊ ዝርያዎችን ባህሪና ዕድገት ማጥናትና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መተንተን ያሻል :: መግቢያ

ስለዚህም ወደ ችግኝ ጣቢያ የሚገቡ ዘሮች ጄነቲካዊ ፊዚካላዊና ፊዚዮሎጂካዊ ጥራት የተረጋገጠ መሆኑ በችግኞት ዝግጅትና በመስክ ተከላዎች ውጤታማነት ላይ ከፍ ያለ ድርሻ ይኖረዋል :: አንድ የዛፍ ዘር ጄነቲካዊ ጥራት አለው ሢባል ከጥሩ እናት ዛፎች የመጣ ለአከባቢውና ለታለመለት አላማ የተስማማ ትክክለኛ የአከባቢያዊ ዝርያ ወይም የዛፍ ዝርያ ማለታችን ነው :: ለምሳሌ የጣውላ ምርት ማምረት የሚፈልግ አካል ወፍራምና ረጅም ሆነው ብዙ ምርት ሊሰጡ የሚችሉ መወላገድ የማያበዙና ቀጥ ያሉ ቅርንጫፋቸው የማይበዛና ወፍራም ቅርንጫፍ የማያወጡ ዛፎች ይመርጣል ፡፡ ፍራፍሬ ወይም መኖ ማምረት የሚፈልግ ሰው ደግሞ አጠር ብለው ብዙ ወፍራም ቅርንጫፎች ያላቸውን ብዙ ቅጠል ወይም ብዙ ፍሬ መሸከም የሚችሉትንና ጣፋጭ ፍሬ ያላቸውን አይነት እናት ዛፎች ይመርጣል ፡፡ መግቢያ . … Good timber tree Bad timber tree

7 Good firewood tree Bad firewood tree Good fodder tree Bad fodder tree

8 Selection of superior phenotypic seed tree

ፊዚካላዊ የዛፍ ጥራት ሢባል በዋናነት የሚነሳው ጉዳይ ዘሩ ከቆሻሻና ከለሎች ባዕድ ነገሮች ምን ያህል ንፁህ ነው የሚለው ሲሆን በአንድ ኪሎ ግራም ዉስጥ የሚኖረው የዘር መጠን ቆሻሻና ሌሎች ባዕድ ነገሮች በበዙ ቁጥር ስለሚቀንስ አነስተኛ የጥራት መጠን ያለውን ዘር መግዛት የማይመከርና ሀብትን አለአግባብ ማባከን ይሆናል :: የፊዚዮሎጂካሊ ጥራት ሲባል ደግሞ ዘሩ ለመበቀልና ችግኝ ለመሆን ያለውን እድል የሚያሳይ ነው :: የዘሩም የመቀበል ሁኔታ ናሙና ዘር በላብራቶሪ ፣ በችግኝ ጣቢያ ወይም በግሪን ሀዉስ ዉስጥ በተዘጋጁ የመዝሪያ ቁሶች ተጠቅሞ መፈተሸ የሚቻል ሲሆን ብቅለቱ በጣም አነስተኛ ሆኖ ከተገኘ ችግሩን ለመፍታት ልዩ ልዩ ጥናቶች ማካሄድ ያስፈልጋል :: የዚህ ማኑዋል አላማ የሚሆነው ከፍተኛ የጀኔቲክ ጥራት ያላቸውን የዛፍ ዘር ምንጮች ሥለማቋቋምና በምን አይነት አያያዝም ከምንጮቹ የሚገኘውን ዘር የተሻለ ማድረግ እደሚቻል ለማስገንዘብና የአሰራር ክህሎትን ለማዳበር ነው :: መግቢያ …..

ም ዕረፍ I. የዛፍ ዘር ምንጮችን ማልማት የተለያዩ በደን ልማት የታወቁ አገሮች ልምዶች እንደሚያሳዩት አዋጭነትና ውጤታማ በመሆነ መልኩ ጥራት ያለው የዛፍ ዘር በብዛት የማግኘት ጉዳይ የሚወሰነው ለዛፍ ዘር ምንጭነት በምንለያቸውና በምናለማቸው የዘር ምንጭ ደኖች መጠን ነው ፡፡ 1.1. የዛፍ ዘር ምንጭ ምንድን ነው ? የዛፍ ዘር ምንጭ ማለት ጥራት ያለው አንድ የተፈለገ ምርት ለማስገኘት ታስቦ ለሚከናወን ተከላ የሚዉል ዘር ሊሰበሰብባቸው የሚችሉ የተመረጡ ዛፎች ፣ የዛፎች ስብስብ ፣ የተፈጥሮ ወይም ሰው ሰራሽ ደን ፣ አሊያም ሁለገብ ጥራቱ ያለው ዘመናዊ የዘር መልቀሚያ ደን ማለት ነው ፡፡ የዘር ምንጮች በአካባቢው አስተዳደርና በብሄራዊ የደን ባለስልጣን ደረጃ ዝርዝር መረጃቸው ማለትም የሚገኙበት ቦታ የቦታ ካርታ እና ባለቤትነትን በሚመለከት ህጋዊ ሰነዶች በሥርዓቱ ተመዝግበው መያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡ ይህም ከደን ልማቱ ጋር በተያያዘ ከሚፈለጉ መረጃዎች በተጨማሪ የዘር ምንጮች ማንኛውም ጉዳት እንዳይደርስባቸውና ሙሉ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ለማድረግ ያግዛል ፡ የዛፍ ዘር ምንጮችን ማልማት

1.2. የዘር ምንጭ አይነቶች በልዩ ልዩ መንገዶች የዘር ምንጭ ደኖችን መከፋፈል ይቻላል ፣ ክፍፍም ከአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታና የልማት ግብ አንፃር የሚደረግ ሲሆን የዛፍ ዘር ምንጮችን መለየት ፣ መመዝገብ ማልማት ተገቢ ይሆናል :: የዘር ምንጭ ዓይኘቶች ክፍፍል መነሻ የሚያደርገው በስተመጨረሻ ከዛፍ ዘሮች የሚገኙ ደኖች ሊሰጡ የሚችሉትን ጥቅም ታሳቢ በማድረግ ሊሆን ይችላል :: ለምሳሌ ፣ በአውሮፓ የኢኮኖሚክ ልማት ኮሚሽን (OECD) የሚታወቁት የዛፍ ዘር ምንጭ ክፍፍሎች ለኢንዱስትሪ ግብዐትነት የሚሆኑ የደን ምርቶችን ታሳቢ የደረጉ ናቸው :: በዚህም መሰረት የዘር ምንጮች እንደከተለው ተለይተዋል ፡፡

1.2. የዘር ምንጭ አይነቶች … በአውሮፓ የኢኮኖሚክ ልማት ኮሚሽን (OECD) የሚታወቁት የዛፍ ዘር ምንጭ ክፍፍሎች : (1) የተለዩ የዘር ምንጮች (Identified Seed Stands (2) የተመረጡ የዘር ምንጮች (Selected seed stands)፦ (3) የዘር ማምረቻ ደን (Seed production area)፦ (4) የተመረጠ የአከባቢ ዝርያ የዘር ምንጭ (Provenance seed stand)፦ (5) የተሻሻለና ዘመናዊ የዘር ማመንጫ (Seed orchard)፦

1.2. የዘር ምንጭ አይነቶች … በአውሮፓ የኢኮኖሚክ ልማት ኮሚሽን (OECD) የሚታወቁት የዛፍ ዘር ምንጭ ክፍፍሎች : (1 ) የተለዩ የዘር ምንጮች (Identified Seed Stands)፦ ከተፈጥሮ ደኖችና ለሌላ አላማ ከለሙ ደኖች መካከል ለዘር ማመንጫነት ጥቅም ላይ እንዲውሉ በዛፍ ዘር አቅራቢው አካል የተመዘገቡ ደኖችን ያመለክታል :: (2) የተመረጡ የዘር ምንጮች (Selected seed stands)፦ ከተፈጥሮ ደኖችና ከሰው ሰራሽ ደኖች የዘር ምንጮችን ከመለየት ባሻገር መስፈርቶችን በማዘጋጀት ከተለያዩ ምንጮች የተሻሉትን መምረጥን ያካትታል :: ስለዚህም ከመጀመሪው አይነት የዘር ምንጭ ተጨማሪ ስራዎችን የሚጠይቅ ሲሆን በዘር ምንጭነቱም የተሻለ የዘር ምንጭ ደረጃን ያመለክታል ::

(3) የዘር ማምረቻ ደን (Seed production area)፦ ይህ የዘር ምንጭ አይነት በሁለት መልኩ ሊቋቋም ይችላል :: የመጀመሪያው መንገድ የሚሆነው በተራ ቁጥር 2 ከተጠቀሱት የዘር ምንጭ አይነቶች ላይ የማሻሻያ ሥራ በማካሄድ ነው :: የማሻሻያ ሥራውም በደኑ ውስጥ የማይፈለጉና በዕድገታችውና በይዞታቸው ደካማ የሆኑትን ዛፎችና በማስወገድ እና ደኑን ለዘር ለቀማ አመቺ እንድሆን በማድረግ ጭምር ነው :: ደካማ የሆኑ ዛፎችን አስወግዶ የተሻሉትን ማስቀረት የሚገኘውንም ዘር የተሻለ የጄነቲክ ይዘትና ጥራት እንዲኖረው ስለሚያደርገው ዘሩን የተሻለ ልንለው እንችላልን :: ስለዚህ ይህ የዘር ምንጭ ቀድሞ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ከተገለፁት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ የዘር ምንጭ ሆኖ እናገኛዋለን :: ሁለተኛው የዘር ማምረቻ ደን የማቋቋሚያው መንገድ ሰው ሰራሽ ደኖችን ለዘር ምንጭነት አላማ በመትከልና አስፈላጊዉን የማሳሳትና ሌሎች የክትትል ስራዎች በማካሄድ ነው :: 1.2. የዘር ምንጭ አይነቶች … በአውሮፓ የኢኮኖሚክ ልማት ኮሚሽን (OECD) የሚታወቁት የዛፍ ዘር ምንጭ ክፍፍሎች …

4) የተመረጠ የአከባቢ ዝርያ የዘር ምንጭ (Provenance seed stand)፦ ይህ አይነቱ የዘር ምንጭ ደን የተመረጠ የአካባቢ ዝርያን በመትከል ወይም ለምርት ከተተከሉ ልዩ ልዩ የአከባቢ ዝርያዎች (provenance) መካከል የተሻለውን በማስቀረት ለዘር ማመንጫነት መንከባከብን ይጠይቃል :: ሥለዚህም በአከባቢ ዝርያዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ እንደ መሆኑ እሰካሁን ከተዘረዘሩት መካከል ብዙ ገንዘብ የሚያስወጣና የተሻለ የዘር ምንጭ ነው :: (5) የተሻሻለና ዘመናዊ የዘር ማመንጫ (Seed orchard)፦ ይህ አይነቱ የዘር ማመንጫ በሁለት መልኩ ሊቋቋም ይችላል :: ይኸውም ሀ) ከችግኝ እና ለ) ከቁርጥራጭና ለሎች ዘር ካልሆኑ የዕፅዋቱ አካላት (vegetative) ዘዴ ሊቋቋም ይችላል :: ከችግኝ ያልሆነው የዘር ምንጭ ክሎናል ( clonal ) የዘር ማመንጫ በመባል ይታወቃል :: የተሻሻለና ዘመናዊው የዘር ማመንጫ ችግኞች ወይም ክሎኖች መነሻ የሚሆነው ከተመረጡ እናት ዛፎች የተቋቋመ የዛፍ ማሻሻያ ሙከራ ሊሆን ይችላል :: የተሻሉ ስለመሆናቸው ከተረጋገጡት እናት ዛፎችም ዘሮችን እና ሌሎች የመባዣ አካላትን በማሠባሠብም ሊካሄዱ ይችላል :: ይህ ዓይነቱ የዘር ምንጭ የመጨረሻው ደረጃ የዘር ምንጭ በመባል ይታወቃል :: 1.2. የዘር ምንጭ አይነቶች … በአውሮፓ የኢኮኖሚክ ልማት ኮሚሽን (OECD) የሚታወቁት የዛፍ ዘር ምንጭ ክፍፍሎች …

የጥምር እርሻና ደን ሥራን ( agroforestry ) ማዕከል ያደረገው የዘር ምንጭ አከፋፈል የእርሻ ማሣ :- እንደሚታወቀው በእርሻ ማሳና በቤቶች ዙሪያ እጅግ በርካታ የዛፍ ዝርያዎች በተፈጥሮ በቅለውና ለምተው ጭምር ይገኛሉ ፡፡ እነዚህ ዛፎችን ለዘር ምንጭነት መጠቀምን ማዕከል ያደረገ ዘር ምንጭ የእርሻ ማሳ ዘር ምንጭ ተብሎ ይታወቃል ፡፡ ዘመናዊ የዘር ማመንጫ ደኖች (Seed Orchards ) የእናት ዛፎች ምንጮች ወይም ቤተሰቦች የታወቁና የጄኔቲክ ( ዘረ-መል ) ጥራታቸው ከፍተኛ ደረጃ ያለው ሲሆን ብዛት ያለው ዘር መስጠት እንዲችሉ የተያዩ እንክብካቤዎች (intensive management) የሚደረግላቸው ናቸው ፡፡ ዘመናዊ የዘር ማመንጫ ቦታዎች በሌሉበት ሁኔታ አንጻራዊ በሆነ መልኩ ጥራት ያለው ዘር በበቂ ሁኔታ ለማግኘት ሌሎች ከ 2 እስከ 4 የተዘረዘሩት የዘር ምንጮቸ እንደጊዜያዊና ፈጣን አማራጭ ይወሰዳሉ ፡፡ የዘር ማመንጫ ደኖች በአጠቃላይ የሚፈለጉ የዛፍ ባህሪያትን በላቀ ሁኔታ በሚያሳዩት ዉጫዊ ገጽታ ፣ ጤናማ የሆኑ ፣ ጥራት ከጎደላቸው ዛፎች በወንዴ ዘር ስርጭት የማይደርስባቸው በመሆኑም የዘረ-መል ጥራታቸው የተጠበቀ እንዲሆኑ ይፈለጋል ፡ ፡ ሆኖም እነዚህን ባህሪያጥ ለማሟላት ለሌላ ዓላማ የተተከሉ ደኖች ሙሉ ስለማይሆኑ የዘር ምጭ ይሆናል ተብሎ ከተፈጥሮ ወይም ሰው ሰራሽ ደኖች ከተለዩ በኋላ የእንክብካቤ ሥራ በተለይም ጥራት የሌላቸውን ዛፎች እየለዩየማስወገድ ፣ ማሳሳት ፣ እንዲሁም ሊገኝ የሚችለውን የዘር መጠን ለመጨመር ጫፋቸውን የመቁረጥ ሥራ ማከናወን ያስፈልጋል ፡፡

(1) የተለዩ የዘር ምንጮች (Identified Seed Stands (2) የተመረጡ የዘር ምንጮች (Selected seed stands)፦ (3) የዘር ማምረቻ ደን (Seed production area)፦ (4) የተመረጠ የአከባቢ ዝርያ የዘር ምንጭ (Provenance seed stand)፦ (5) የተሻሻለና ዘመናዊ የዘር ማመንጫ (Seed orchard)፦ 6) የእርሻ መሬት (Farm land trees) Seed Orchards Provenance Seed Stand Seed Production Area Selected Stands Identified Stands Farmland Trees የዘር ምንጭ ደኖችን በአይነት በአይነት ለይቶ መመዝገብ ያስፈልጋል ፡፡ የዘር ምንጭ አይነቶች በኢትዮጵያ በኢትዮያ የሚታወቁት የዛፍ ዘር ምንጭ ክፍፍሎች

1.2. የዘር ምንጮችን ማቋቋም የዘር ምንጮች በሁለት መሠረታዊ መንገዶች ሊቋቋሙ ይችላሉ ፡፡ ይኸውም ነባር ምንጮች ለይቶ በመመዝገብ ወይም ዘር ማምረትን ዋነኛ ዓላማው ያደረገ የደን ተከላን በማካሄድ ነው ፡፡ የሚከተሉትን የዘር ምንጭ ደኖች በኢትዮጵያ ማቋቋም ጠቃሚ ይሆናል ፡፡

የተፈጥሮ ደን የዘር ማመንጫ ማቋቋም ፡- በኢትዮጵያ የሚገኙ ደጋማና ቆላማ ደኖች በባህሪያቸው በርካታ የዝርያ ስብጥር ይታይባቸዋል ፡፡ የተለያዩ የዛፍ ዝርያዎችም በአንድ የተፈጥሮ ደን ወይም በአንድ አካባቢ ተወስነው የሚገኙ ሳይሆኑ ይልቁንም በበርካታ ደኖችና አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው ፡፡ ስለዚህ አካባቢያዊ ዝርያዎች (provenances) ጀነቲካዊ ተለያይነት ሊኖራቸው እንደሚችል ይገመታል ፡፡ ስለዚህም ከተፈጥሮ ደን የዘር ምንጭ ሲለይ ይህንን በዝርያቸው ውስጥ ያለ ተለያይነት ከግምት ውስጥ ማስገባትና ወካይ ሊባሉ በሚችሉ አካባቢዎችና ደኖች ውስጥ የዘር ምንጮችን መለየት ተገቢ ይሆናል ፡፡ እነዚህን የተለዩ የዘር ምንጭ ደኖች በአግባቡ መመዝገብና በካርታ ላይ ማሳይት አስፈላጊ ይሆናል ፡፡ የተፈጥሮ ደኖች በባሕሪያቸው ምርጫ የተካሄደባቸውና መሻሻል የተደረገባቸው ሳይሆኑ ከጥሩ እስከ መጥፎ ከደካማ እስከ ብርቱ ሁሉም አይነት ዛፎች ተቀላቅለው የሚገኝባቸው ኛቸው ፡፡ በአንድ አካባቢ አድገው የሚገኙ ዛፎች በተጨማሪም ዘራቸው ወደ ኋላ ሲጠና ከአንድ እናት ዛፍ የተገኙና ቤተሰብነት ያላቸው ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ ስለዚህ የቤተሰባዊ አደረጃጀት (family structure) ሊኖር እንደሚችል ይገመታል ፡፡ እነዚህን ከላይ የተገለፁ ሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች በማጤን ለተሻለ የዘር ለቀማ የሚከተሉትን ሁለት ስልቶች መከተል ተገቢ ይሆናል ፡፡

በተፈጥሮ ደን ውስጥ የተሻሉ የእናት ዛፎች የመምረጥ በተፈጥሮ ደን ውስጥ የተሻሉ የእናት ዛፎች የመምረጥ ስልት ስለመረጥናቸው እናት ዛፎች ጥሩነት በከፊል (50%) እርግጠኞች ያደርገናል ፡፡ በከፊል ብቻ ሲባል የወንዴው ዘር ከየትኛው ዛፍ ላይ ተነስቶ መጥቶ የተመረጠችው እናት ዛፍ እንደደቀለ ስለማናውቅ ነው ፡፡ ለምን ታዲያ ምርጥ ምርጥ ዛፎችን አስቀርተን የማንፈለልጋቸውን በማስወገድ የዘር ምንጩን አናሻሽለውም የሚል እጅግ ተገቢ የሆነ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል ፡፡ ሆኖም ይህ ተግባር የደኑ ባለቤት በሆነውና በሚያስተዳድረው አካል ተቀባይነት የሌለው አሰራር ሊሆን ስለሚችልና የወንዴ ዘሮችም ቢሆኑ ከምን ያህል ርቀት መጥተው በመረጥናቸው ዛፎች ላይ ሊያርፍና ሊደቅሉም እንደሚችል ማረጋገጫ ስለሌለን በዚህ አቅጣጫ ብዙም ማድረግ አይቻልም ፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የወንዴ ዘሮች በንፋስ ፣ በነፍሳትና በወፎች አማካኝነት በርካታ ኪ/ ሜትር ሊጓዙና ሊደቅሉ ይችላሉ ፡፡ ስለዚህም የተሻሉ እናት ዛፎችን በበቂ ቁጥር (25 አካባቢ ) ለዘር ምንጭነት ችንደ አጥጋቢና አይነተኛ ስልት ነው ፡፡

በተፈጥሮ ደኖች ውስጥ የእናት ዛፎች ስንመርጥ ርቀትን መጠበቅ ፡- ይህ ስልት አስፈላጊ የሚሆነው በተፈጥሮ ደን ውስጥ ሊኖር ይችላል የሚባለውን ቤተሰባዊ አደረጃጀት ግምት ውስጥ በማስገባት ነው ፡፡ ተለያይነት (genetic variation) በምናደርገው የዘር መሰብሰብ ሥራ ውስጥ አስፈላጊ ነው ፡፡ ይህም ከአንድ ዛፍ ወይም ከአንድ ቤተሰብ ውስጥ ዘሮችን ለቅመን የምንሰራ ከሆነ ተለያይነት አይኖራቸውም ወይም እጅግ አነስተኛ ይሆናል ፡፡ ተለያይነት አለመኖር ከአጭር ጊዜ ጥቅም አንጻር ምንም ጉዳት ላይኖረው ይችላል ፡፡ ሆኖም ግን ከረጅም ጊዜ አንጻር በሽታና አካባቢያዊ ጫናዎች ሲፈጠሩ በዚህ መልክ ሰብስበን ያለማንው ደን ችግሮቹን የመቋቋም አቅም ላይኖረው ይችላል ፡፡ ስለዚህ ተፈጥሮ ደን ውስጥ ያለውን ቤተሰባዊ አደረጃጀት ተረድተን የምንመርጣቸው እናት ዛፎች ከተለያየ ቤተሰብ የመጡ መሆኑን ለማረጋገጥ በሁለት እናት ዛፎች መካከል የሚኖረው ርቀት ከ50 እስከ 100 ሜትር ቢያንስ መራራቅ ይኖርባቸዋል ፡፡ በባህሪያቸው ከበድ ያለ ፍሬ ያላቸው ዛፎች ዘር በአብዛኛው ብዙ ርቀት ስለማይጓዝ 50 ሜትር ሊበቃ ይችላል ፡፡ ቀለል ያለ ፍሬ ላላቸው ዛፎች ደግሞ 100 ሜትር እንደማለት ነው ፡፡

የሰው ሰራሽ ደኖች ከሀገር በቀል ዝርያዎች ወይም ከውጭ አገር ዝርያዎች እንጨት ለማምረት በሚል አላማ ለምተው ሊገኙ ይችላሉ :: በኢትዮጽያ በስፋት በሠው ሠራሽ ደን መልክ ለምተው ከሚገኙት ዝርያዎች መካከል ነጭ ባሕርዛፍ ፡ ቀይ ባሕርዛፍ ፡ የፌረንጅ ጥድ ፡ ፓይነስ እና የአበሻ ጥድ የመሣሠሉት ይገኙበታል ፡፡ በአብዛኛዎቹ የሠው ሠራሽ ደኖችን በተመለከተ የጄነትክ ታሪካቸው ላይታወቅ ይችላል ፡፡ ስለዚህም ደኑ ሢመሠረት ስለዘር ምንጩ ግልፅ የሆነ መረጃ አለመኖሩ እያባዛን ስለምንገኘው የዛፍ ዘር ጥራት እርግጠኞች እንዳንሆን ያደርገናል ፡፡ ሆኖም የሠው ሠራሽ ደኖችን ለዘር ምንጭነት መጠቀም የተለመደ ነው ፡፡ በሠው ሠራሽ ደኖች ውስጥ በተፈጥሮ ደን እንዳለው የቤተሠባዊ አደረጃጀት አይገኝም ፡፡ በሠው ሠራሽ ደኖች ግን ሁለት አይነተኛ ባሕርያት እንመለከታለን ፡፡ እነዚህም 1) የሠው ሠራሽ ደኖች እድሜያቸው በግልፅ የሚታወቅ መሆኑ እና 2) በአብዛኛው ያልተቀላቀሉና በአንድ አይነት ዝርያ ብቻ የተመሠረቱ መሆናቸው ፡፡ ሥለዚህ ከሠው ሠራሽ ደኖች መካከል ዘሮችን ለመልቀም ስንወስን 1) ተመሣሣይ ዕድሜ ካላቸው መካከል የተሸሉ የሚባሉትን ዛፎች መምረጥ 2) በዛሮች መካከል ርቀት መጠበቅ ሣያስፈልገን እናት ዛፎችን በስፋት መምረጥ እንችላለን ፡፡ የሰው ሰራሽ ደኖች የዘር ምንጭ ማቋቋም ፡ -

በሌላ መልኩ በነባር የሠው ሠራሽ ደኞች ውስጥ የዘር ምንጮችን ለይቶ ከማቋቋም ባሻገር አዳዲስ ተከላዎችን በማካሄድ የዘር ማቋቋም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ፡፡ ይህም የሚሆነው የዘር ምንጭ ከውጭ ሀገር በቀጥታ የሚገባ ሲሆን ነው ፡፡ ለምሳሌ የደን ምርምር ማዕከል የግራቪሊያን ዘር ከውጭ ሀገር በማስመጣት በይርጋለም፡በሀገረማርያም እና በበዳሌ አከባቢዎች የሠው ሠራሽ ደኖችን ማቋቋሙ ይታወቃል ፡፡ ሁለተኛውን ትውልድ የግራቪሊያ በሠው ሠራሽ ደን መልክ ለዘር ምንጭነት ለመተከል ሲታሰብ የእናት ዛፎችን በመምረጥ በብሎኮች ዘመናዊ የዘር ማመንጫ ተከላዎችን ማካሄድ ተመራጭ ይሆናል ፡፡

በእርሻ ማሳዎች በርካታ የዛፍ ዘሮች በቤት ዙሪያ (homestead) በሰብል መሬት (crop-land)፣ በግጦሽ መሬት (grazing land) ፣ በአነስተኛ ደኖች (small-scale plantation) እንዲሁም በመስመር ተከላዎች ውስጥ ይገኛሉ ፡፡ እነዚህ የእርሻ ላይ ዛፎች በተፈጥሮ ደን እና በሰው ሰራሽ ደኖች ውስጥ እንደሚገኙት ዛፎች ሁሉ እጅግ ጠቃሚ የጀነቲክ ሀብት ናቸው ፡፡ በእርሻ ማሳ የሚገኙ ዛፎችን ለዘር ምጭነት ላለመጠቀም ዛፎቹ የተለዩ (isolated) ስለሆኑ ለደካማነት (inbreeding depression) የተጋለጡ ናቸው የሚል ክርክር በአንዳንድ ወገኖች ሊነሳ ይችላል ፡፡ ሆኖም ግን በማሳ ላይ ተራርቀው መገኘታቸው እውን የእርስ በዕርስ መዳቀልን ከልክሏል ወይ የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ይሆናል ፡፡ እውነታው ግን ሲታይ የዛፎች የወንዴ ዘር ባብዛኛዎቹ ዝርዎች ዘንድ ብዙ ርቀት መጓዝ ይችላል ፡፡ በቅርቡ የተጠኑ አንዳንድ ጥናቶች በማሳ ላይ ተበታትነው የሚገኙ ዛፎች መካከል ሰፊ የጀነቲክ ተለያይነት እንዳለና የዘር ፍሰት (gene flow) ያልተገደበ እንደሆነ ነው ፡፡ ስለዚህም የእናት ዛፎችን በመምረጥ የእርሻ ማሳ ዛፎችን ለዘር ምንጭነት መጠቀም ይቻላል ፡፡ የእርሻ ማሳ የዛፍ ዘር ምንጮች ማቋቋም

በተራ ቁጥር 1 እስከ 3 የተጠቀሱት የዘር ምንጮች ከነባር ደኖች ወይም ተከላዎች በመለየትና በመመዝገብ የሚካሄድ ነው ፡፡ ሆኖም ከዚህ ቀጥሎ የምንመለከተው ከተሻሉ የእናት ዛፎች የመጡ ዘሮችን ወይም ከዘር ውጭ የሆኑ መራቢያዎችን በመጠቀም ለዘር ምንጭነት ሰው ሰራሽ ደኖችን ማቋቋምን የሚመለከት ነው ፡፡ በሁለት መሰረታዊ ስልቶች የሚከናወን ነው ፤ ዘመናዊ የተሻሉ የዘር ምንጮችን ማቋቋም

ይህ ሥራ ያለፉ ስህተቶችን በማረም በስፋት ሊሰራበት የሚገባ ለዘር ምንጭነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የሰው ሰራሽ ደኖችን ማቋቋምን ይመለከታል ፡፡ ለምሳሌ የደን ምርምር ማዕከል የኮሶን ፣ የጥድን እና የዋንዛን ዛፎች ከተፈጥሮ ደኖች በማሰባሰብ ሰው ሰራሽ የዘር ምንጮችን በኮፈሌ በበደሌና በአጋሮ አካባቢዎች ለማቋቋም ሙከራዎች አድርጓል ፡፡ ሆኖም ዘሮቹ የተሰበሰቡት ከተሻሉ እናት ዛፎች ተመርጠው አልነበረም ፡፡ ሥለዚህም በብሎኮች የተከፋፈሉ ተከላዎች አይደሉም ፡፡ በተሰራው ስራ እነዚህን የአገር በቀል ዝርያዎች በሰው ሰራሽ ደንነት በተሳካ ሁኔታ ማቋቋም እንደሚቻል ትምህርት የተወሰደባቸው መሆናቸው ግን መዘንጋት አይኖርበትም ፡፡ በቅርቡ ግን በዋንዛ ላይ በቴፒና በመሆኒ አካባቢ የተቋቋሙት በእናት ዛፎች መረጣ ላይ የተመሰረቱና በብሎክ የተከፋፈሉ የምርምር ተከላዎች ግን ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ ጉዞ መጀመራችንን የሚያሳዩ ናቸው ፡፡ ሀ. በችግኝ የሚቋቋም የዘር ምንጭ (seedling seed orchard)፡-

1ኛ ) በቂ ( ከመቶ እስከ ሶስት መቶ ) እናት ዛፎችን መምረጥ 2ኛ ) የእያንዳንዱን ዛፍ ፍሬ / ዘር ለይቶ መያዝ 3ኛ ) ከአንድ እናት ዛፍ የመጡ ችግኞች (progenies) አንድን ቤተሰብ (family) ስለሚወክሉ እነዚህን ችግኞች ከሌላው ሳይቀላቅሉ ማዘጋጀትና 4ኛ ) እያንዳንዱን ቤተሰብ በብሎኮች ከፋፍሎ መትከል ያስፈልጋል ፡፡ የችግኝ የዘር ኦርቻርዶችን ለማቋቋም መከተል የሚገቡን ነጥቦች ፡

ሠንጠረዥ 1. የመቶ ቤተሰቦች ኦርቻርድ አተካከሉ በሚከተለው ሠንጠረዥ በተመለከተው መልክ ሊከናወን ይችላል ፡፡ የብሎክ ቁጥር ለዛፍ ቤተሰቡ የተሰጠው መለያ (100 ቤተሰብና ከዚያ በላይ ) 1 * * (1) * ) * * * (2) * ) * * * (3) * ) * * * (4) * ) * * * (5) * ) * * * (6) * ) * … ) … … * * (99) * ) * * * (100) * ) * 2 * * (99) * ) * * * (17) * ) * * * (67) * ) * * * (71) * ) * * * (85) * ) * * * (35) * ) * … ) … … * * (59) * ) * * * (10) * ) * 3 * * (43) * ) * * * (57) * ) * * * (39) * ) * * * (100) * ) * * * (48) * ) * * * (94) * ) * … ) … … * * (1) * ) * * * (69) * ) * 4 * * (80) * ) * * * (63) * ) * * * (78) * ) * * * (26) * ) * * * (50) * ) * * * (3) * ) * … ) … … * * (4) * ) * * * (78) * ) * … … ) … … … ) … … … ) … … … ) … … … ) … … … ) … … … ) … … … ) … … … ) … … … ) … … … ) … … … ) … … … ) … … … ) … … … ) … … … ) …

የችግኝ ዘር ኦርቻርድ እንደ አንድ ትልቅ የጄነቲክ ሙከራ (progeny trial) ሊቆጠር የሚችል ሲሆን ደካማ ቤተሰቦችን በማስወገድ እየተሻሻለ ሊሄድ የሚችል ሰው ሰራሽ የዘር ማመንጫ ደን ነው ፡፡ ይህ አይነቱ የዘር ማመንጫ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት የሚገባ ሲሆን በሁለት መሠረታዊ ስልቶች ሊካሄድ ይችላል ፡፡ ይህም ማለት ዘሮቹ ከተመረጡ እናት ዛፎች የሚመጡበት ስልት (half-sib) አንዱ ሲሆን እናት ዛፎችን መርጦ በሰው ሰራሽ መንገድ በማዳቀል (controlled pollination) ዘሮቹ የሚገኙበት (full-sib) መንገድ ሌላው ነው ፡፡ ሆኖም በሰው ሰራሽ መንገድ ዛፎችን ማዳቀል ውድና አድካሚ ሥራ ስለሆነ በስፋት የሚሰራበት የመጀመሪያው ስልት (half-sib) ነው ፡፡ ምክንይቱም በማንኛውም የተፈጥሮ ደን ፣ የሰው ሰራሽ ደንም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የምናገኛቸው የዛፍ ዘሮች በሙሉ በእናት ብቻ የሚገናኙ (half-sib) ስለሆኑ ነው ፡፡ ይህም የሚሆነው የወንዴ ዘር ምንጭ ሌላ በአካባቢው ያለ ማንኛውም ዛፍ ሊሆን ስለሚችል ነው ፡፡ ይህ ክፍፍል ግን ሙሉ በሙሉ የራስ በራስ ድቀላ (self-pollination) በሚያካሂዱ ዝርያዎች ላይ አይሰራም ፡፡ ምክንያቱም ከእንዲህ ያሉ ዝርያዎች የሚገኙ ዘሮች በሙሉ ተመሳሳይነት ያላቸው (full-sib) ናቸውና ፡፡ ከላይ እንደተገለጸው በሰው ሰራሽ መልኩ ሙሉ ተዛምዶ ያላቸው ዘሮች (full-sib) በሰው ሰራሽ መንገድ በማዳቀል መፍጠር ይቻላል ፡፡ ይኸውም ከተመረጡት እናት ዘሮች መካከል የተወሰኑትን እንደ ወንዴ ዘር ተቀባይ ሌሎቹን ደግሞ እንደ ወንዴ ዘር ሰጪ በማድረግ በማዳቀል ነው ፡፡

ከላይ ለተዘረዘሩት በሙሉ እጅግ ተፈላጊው የዘር ምንጭ አይነት ነው ፡፡ በመሠረቱ ከችግኝ ከሚነሳው ኦርቻርድ ጋር ተመሣሣይነት አለው ፡፡ ልዩነቱ ከችግኝ የሚቋቋም የዘር ምንጭ ከእናት ዘፎች የሚሰበሰበው ዘር ሲሆን በዚህኛው አሠራር ግን የሚሰበሰበው ዘር ሣይሆን ቁርጥራጭ ወይም ዘር ያልሆነ የመራቢያ ዘዴ መሆኑ ነው ፡፡ ይህ የዘር ምንጭ የማቋቋሚያ ዘዴ ከዘር ውጭ በቀላሉ ለሚራቡ የዛፍ ዝርያ ዘይነቶችን እጅጉን ተመራጭ ነው ፡፡ የኢትዮጵያ አርሶ አደር እንደ ኮርች ፣ ቀርከሃ የመሣሠሉ ዝርያዎችን በቁርጥራጭ እንደሚያባዛ ይታወቃል ፡፡ በዘመናዊ መንገዶችም ማለት በቲሹ ከልቸር ወይም በተለያዩ የማክሮ የማባዣ (macro propagation) ዘዴዎች ዛፎችን በተሳካ ሁኔታ ማባዛት እንደሚቻል ጥናቶች የሳያሉ ፡፡ በደብረብርሃን አካባቢ ስፔን አገር ተዘጋጅተው የመጡ የነጭ ባሕርዛፍ ሁለት ከሎኖች ተተክለው የሚገኙ ሢሆን በልዩ ልዩ የአገር በቀል ዝርያዎች ላይም በአዲስ አበባ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ለአብነት ሊጠቀሡ ይችላሉ ፡፡ ስለዚህም የእናት ዛፎች ተመርጠው ፣ ክሎኖች ከተዘጋጁ በኋላ ልክ የችግኝ ኦርቻርድ ስናቋቋም የምነከተለውን በብሎኮች የመተከል ዘዴ በመትከል የከሎናል የዘር ምንጮችን ማቋቋም እንችላለን ፡፡ ለ ) ከዘር ውጭ በማራባ ዘዴ የተዘጋጀ ዘመናዊ የዘር ምንጭ ( clonal seed crchard /

የዘመናዊ የዘር ምንጭ ደኖች አለማምና አያያዝ ከዚህ በታች ዘመናዊ የዘር ምንጭ /seed orchard/ ደኖችን አለማምና አያያዝ እንመለከታለን ፡፡ ለዘር ምንጭ ልማት የሚመረጡ ዝርያዎች በከፍተኛ ጥንቃቄና በሣይንሣዊ መንገድ የተመረጡ /Priority/ ዝርያዎች ሊሆኑ ይገባል ፡፡ ይኸውም ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ የረጅም ጊዜ ፕሮግራም በማዘጋጀት ሊሠራ የሚገባው ጉዳይ እንጂ ዘላቂነት በሌለው ያዝ-ለቀቅ በሚል ሁኔታ የሚሠራ ባለመሆኑ ጭምር ነው ፡፡ ከዚህ ቀደም የተሠሩና በመስክ ላይ የሚገኙ ሥራዎችን መለስ ብለን ብንመለከት የቀይ ባሕርዛፍ የጄነቲክ ማሻሻያ ሙከራ /Progeny trial/ በማንኩሳ አካባቢ እና የዋንዛ ተመሣሣይ ሙከራዎች በቴፒና በመሆኒ አካባቢዎች እንዳሉ እንመለከታለን ፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ የዘመናዊ የዘር ምንጭ /seed orchard/ ጥንስሶች ፡፡ የቀይ ባሕርዛፍ ተከላውን በተለየ ሁኔታ ብንመለከት ሁለት ጥናቶች የካሄድበት የቆየ ሙከራ ነው ፡፡ ይህ ሙከራ እስከ 405 የሚደርሱ ቤተሠቦች በብሎኰች የተተከሉበት ሙከራ ነው ፡፡ ይህንን ሙከራ በቀጥታ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዘመናዊ የዘር ምንጭ /seed orchard/ ብሎ መበየን /declare/ ይቻላል ፡፡

ይህንን የዘር ምንጭ 1 ) እድሜው 25 ዓመት ሆኖታል ፡፡ ምናልባትም ሙሉ በሙሉ በመቁረጥ መልሶ እንዲያቆጠቁጥ /Coppice/ እንዲያደርግ ማድረግ ለማባዛት ስራዎች አስፈላጊ ይሆናል ፡፡ 2 ) ደካማ የሆኑ ቤተሠቦችን መልሰው እንዳያቆጠቁጡ የሚያደርግ አሠራርን መከተል ይገባል ፡፡ 3 ) በሌሎች ቦታዎችም ክሎናል በሆነ ዘዴ ተመሣሣይ የዘር ምንጮችን ለማቋቋም ምርምር ማካሄድ ተገቢ ይሆናል ፡፡ 4 ) በተጨማሪም ሠፊ የእናት ዛፎች መረጣ በአገር አቀፍ ደረጃ በማካሄድና በመቁረጥ ጉቶው ሲያቆጠቁጥ /Coppice/ ክሎኖችን በመሠብሠብና ከማንኩሳ ከሚገኘው ክሎን ጋር በማደባለቅ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የዘር ምንጭ የሚሆኑ /Clonal Seed orchards/ ማቋቋም ተገቢ ይሆናል ፡፡ ለዚህም የቀይ ባሕርዛፍ የማሻሻያ ፕሮግራም በዝርዝር ተዘጋጅቶና አስፈላጊው በጀት ተመድቦለት ሊሠራ ይገባል ፡፡ በዚህ ላይ የሚሠራው የተጠናከረ የምርምርና የማባዛት ስራ ሰፊ አገራዊ አቅም በሚፈጥርበትና በሌሎች ዝርያዎች ላይ ለሚሠሩ ሥራዎች እንደ መነሻ ተደርጒ ሊቀረጽ ይገባል ፡፡ በተጨማሪም በዋንዛና በጥድ ላይ የተጀመሩና በመጀመር ላይ ያሉ መሠል የጀነቲክ ማሻሻያ ሙከራዎች /progeny trials/ ተጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል ፡፡

የዘር ማመንጫ ኦርቻርዶችን ልማትና አያያዝ በተመለከተ የሚሠሩ ዝርዝር ሥራዎች በሚከተሉት መርሆዎች ላይ የሚያጠነጥኑ ይሆናሉ ፡፡ ወካይ ቦታዎች ፡- ኦርቻርዶች ወካይ በሆኑና በተመረጡ የደን ልማቱንና የዘር ስርጭት ቀጠናዎችን ወይም መመሪያዎችን ባገናዘበ መልኩ በተመረጡ ቦታዎች ላይ ሊለሙ ይገባል ፡፡ ተደራሽነት /Accessibility/:- የኦርቻርዶች ልማት ተደራሽ በሆኑ አመቺ ሥፍራዎች ሊለሙ ይገባል ፡፡ ጥሩ መሬት ፡- የኦርቻዶቻ ልማት በተጐዱና በሞቱ መሬቶች ላይ ሣይሆን ጥሩ ለምነት ባላቸው እና አቀማመጣቸውም አመቺ በሆኑ ቦታዎች ላይ ሊለሙ ይገባል ፡፡ እንዲህ ዓይነት መሬት እጅግ ውድ በሆነ ሁኔታ የተዘጋጁትን ከምርጥ እናት ዛፎች የተገኙ ችግኞች ወይም ክሎኖች ለማፅደቅና ለፈጣን እድገት አይነተኛ ሀብት ነው ፡፡ ከማይፈለጉ የወንዴ ዘሮች ማራቅ ፡ የኦርቻርዶች ልማት ከሌሎች ካልተመረጡ ዛፎች ዘሮች በተቻለ መጠን መጠበቅ ይኖርበታል ፡፡ ከተከላ በኋላ የሚደረግ እንክብካቤ ፡- የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁና ለፈጣን እድገት ሲባል የተጠናከረ የአረምና ኩትኳቶ ሥራ ፣ ውሃ የማጠጣትና ማዳበሪያ የመጨመር የተጠናከረ ሥራ በተለይ በመጀመሪያው ሁለት ዓመታት ማካሄድ በጣም አስፈላጊ ነው ፡፡

የዘር ምንጭ ዛፎች ብዛት ፡- በዘር ምንጭ ልማት ልክ እንደሌሎች የደን ልማቶች በብዙ ችግኞች ጀምሮ በማሳሳት ወደ አነስተኛ ቁጥር ይኬዳል ፡፡ ሆኖም ከሌሎች የተከላ ዓይነቶች በተለይ የመጨረሻው የዛፎች ቁጥር አነስተኛ ወይም ከ 300-500 ዛፎች በሄ /ር መሆን ይገባዋል ፡፡ ከመነሻው ጀምሮ ዛፎች ራቅ ራቅ ብለው ያለምንም ችግር ጠንካራና ብዙ ቅርንጫፎችን እንዳያወጡ መሰራት አለበት ፡፡ ይህም የዘር ምርትን በከፍተኛ ደረጃ የሚጨምር አሰራር ነው ፡፡ የዘር ምንጭ ዛፎች ቁመት ፡- የዘር ምንጭ ዘፎች ለለቀማ አስቸጋሪ ረዣዥም ዛፎች መሆን የለባቸውም የዘር ምንጭ ዛፎች ይልቁንም ለለቀማ አመቺ አጠር አጠር ያሉ መሆን አለባቸው ፡፡ ስለዚህም ከአናት መቆረጥ /pollarding/ ዛፎችን አጭር እንዲሆኑ የሚያደርግ በመሆኑ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል ፡፡ ሆኖም በዚህ ዓይነት ማኔጅመንት ምክንያት በተፈጥሯቸው ሊጎዱ በሚችሉ ዝርያዎች ላይ ከአናት መቁረጥን ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም ፡፡ በዚህ ረገድ ዛፎች ከአናት ሲቆረጡ በሚሰጡት ምላሽ ላይ ምርምሮችን ማካሄድ አስፈላጊ ነው ፡፡ እንደ ግራቪሊያ ፣ ዋንዛ የመሳሰሉ ዛፎች አናታቸው ሲቆረጥ ለጎን ስለሚያቆጠቁጡ የአናት ቆረጣ ተግባራዊ ሊደረግባቸው እንደሚችል ያሣያል ፡፡

ለማጠቃለል ኦርቻርጆች ምንም እኳን ከተመረጡ እናት ዛፎች የመጡ ቢሆንም በሰፊ አተካከል /spacing/ እና በአናት ቆረጣ /pollarding/ ምክንያት የማያምሩ ዛፎች ስብስብ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ ሆኖም እነዚህ ናቸው የጥሩና የምርጥ ዘር ምንጮች ፡፡ ኦርቻርዶችን በተመለከተ የሚደረግ ምዝገባ ሌሎችን የዘር ምንጮች በተመለከተ ከሚደረገው የምዝገባ ዝርዝር በተጨማሪ የእናት ዛፎችና ቤተሰቦች ቁጥር ፣ ዝርዝርና ማንነት ፣ የተከላና የማኔጅመንት ዝርዝር መረጃዎች በየጊዜው ሊያዝላቸው ይገባል ፡፡

የዘር ምንጭ ደኖች ምዝገባ የዘር ምንጭ ደኖችን በአይነት በአይነት ለይቶ መመዝገብ ያስፈልጋል ፡፡ በተጨማሪም ያሉበት ጂኦግራፊያዊ ቦታ ፣ ከፍታ ፣ የተፈጥሮ ዕፅዋት ዓይነት ፣ የአየር ሁኔታ ፣ የመረጡ የእናት ዛፎች ብዛት ፣ በአካባቢ ያሉ ሥጋቶች ፣ የደኑ አስተዳደር የመሣማሉትን መመዝገብና የዘር ምንጭ ደኑን የሚያሣይ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የታገዘ ካርታ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው ፡፡ ይህ አይነቱ ምዝገባ የተመሠከረለት /Certified/ ዘር ለማቅረብ እንደመነሻ ሊያገለግል ይችላል ፡፡ ይህም ማለት ማንኛውም መንግስታዊም ሆነ የግል ዘር አቅራቢ የሚያሰራጫቸው ዘሮች ከነዚህ ምንጮች መሆኑን የሚያስገድድ አሠራር ለማስተዋወቅና የዘሮችን የጄነቲክ ጥራት ደረጃ ለመወሠን የሚረዳ ይሆናል ፡፡